Get Mystery Box with random crypto!

ሸይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያህ እንዲህ ይላል፦ 'አንድ ሰው ከማይፈልገው ጋር ትዳርን እንዲመሰር | «ሰሊም<=> ሚድያ»

ሸይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያህ እንዲህ ይላል፦
"አንድ ሰው ከማይፈልገው ጋር ትዳርን እንዲመሰርት ወላጆች ማስገደድ አይችሉም፡፡ አልፈልግም ካለ ትዳሩ ታሰረ(አጨ) አይባልም፡፡ አንድ ሰው ነፍሱ ደስ ያለችውን መርጦ የመብላት ችሎታና መብት እያለው ማንም ተነስቶ የማይፈልገውን ምግብ ብላ ብሎ ማስገደድ እንደማይችለው ሁሉ ትዳር ላይ ደግሞ ከዚህ በበለጠ መልኩ ይሆናል፡፡ ለምን ቢባል አንድ ሠው መጥፎ እንዲበላ ቢገደድ ወይም ቢመገብ ያ መጥፎ ጣዕም ለተወሰነ ጊዜ ነው የሚቆየው፡፡ መጥፎ ትዳር(ኑሮ) ከሆነ ግን ከሁለቱም ጥንዶች ጋር ብዙን ጊዜ ይቆያል፡፡ ሰውየውም ትልቅ እንግልት ውስጥ ይገባል፡፡ ልለየው ቢል እንኳ መለየቱ አዳጋች ይሆናል፡፡"
[መጅሙዕ አል ፈታዋ 32/30].
@eross_eross