Get Mystery Box with random crypto!

በ12 አገራት ወደ 80 የሚጠጉ ሰዎች በዝንጀሮ ፈንጣጣ (ሞንኪፖክስ) መያዛቸው መረጋገጡን የዓለም | Esat tv

በ12 አገራት ወደ 80 የሚጠጉ ሰዎች በዝንጀሮ ፈንጣጣ (ሞንኪፖክስ) መያዛቸው መረጋገጡን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ

የአገራቱን ስም ሳይገልጽ ሌሎች 50 ተጠርጣሪዎችም በምርመራ ላይ መሆናቸውንም የዓለም ጤና ድርጅት ገልጿል።መጀመሪያ በአውሮፓ መታየቱን ተከትሎ ቀደም ሲል በጣሊያን፣ በስዊድን፣ በስፔን፣ በፖርቱጋል፣ በአሜሪካ፣ በካናዳ እና በዩናይትድ ኪንግደም በሽታው መኖሩ ተረጋግጧል።
የዝንጀሮ ፈንጣጣ በብዛት በመካከለኛው እና በምዕራብ አፍሪካ አካባቢዎች በብዛት የሚከሰት ነው።

የእንግሊዝ ብሔራዊ የጤና አገልግሎት እንደገለጸው፣ ይህ ያልተለመደ የቫይረስ ኢንፌክሽን አብዛኛውን ጊዜ ቀላል ሲሆን ብዙዎች ላይም በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የሚድን ነው።ቫይረሱ በሰዎች መካከል በቀላሉ የማይሰራጭ ሲሆን በሰፊው ሕዝብ ጤና ላይ የሚያስከትለው ስጋት በጣም ዝቅተኛ ነው ተብሏል።

ለዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ የተለየ ክትባት የለም። ከመደበኛው ፈንጣጣ ጋር ተመሳሳይ በመሆናቸው የፈንጣጣ ክትባት 85 በመቶ የመከላከል አቅም ይሰጣል።የዓለም ጤና ድርጅት አርብ ዕለት በሰጠው መግለጫ "በቅርብ ጊዜ በ11 አገሮች የተመዘገበው ወረርሽኞች ተላላፊ ባልሆኑ አገሮች ውስጥ መከሰቱ ያተለመደ ነው" ብሏል።

"ተጎጂዎችን ለማግኘት፣ ለመደገፍና የበሽታ ክትትልን ለማስፋፋት ከተጎዱት አገራት እና ከሌሎች ጋር እየሠራሁ ነው" ብሏል።በተጨማሪም ድርጅቱ በበሽታው ምክንያት ማግለል እንዳይኖር አስጠንቅቋል።