Get Mystery Box with random crypto!

ልቤ አንተን ይላል መንፈሴም ወዳንተ ይገሰግሳል ጉጉቴ አንተን ማክበር ነው ፍላጎቴ ክብርህን | የኤማሁስ መንገደኞች........ channel )

ልቤ አንተን ይላል
መንፈሴም ወዳንተ ይገሰግሳል
ጉጉቴ አንተን ማክበር ነው
ፍላጎቴ ክብርህን ማየት ነው

የእኔ ደስታ አንተን ማስደሰት ነው
ዓላማዬ የአንተ ዓላማ ነው
የእኔ ደስታ ደስ ሲልህ ማየት ነው
ዓላማዬ የአንተ ዓላማ ነው

ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ (2x)

ከምትወደው ጋራ እስማማለሁ
የምትጠላው ለኔ ጠላቴ ነው
በመታዘዝ ፍቅሬን እገልጻለሁ
ዝቅ ማለቴ አንተን ከፍ ላደርግ ነው

መኖር ትርጉም ሚስጥሩ አንተ ነህ
እወዳለሁ ዛሬም ልገዛልህ (2x)

ዋላ ወደውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ
ነፍሴ አንተን ተጠማች
ነፍሴ አንተን ተጠማች (2x)

ኢየሱስ…

እንደልብህ ሆኜ ልኑርልህ
ልቤን ትቼ ያየኸውን ልይልህ
መንፈስን ከኔ አትውሰደው
አጥፍ ልስገድ ሁሌም ላገልግለው

ከውሃ ውስጥ እንደወጣ ዓሣ
መኖር አልችልም ተለይቼ ጌታ (2x)

ዋላ ወደውኃ ምንጭ…

ኢየሱስ…
https://t.me/Emmausmengdgnch
https://t.me/Emmausmengdgnch