2022-06-30 10:28:21
አሜሪካዊው ቢሊዬነር ስቲቭ ጆብስ በህይወቱ መጨረሻ ሰዓት ላይ ያስተላለፈው አስደናቂ መልዕክት
ስቲቭ ጆብስ በ56 አመቱ ያረፈ አሜሪካዊ ቢሊዬነር ሲሆን ህይወቱ ያለፈው በካንሰር በሽታ ነው::
…
በንግዱ አለም ውስጥ የመጨረሻ ከፍታ ጫፍ የሚባለው ቦታ ደርሻለሁ፣ ይሁን እንጂ ከዚህ ሁሉ ሀብት ደስታን ማግኘት አልቻልኩም። በልፋቴ ካከማቸሁት ሃብት ያገኘሁት ደስታ እዚህ ግባ የማይባል ነው፣
,
አሁን፣በህይወቴ የመጨረሻው ሰዓት አካባቢ፣አልጋ ላይ ሆኜ ያሳለፍኩትን ነገር ሁሉ ወደሗላ ሳስበው ፣ እኮራበት የነበረው ሀብቴና ዝናዬ ከንቱ እና ትርጉም አልባ እንደሆነ ተረድቻለሁ፥፥
,
,,አንድን ሰው መኪና እንዲነዳልህ ወይም ሰርቶ ገንዘብ እንዲያስገባልህ ልትቀጥረው ትችላለህ፣ እየተሰቃየህበት ያለውን ህመም እንዲሸከምልህ ግን ልትቀጥረው አትችልም፥
,
,, ምድራዊ የሆኑ ቁሳቁሶች ሁሉ ሊጠፉ ፣ዳግም ሊገኙም ይችላሉ፥ አንድ ጊዜ ካመለጠ ደግመህ ልታገኘው የማትችለው አንድ ነገር ግን አለ… እርሱም #ህይወትህ ነው፥
,
አንድ ሰው የቀዶ ጥገና ወደሚደረግለት ክፍል ሲገባ አንብቦ ያልጨረሰው አንድ መጽሃፍ ትዝ ቢለው የመጽሐፉ ርዕስ "ጤናማ ህይወት የመኖር ሚስጥር" የሚል ሊሆን እንደሚችል ጥርጥር የለውም፣
,
; በየትኛውም የህይወት ከፍታ ላይ ብንሆን የህይወታችን መጋረጃ የሚዘጋበትን ቅጽበት ፊት ለፊት የምንጋፈጥበት አንድ ቀን መምጣቱ አይቀርም፣
,
, ለቤተሰብህ፣ለትዳር አጋርህ እና ለጏደኞችህ የፍቅርን ውርስ አስቀምጥላቸው፣
,
, ራስህን ተንከባከብ ፣ ከሌሎች ጋር መልካም ግንኙነት ይኑርህ
,
, እያደግን ስንሄድና የህይወት ትርጉሙ ሲገባን ውድ ሰዓትም አሰርን ርካሽ ሰዓት ፣ ሁለቱም የሚነግሩን ጊዜ እኩል መሆኑ ይገባናል
,
, በኪሳችን ውድ ቦርሳም ያዝን ርካሽ ቦርሳ ፣በውስጡ የሚኖረውን የገንዘብ መጠን አይቀይረውም ፣
,
, የኣንድ ሚሊዮን ብር መኪናም ነዳን የሶስት መቶ ሺህ ብር መኪና ፣የመንገዱ ርዝመት አይቀየርም፣ አቅጣጫውም ያው አንድ ነው፥፥የምንደርሰውም ያው እዚያው ቦታ ነው ፣
,
, ውድ መጠጥም ጠጣን ርካሽ መጠጥ፣ ስካሩና አድሮ የሚያመጣው ራስ ምታት ለውጥ የለውም፣
,
, ሰፊ ግቢ ውስጥ ኖርንም ጠባብ ቤት፣ ብቸኝነቱ ያው እኩል ነው፣
,
…የውስጥ ደስታ በቁሳቁስ እንደማይገኝ ያን ጊዜ ይገባሃል
,
,አውሮፕላን ላይ የክብር ቦታም ተቀመጥክ ወይም ተራ ቦታ ፣አውሮፕላኑ ከተከሰከሰ እኩል ቁልቁል ትወርዳለህ፣
,
እውነተኛው ደስታ የሚገኘው ከቤተሰብህ፣ከጓደኞችህ፣ ከዘመዶችህ ጋር በሚኖርህ ውብ ጊዜኣት ብቻ ነው፥፥
ከእነርሱ ጋር በምታሳልፈው ጊዜ ፣በምትጫወተው ጨዋታ፣ በምትዘምረው መዝሙር፣ በምትስቀው ሳቅ እውነተኛ ደስታን ታገኛለህ ፣
,
5 ሊካዱ የማይችሉ የህይወት እውነታዎች አሉ …
,; ልጆችህ ሀብታም እንዲሆኑ አታስተምራቸው፥፥ ይልቅ እንዴት ደስተኛ መሆን እንደሚችሉ አስተምራቸው፥፥ ሲያድጉ የነገሮች ዋጋ ሳይሆን ጥቅማቸው ይገባቸዋል፣
,
; ምግብህን እንደ መድሃኒት ውሰድ ካልሆነ መድሃኒት እንደምግብ ትወስዳልህ ፣
,
; የሚወድህ ሰው በቀላሉ አይለይህም፣ ከኣንተ ለመለየት 99 ምክንያት ቢኖረው እንኳ መለየት በማይችልባት አንዲት ነገር ላይ ፀንቶ ይቆማል፣
,
;"ሰው ሆኖ በመፈጠር"ና "ሰው በመሆን" መካከል ትልቅ ልዩነት አለ፥፥ ይህ የሚገባቸው ጥቂት ሰዎች ናቸው፥
,
;ስትወለድ ውድ ነበርክ፣ ስትሞትም ውድ ትሆናለህ፣ በመካከል ያለውን ማስተካከል ያንተ ፋንታ ነው፣
,
;በፍጥነት ለመሄድ ከፈለክ ብቻህን ሂድ፣ሩቅ ለመድረስ ከፈለግህ ግን ከሌሎች ጋር አብረህ ተጓዝ ፣
,
;በዓለም ላይ ያሉ ስድስቱ ፈዋሽ ነገሮች የሚከተሉት ናቸው…
የፀሃይ ብርሃን
እረፍት
ስፖርት
ጥሩ ምግብ
በራስ መተማመን እና
ጓደኛ
እነዚህን አጥብቀህ ያዝ፥፥ ደስተኛ ህይወትን አጣጥም!!
https://t.me/Emmausmengdgnch
https://t.me/Emmausmengdgnch
87 views🇩aኒ Revival , edited 07:28