Get Mystery Box with random crypto!

  የህይወት እይታ ባህሪህን እወቅ በመንገድ ላይ ሲጓዝ የነበረ አንድ ሰውዬ መርዛማ የሆነ እባብ | «ሰሊም<=> ሚድያ»

  የህይወት እይታ
ባህሪህን እወቅ

በመንገድ ላይ ሲጓዝ የነበረ አንድ ሰውዬ መርዛማ የሆነ እባብ በእሳት ሲቃጠል ተመለከተና ከእሳቱ ውስጥ ሊያወጣው ወሰነ። ከእሳቱ ውስጥ ሊያወጣ ሲያነሳው እባቡ እጁ ላይ ነደፈው። ሰውዬው በድንጋጤ እባቡን ወረወረው እባቡም ተመልሶ እሳቱ ውስጥ ወደቀ።

ሰውዬውም በድጋሚ ሁለት እንጨቶችን ተጠቅሞ ከእሳቱ አወጣው። እናም የእባቡ ሕይወት ተረፈ።
ቆሞ ድርጊቱን ይመለከት የነበረ አንድ ሰው ወደ ሰውየው ቀርቦ

"ይህ እባብ በመርዙ ነድፎህ ሳለ ድጋሚ ልታድነው የምትሞከረው ለምንድነው?" ብሎ ጠየቀው።

ሰውየውም "የእባቡ ባህሪ መንደፍ ነው የእኔ ደሞ ማትረፍ ነው። ሁለታችንም ያለንን ነው ያንፀባረቅነው። ለሱ ክፉ ባህሪ ብዬ የኔን መልካም ባህሪ መለወጥ የለብኝም" ብሎ መለሰ።

ክፉ ነገር በክፉ ሊመለስ አይገባም። መጥፎ ሰዎች በዙሪያህ ቢኖሩም፣ የቱንም ያህል ክፋት ቢሰሩብህ አንተ የራስህን መልካም ብህሪ አንፀባርቅ እንጂ በነሱ ውስጥ አትዋት።አንድ ቀን ከዚህ ስራቸው ታድናቸዋለህ።

ሀል ጊዜም እራስህን ሁን!!!!

የእውነት የሰውኛ ባህሪያችን ምንድነው?እየሆንን ያለውስ.?
#share_channel
@eross_eross