Get Mystery Box with random crypto!

«ሰሊም<=> ሚድያ»

የቴሌግራም ቻናል አርማ eross_eross — «ሰሊም<=> ሚድያ»
የቴሌግራም ቻናል አርማ eross_eross — «ሰሊም<=> ሚድያ»
የሰርጥ አድራሻ: @eross_eross
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.16K
የሰርጥ መግለጫ

☞ ወርቃማ ንግግሮችና ምክሮች፣ አነቃቂ ትምህርቶች የሚቀርቡበት ቻናል ነው ‼️
👇👇👇ሼር
@eross_eross

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-15 18:52:59 በአላህ ፍቃድ በቅርቡ በነዚህ እርዕሶች እንመካከራለን


የወሲብ ፎቶዎችና ቪዲዮዎች በማየት ሱስ ለተጠመዱ

ጠቃሚና ዘላቂ ጓደኛ እንዴት ማግኘት እንችላለን

እራስን ከምቀኝነትና ጥላቻ እንዴት መውጣትና መጠበቅ እንችላለን

በአላህ ፍቃድ በቅርቡ ይጠብቁን
ለሌሎች ተደራሽ እንዲሆን
ሼር ሼር ሼር
Join us on

@Eross_eross
442 viewsአቡ ጁለይቢብ, 15:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 13:23:09 ሃሠኑል በስሪይ እንዲህ ይላሉ፦
" አንድ ባሪያ ላይ ወንጀሎች ከበዙና እኚህ ወንጀሎቹን የሚያብሱ መልካም ስራዎችን ካልሠራ፤ ወንጀሎቹን ማበሻ ይሆነው ዘንድ ሃሳብ(ትካዜዎች) ይጣሉበታል።"
[ሱነኑ ሷሊሂን 2957]

@tewihd
455 viewsአቡ ጁለይቢብ, 10:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 13:14:42 ሸይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያህ እንዲህ ይላል፦
"አንድ ሰው ከማይፈልገው ጋር ትዳርን እንዲመሰርት ወላጆች ማስገደድ አይችሉም፡፡ አልፈልግም ካለ ትዳሩ ታሰረ(አጨ) አይባልም፡፡ አንድ ሰው ነፍሱ ደስ ያለችውን መርጦ የመብላት ችሎታና መብት እያለው ማንም ተነስቶ የማይፈልገውን ምግብ ብላ ብሎ ማስገደድ እንደማይችለው ሁሉ ትዳር ላይ ደግሞ ከዚህ በበለጠ መልኩ ይሆናል፡፡ ለምን ቢባል አንድ ሠው መጥፎ እንዲበላ ቢገደድ ወይም ቢመገብ ያ መጥፎ ጣዕም ለተወሰነ ጊዜ ነው የሚቆየው፡፡ መጥፎ ትዳር(ኑሮ) ከሆነ ግን ከሁለቱም ጥንዶች ጋር ብዙን ጊዜ ይቆያል፡፡ ሰውየውም ትልቅ እንግልት ውስጥ ይገባል፡፡ ልለየው ቢል እንኳ መለየቱ አዳጋች ይሆናል፡፡"
[መጅሙዕ አል ፈታዋ 32/30].
@eross_eross
597 viewsአቡ ጁለይቢብ, 10:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 14:01:34 ፈገግታ ለስው ልጅ አስፈላጊ ከሆኑ ነገሮች አንዱ ነው ፈገግታችንን ስንደብቅ ውስጣችን ያለውን ጭነቅት እያሰብን ወደማይፈለግበት ትካዜ ውስጥ እንድንገባ ያደርገናል ሀሳባችንን ለአሏህ እንስጠው ጭንቀታችንን በዚክር እናስወግደው ለነብሳችን እንዘንላት ነገሮችን መርሳት ባንችልም በነግሮች ደጋግመን ላልመጎዳት እንሞክር ፈግግ እንበል በፈገግታ ራሳችንን እናስውብ።
585 viewsአቡ ጁለይቢብ, 11:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 03:36:19   የህይወት እይታ
ባህሪህን እወቅ

በመንገድ ላይ ሲጓዝ የነበረ አንድ ሰውዬ መርዛማ የሆነ እባብ በእሳት ሲቃጠል ተመለከተና ከእሳቱ ውስጥ ሊያወጣው ወሰነ። ከእሳቱ ውስጥ ሊያወጣ ሲያነሳው እባቡ እጁ ላይ ነደፈው። ሰውዬው በድንጋጤ እባቡን ወረወረው እባቡም ተመልሶ እሳቱ ውስጥ ወደቀ።

ሰውዬውም በድጋሚ ሁለት እንጨቶችን ተጠቅሞ ከእሳቱ አወጣው። እናም የእባቡ ሕይወት ተረፈ።
ቆሞ ድርጊቱን ይመለከት የነበረ አንድ ሰው ወደ ሰውየው ቀርቦ

"ይህ እባብ በመርዙ ነድፎህ ሳለ ድጋሚ ልታድነው የምትሞከረው ለምንድነው?" ብሎ ጠየቀው።

ሰውየውም "የእባቡ ባህሪ መንደፍ ነው የእኔ ደሞ ማትረፍ ነው። ሁለታችንም ያለንን ነው ያንፀባረቅነው። ለሱ ክፉ ባህሪ ብዬ የኔን መልካም ባህሪ መለወጥ የለብኝም" ብሎ መለሰ።

ክፉ ነገር በክፉ ሊመለስ አይገባም። መጥፎ ሰዎች በዙሪያህ ቢኖሩም፣ የቱንም ያህል ክፋት ቢሰሩብህ አንተ የራስህን መልካም ብህሪ አንፀባርቅ እንጂ በነሱ ውስጥ አትዋት።አንድ ቀን ከዚህ ስራቸው ታድናቸዋለህ።

ሀል ጊዜም እራስህን ሁን!!!!

የእውነት የሰውኛ ባህሪያችን ምንድነው?እየሆንን ያለውስ.?
#share_channel
@eross_eross
591 viewsአቡ ጁለይቢብ, 00:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 03:26:43 ዱንያ ላይ ስትኖር ሁሉን ነገር ማስተናገድ ግድ ይለሀል ደስታውም ሀዘኑም ስለዚህ በደስታ ጊዜ በጣም ከፍተኛ ስሜት ውስጥ አትግባ ምክኒያቱም የተደሰትክበት ነገር በቅፅበት ልታጣው ትችላለህ ደስታህን ለከት ይኑረው በሀዘን ጊዜ በጣም አትዘን አትናደድም በማዘንህ ምክኒያት ብዙ ነገር ታጣለህ ስለዚህ ሁለቱም ሲመጡብህ አላህን አመስግን የተሻለ ነገር ታገኛለህ፡፡

አልሃምዱሊላሂ
#Share_join
@eross_eross
487 viewsአቡ ጁለይቢብ, 00:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 03:23:54 ↬ ከገደል ጫፍ ላይ የወደቀ ሰው መሬት ላይ እስኪያርፍ ድረስ ምንም የህመም ስሜት አይሰማውም ።

↬ ዳገትም የሚወጣ ሰው መሀል ላይ አይሰማውም ሲጨርስ አንጂ ።

↬ መጥፎ ስራ ብዙ ጊዜ ሲሰሩት ይጥማል ኋላ ግን ይከነክናል ።

↬ አብዛኛውን ጊዜ መልካም ስራን ሲሰሩት ይከብዳል ኋላ ግን ይጣፍጣል ።
#Share
@eross_eross
412 viewsአቡ ጁለይቢብ, 00:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 17:35:33 በህይወትህ ውስጥ ሁሉንም ልትሆን ትችላለህ ጠቃሚው ነገር ግን መልካምና ደግ ሰው መሆን ነው!
533 viewsNew life chapiter one, 14:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 17:31:02 አንድት ሴት ከመገላለጥ ትጠንቀቅ
አንቺ ውዷ እህቴ ሆይ ዛሬ ላይ ብዙሃን ሴቶች እያደረጉት ያለው ድርጊት ከትልልቅና አፀያፊ ወንጀል ተደርጎ ይወሰዳል፦ ከቤታቸው ሌሎችን አማላይና ለራሳቸው የማለሉ ሆነው ተቀባብተው ተውበው መውጣታቸው ትልቅ የፊትና በር ከፋቾች ሆነዋል።

ያም ጌጥን ውበትን መገላለጥ
ሸቶ መቀባባት የተላያዩ ፈታኝ የሰውነት ክፍሎችን ማሳየት ወንዶችን መቀላቀል ይህ አስቀያሚ ድርጊት ይፈፅማሉ በራሳቸውም ላይ የአሏህን ቁጣ ያረጋግጣሉ።


قال الله تعالى: - (وَمَا ظَلَمْنَاهُمْ وَلَٰكِن ظَلَمُوا أَنفُسَهُمْ ٍۖ )
هود (101)

አሏህ እንድህ አለ፦ 【እኛ አልበደልናቸውም ነገር ግን እነሱ እራሳቸውን በደሉ።】
ሱረቱል ሁድ [101]

والله عز وجل يقول : " وَقَرْنَ فِي بُيُوتِكُنَّ وَلَا تَبَرَّجْنَ تَبَرُّجَ الْجَاهِلِيَّةِ الْأُولَى " [سورة الأحزاب، الآية : 33].

አሏህ እንድህ አለ፦ ((ቤታችሁ ተቀመጡ የቀደምት የመሀይማንን አገላለጥ አትገላለጡ))።
ሱረቱል አህዛብ [33]

ويقول سبحانه : " وَلَا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ " [سورة النور، الآية : 24].

ሉኡሉ ጌታችን ይላል፦ ((ጌጣቸውን ግልፅ አያድርጉ))
ሱረቱ ኑር [24]

وقال النبي صلى الله عليه وسلم «صنفان من أهل النار لم أرهما : قوم معهم سياط كأذناب البقر يضربون بها الناس، ونساء كاسيات عاريات مائلات مميلات رءوسهن كأسنمة البخت المائلة، لا يدخلن الجنة ولا يجدن ريحها، وإن ريحها ليوجد من مسيرة كذا وكذا»
رواه مسلم وغيره

የአሏህ ነብይ እንድህ አሉ፦ «ሁለት አይነት ሰዎች የእሳት ናቸው አሁን አላያቸውም ፤ ሰዎች ናቸው ከነሱ ጋር ሰዎችን የሚደበድቡበት የከብት ጅራት መሰል አለንጋ ያላቸው ፣ እናም ለብሰው ያለበሱ ለራሳቸው የሚማልሉ ሌሎችንም የሚያማልሉ ሴቶች ናቸው ፀጉራቸው እንደተዘነበለ ግመል ሻኛ ነው ጀነት አይገቡም ሽታዋንም አያገኙም…።»
ሙስሊምና ሌሎችም ዘግበውታል

አንድት ሙስሊም የሆነች ሴት ጠባብ ዘርዛራ የሰውነት ቅርፅን ከሚያሳይ የሰውነትን ውበት ከሚያጋልጥ ልብስ መራቅ ይኖርባታል።

እንድሁም ከመሰባበር ድምፅን ከማቅለስለስና በአካሄድ ሰዎችን ከመፈተን ልትጠነቀቅ ይገባታል።

ከራሷ ላይ ሂጃብ ማንሳት ከደረት ከክንድ ከባት መሰል የሰውነት ክፍሎችን መግለጥን ትጠንቀቅ።
ጋጠ ወጥ የሆኑ ሴቶች የሚለብሱትን አይነት አጫጭር ልብስ ከመልበስ ልትጠነቀቅ ይገባታል።
ይህ አሏህ እርም ክልክል ካደረገው ነገር ስለሆነና እንድሁም ለአደገኛ ፊትና ስለሚያጋልጥ።

قال العلامة ابن باز رحمه الله :
فالواجب الحذر من ذلك، والمرأة عورة وخطرها عظيم على نفسها وعلى غيرها، فالواجب عليها أن تكون بعيدة عن أسباب الفتنة بالتحجب ولبس الجلباب الذي يسترها ...

ኢማም ኢብኑ ባዝ አሏህ ይዘንላቸው እንድህ ነበር ያሉት፦
«ግዴታው ከዚህ ልትጠነቀቅ ነው ፣ ሴት ሰውነቷ በሙሉ ሃፍረተ ገላ ነው ፣ አደጋዋም በራሷም ሆነ በሌሎች ላይ የከፋ ነው ፣ ግደታው እሷነቷን ልሸፍን የሚችለውን ጅልባብ በመልበስ ከፊትና ምክናየቶች የራቀች ልትሆን ነው…።»

ሴት ሰውነቷ በሙሉ ሊገለጥ የማይገባው ሃፍረተ ገላ ነው ወደ ሱቅ ስትወጣ ሸይጧን ይክባታል።
ለዚህም ልትሸፈንና ሂጃቧን አጥብቃ ልትይዝ ይገባታል ይህ የሰላም ምክናየት ስለሆነ።

والله يقول سبحانه في كتابه العظيم: (وَإِذَا سَأَلْتُمُوهُنَّ مَتَاعًا فَاسْأَلُوهُنَّ مِنْ وَرَاءِ حِجَابٍ ذَلِكُمْ أَطْهَرُ لِقُلُوبِكُمْ وَقُلُوبِهِنَّ )[الأحزاب:53]،

አሏህ በተከበረው ቃሉ እንድህ አለ፦ 【እቃን ስትጠይቁ ከመጋረጃ ጀርባ ሆናችሁ ጠይቁ ይህም ለናንተም ሆነ ለነሱ ልብ ንፅህና የተሻለ ነው።】
ሱረቱል አህዛብ [53]

እህቴ በመሸፈንሽ የሌሎችንም የራስሽንም ልብ ከተለያዩ በሽታዎች ትጠብቂያለሽ።

እህቴ አሏህ ይዘንልሽ እነዚያ ምርጥ ቆነጃጅት የነብዩ ምርጥ የነብዩ ባልደረቦች የነበሩት ጀግና ሴቶችን ሞደል አድርጊ ፤ እነዚህ ዛሬ ላይ ክብራቸውን ማንነታቸውን አርግፈው የጣሉ ክብራቸው መደፈሩ የማያሳስባቸው የዝንብ መዋያ የሆኑ ሴቶች እስታይል እንዳይሸውድሽ ስልጣኔ መስሎች የስልጣነውን ማማ የስልጣነውን ሰገነት አውልቀሽ አልሰለጠነው አውሬነት እንዳትመለሽ።

https://telegram.me/tewihd
525 viewsNew life chapiter one, 14:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 17:19:15 ራስን በራስ ማርካት (#ሴጋ) የሚበላው ነገር እንዴት ይታያል በሸሪዓችን

ማስተርቤሽን (ሴጋ) ወይም ራስን በራስ ማርካት በሸሪዓችን #የተከለከለና የተወገዘ ተግባር ለመሆኑ #በርካታ ኡለሞች በየአጋጣሚው ይናገራሉ። ለዚህ አቋማቸውም ይህን የአላህ ንግግር #እንደመረጃ ይጠቀማሉ ፣

" እነዚያ (ሙእሚኖች) ብልቶቻቸውን #ጠባቂዎች የሆኑት ናቸው ፣ በሚስቶቻቸው ወይም በባሪያዎቻቸው ላይ #ሲቀር እነሱ የማይወቀሱ ናቸው። ከዚህ ውጭ #ሌላን የፈለጉ ሰዎች እነዚያ ወሰን #አላፊዎች ናቸው።"
ሱረቱል ሙእሚኒን ፣ 5 - 7
ይህ የቁርአን አንቀፅ ከሚስቶች #ውጭ ባለ ነገር ስሜትን #መወጣትና ራስን ማርካት የሙእሚኖች ባህሪ #እንዳልሆነና ይህንን የሚያደርግ ደግሞ #የሚወቀስ መሆኑን ያመለክተናል። ከዚህም በተጨማሪም #በጤንነት እና #በሰውነት አካል ላይ የጎንዬሽ #ጉዳት እንዳለው የዘርፉ ባለሙያ የሆኑ #ዶክተሮችም ይናገራሉ።
ምንጭ :— ኢብኑ ተይሚያ ፣ መጅሙዑል ፈታዊ ፣ 34/229 ፣ ሸይኹል አልባኒ ፣ ተማሙል ሚንናህ ፣ 420 ፣ ሸይኽ ሙሀመድ አማን አሽሸንቂጢይ ፣ አድወኡል በያን ፣ 5/525
telegram
https://telegram.me/tewihd
440 viewsNew life chapiter one, 14:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ