Get Mystery Box with random crypto!

በአባቷ የቀብር ስነስርዓት ላይ ለጓደኛዉ የታገቢኛለሽ ወይ? ጥያቄ ያቀረበዉ ግለሰብ አነጋጋሪ ሆኗል | Esat tv

በአባቷ የቀብር ስነስርዓት ላይ ለጓደኛዉ የታገቢኛለሽ ወይ? ጥያቄ ያቀረበዉ ግለሰብ አነጋጋሪ ሆኗል !!

የጉድ ሀገር እንዲሉ በአባቷ ቀብር ላይ ለጓደኛዉ ቀለበት ያሰረዉ ደቡብአፍሪካዊ ከሀገሩ እንዲሁም ከሌሎች የዓለማችን ክፍል ነዋሪዎች ዘንድ ከባድ ትችትን እያስተናገደ ይገኛል፡፡

በአባቷ የቀብር ስነስርዓት ላይ ተንበርክኮ ታገቢኛለሽ ብሎ ሲጠይቃት የሚያሳየዉን አስደንጋጭ ቪድዮ የቀብር ስነስርዓቱ ላይ የተገኘች አንዲት ሴት ቀርጻ ወዲያዉ በቲክቶክ የማህበራዊ መገናኛ ላይ ከለቀቀች በኋላ፤ እጅግ በርካታ ሰዎች እንደተቀባበሉት እና ብዙ ተጠቃሚዎችም ትችቶችን እንደሰነዘሩበት ኦዲቲ ሴንትራል ነዉ የዘገበዉ፡፡

ቪድዮዉ ላይ የሚታየዉ የአባቷ አስከሬን ሳጥን ፊት ቁጭ ብላ በማልቀስ ላይ የምትገኘዉ ጓደኛዉን ተንበርክኮ የታገቢኛለሽ ጥያቄ ሲያቀርብ ነዉ። ማይክራፎን በመጠቀምም ንግግር ያደርግ እና የሌሎች ሹክሹክታ እና ተቃዉሞ አንዳች ሳያግደዉ ቀለበት አዉጥቶ በጣቷ ላይ ሲያጠልቅ ያሳያል፡፡

ጓደኛዉ በፍጹም ድንጋጤ ዉስጥ ሆና የምትታይ ሲሆን ምንም ዓይነት ምላሽ ባለመስጠቷም የጋብቻ ጥያቄዉን ትቀበል አትቀበል ምንም ግልጽ የሆነ ነገር የለም፡፡ በቦታዉ እየሆነ ያለዉን ነገር በስርዓቱ ለማጣጣም በትክክለኛዉ የስሜት ሁኔታ ላይ እንዳልነበረችም በግልጽ ይታይ ነበር፡፡

Via oddity central

https://t.me/esat_television_official
https://t.me/esat_television_official