ራስን በራስ ማርካት (#ሴጋ) የሚበላው ነገር እንዴት ይታያል በሸሪዓችን ማስተርቤሽን (ሴጋ) ወይም ራስን በራስ ማርካት በሸሪዓችን #የተከለከለና የተወገዘ ተግባር ለመሆኑ #በርካታ ኡለሞች በየአጋጣሚው ይናገራሉ። ለዚህ አቋማቸውም ይህን የአላህ ንግግር #እንደመረጃ ይጠቀማሉ ፣ " እነዚያ (ሙእሚኖች) ብልቶቻቸውን #ጠባቂዎች የሆኑት ናቸው ፣ በሚስቶቻቸው ወይም በባሪያዎቻቸው ላይ #ሲቀር እነሱ የማይወቀሱ ናቸው። ከዚህ ውጭ #ሌላን የፈለጉ ሰዎች እነዚያ ወሰን #አላፊዎች ናቸው።" ሱረቱል ሙእሚኒን ፣ 5 - 7 ይህ የቁርአን አንቀፅ ከሚስቶች #ውጭ ባለ ነገር ስሜትን #መወጣትና ራስን ማርካት የሙእሚኖች ባህሪ #እንዳልሆነና ይህንን የሚያደርግ ደግሞ #የሚወቀስ መሆኑን ያመለክተናል። ከዚህም በተጨማሪም #በጤንነት እና #በሰውነት አካል ላይ የጎንዬሽ #ጉዳት እንዳለው የዘርፉ ባለሙያ የሆኑ #ዶክተሮችም ይናገራሉ። ምንጭ :— ኢብኑ ተይሚያ ፣ መጅሙዑል ፈታዊ ፣ 34/229 ፣ ሸይኹል አልባኒ ፣ ተማሙል ሚንናህ ፣ 420 ፣ ሸይኽ ሙሀመድ አማን አሽሸንቂጢይ ፣ አድወኡል በያን ፣ 5/525 telegram https://telegram.me/tewihd 440 viewsNew life chapiter one, 14:19