Get Mystery Box with random crypto!

የኤማሁስ መንገደኞች........ channel )

የቴሌግራም ቻናል አርማ emmausmengdgnch — የኤማሁስ መንገደኞች........ channel )
የቴሌግራም ቻናል አርማ emmausmengdgnch — የኤማሁስ መንገደኞች........ channel )
የሰርጥ አድራሻ: @emmausmengdgnch
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 316

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-05-19 19:03:41 https://t.me/FreeEearnMoneyPay_Bot?start=r04506632904
ይህን ለ5 ሰው በመላክ  የ500  ብር ተሸላሚ ይሁኑ
ብዙዎች እየተሸለሙበት ነው እርሶም ይሞክሩ ይሸለሙ ጥቅት ቀን ብቻ የቀረው
42 views🇩aኒ Revival , 16:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-14 14:44:31 https://t.me/FreeEearnMoneyPay_Bot?start=r04506632904
ይህን ሊንክ በመጫንና ለጓደኛው ሼር በማድረግ እንድትሸለሙ ልከን ብዙዎች fake መስሎአችሁ ሽልማቱ እንዳያመልጣችሁ ለተወሰነ ጊዜ ብቻ የሚቆይ ነው በመጀመሪያ ሊንኩን ስትጫኑት የ1000 ብር ተሸላሚ ይሆናሉ ከዚያ ለጓደኛ ሼር ስታደርጉት በአንድ ሰው 50 ብር ይደርሳችዋልይህ ማለት ሰውን በጋበዛችሁ መጠን ብሩ ይደርሳችዋል ማለት ነው ሰለዚህ አሁኑኑ ሊንኩን ከላይ ያለውን ሊነሰኩን በመጫንና ለጓደኛው ሼር በማድረግ ይሸለሙ
https://t.me/FreeEearnMoneyPay_Bot?start=r04506632904
300 views🇩aኒ Revival , edited  11:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 18:29:33 https://t.me/FreeEearnMoneyPay_Bot?start=r04506632904
ይህን ለ5 ሰው በመላክ የ500 ብር ተሸላሚ ይሁኑ
686 views🇩aኒ Revival , 15:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 11:29:43 "ጽድቅ” ማለት #በእግዚአብሔር_ሚዛን የሆነ ትክክለኛ
ኑሮ ማለት ነው፨ “#ጻድቅ” የሚባለውም እግዚአብሔር “#ትክክል_ነው” በሚለው መንገድ ኑሮውንና ሕይወቱን የሚመራ ነው፨ እግዚአብሔር በቀደመው ዘመን እነ ኢዮብን "ጻድቅ" ያለበትንና ኋላም በክርስቶስ በገለጠው የራሱ ጽድቅ መካከል ሰፊ ልዩነት እንዳለ ማወቁ በእጅጉ አስፈላጊ ነው፨ እግዚአብሔር በሙሴ በኩል ከሰጠው ሕግ በፊት ይኖሩ የነበሩት እነኢዮብ፣ ኖህና አብርሃምን የመሳሰሉ አባቶች "ጻድቃን" ተብለው የተጠሩት፣ እነርሱ ይኖሩበት በነበረው ዘመን በኖሩት ኑሮ ልክና መጠን ነው፨ ያ ማለት ግን ኑሮአቸው በእግዚአብሔር ጽድቅ ልክና መጠን ነበር ማለት አይደለም፨ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ጽድቅ የተገለጠው በክርስቶስ ስለሆነ ነው፨

“አሁን ግን በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦአል። እርሱም፥ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው…” ሮሜ.3፥21-22

ሕግ የተሰጣቸውን እስራኤላውያንንም ስንመለከት በእነርሱ እንዲገለጥ የተፈለገው ጽድቅ ሕጉ በሚጠይቀው መጠንና ልክ ብቻ ነበር። ይህም ቢሆን ኋላ በክርስቶስ ከተገለጠው የእግዚአብሔር ጽድቅ ጋር እጅግ ሰፊ የሆነ ልዩነት አለው፨ ለምሳሌ፡- ሕጉ "አታመንዝር" ሲል፡- ከአንዲቷ ሚስትህ ውጪ ከሌላ ሴት ጋር አትተኛ ማለቱ ነው። ነገር ግን በዚሁ አታመንዝር በሚለው ትዕዛዝ ላይ በክርስቶስ የተገለጠው የእግዚአብሔር ጽድቅ "ወደሴት ያየ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርሷ ጋር አመንዝሮአል" ይላል፨ በሕጉ የተገለጠው ትክክለኛ ኑሮ የሚወዱንን መውደድ፣ የሚጠሉንን መጥላት ነው፨ ነገር ግን በክርስቶስ የተገለጠው የእግዚአብሔር ጽድቅ፣ ጠላቶቻችንን እንድንወድ፣ የሚረግሙንን እንድንመርቅ፣ ለሚጠሉንም መልካም እንድናደርግ፣ ስለሚያሳድዱን እንድንጸልይ... ያስችለናል፨

ስለዚህ በኢዲሱ ኪዳን ስለተገለጠውና በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን ብቻ ስለሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ወይም ትክክለኛ ኑሮ ስናስብ፣ ሰው በራሱ አቅምና ብቃት ፈጽሞ ሊኖረው የማይችል እጅግ የከበረና የላቀ የጽድቅ ሕይወት ነው፨ ይህ "የእግዚአብሔር ጽድቅ" ማንም "የእኔ" ሊለው አይችልም፨ የእያንዳንዱ ሰው ሕይወት በዚህ የጽድቅ ሚዛን ሲለካ ጎደሎ ነው፨ ከሥጋና ከደም ከተወለዱ የሰው ልጆች መካከል ማንም በዚህ ጽድቅ ልክ የኖረ የለም፨ ለዚህም ነው የእግዚአብሔር ቃል
፦"ጻድቅ የለም አንድ ስንኳ" በማለት አስረግጦ የሚነግረን፨ በዚህ በክርስቶስ በተገለጠው የእግዚአብሔር ጽድቅ ሚዛን ላይ ብናስቀምጠው፣ ኢዩብም ጻድቅ አይደለም፣ አብርሃምም ሆነ ኖህ፣ ሙሴም ሆነ ዳዊት.... ተክልዬም ሆኑ አቡዬ ጻድቅ አይደሉም፨
"ጻድቅ የለም - አንድ ስንኳ!!!!!!!!"

ስለዚህ እግዚአብሔር ይሄንን የራሱን ጽድቅ በሰዎች ሕይወት ውስጥ ለማኖርና ለመግለጥ ነው አንድያ ልጁን በሥጋ ወደዚህ ዓለም የላከው፨ በክርስቶስ እምነት የምንካፈለው የእግዚአብሔርን የራሱን ጽድቅ ነው፨ ይህም ጽድቅ በእኛ ሕይወት የሚገለጥበት ሁለት ደረጃዎች አሉት፨ የመጀመሪያው የእግዚአብሔር ጽድቅ በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን በጸጋ ብቻ የሚገኝ
ነጻ ስጦታ እንደሆነ አምነን የምንቀበልበትና የራሳችን
የምናደርግበት ደረጃ ነው፨ ይህንን ደረጃ፦ #Imputed_Righteousness ይሉታል፨ የጽድቅ ሕይወትና ኑሮ ገና በእኛ መገለጥ ሳይጀምር፣ በእግዚአብሔር ዓይንና አቆጣጠር ብቻ "#ጻድቃን" ተብለን የምንጠራበትና የምንቆጠርበት ደረጃ ነው፨ "አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ፣ ጽድቅም ሆኖ ተቆጠረለት" የሚለው ቃል ለዚህ ሕያው እውነት ምስክር ነው፨ የእግዚአብሔር ጽድቅ በሥራ ሳይሆን፣ በእምነት ብቻ የሚገኝ ነው፨

"ሥጋን የለበሰ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት እንዳይመካ ፤ነገር ግን የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ ተብሎ እንደ ተጻፈው ይሆን ዘንድ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው።" 1ቆሮንቶስ 1፥29-31

,#ክርስቶስ_እርሱ_ጽድቃችን_ነው፤ የመጀመሪያው
ነገር ይሄንን አምኖ መቀበልና በክርስቶስ ባለ እምነት ብቻ "#ጻድቅ" ወይም "#ቅዱስ" ተብሎ መጠራት ነው!
እዚህ ላይ "#ጻድቅ_ወይም_ቅዱስ" ተብሎ መጠራትና መሆን የተለያዩ ደረጃዎች ናቸው፨ ከመሆናችን በፊት መጠራታችን ወይም መቆጠራችን ከመቅደሙም በላይ ለመሆናችን መሠረት ነው፨ ይህም ገበሬው የስንዴውን መከር ከማጨዱና ከመሰብሰቡ በፊት አስቀድሞ ቅንጣቱን እንደመዝራቱ የሚቆጠር ነው፨ የጽድቅ ዘር የሆነው ክርስቶስ አስቀድሞ በእኛ ሕይወት ካልተዘራ የጽድቅ ፍሬ የሚባል ነገር የለም፨ የተወደደው ወንድማችን ጳውሎስ፦ ለፊሊጲስዩስ ቅዱሳን በጻፈው መልእክቱ ውስጥ ይህ እውነት ተገልጦአል፦

"ለእግዚአብሔርም ክብርና ምስጋና ከኢየሱስ ክርስቶስ የሚገኝ የጽድቅ ፍሬ ሞልቶባችሁ፥ ለክርስቶስ ቀን ተዘጋጅታችሁ ቅኖችና አለ ነውር እንድትሆኑ የሚሻለውን ነገር ፈትናችሁ ትወዱ ዘንድ፥ ፍቅራችሁ በእውቀትና በማስተዋል ሁሉ ከፊት ይልቅ እያደገ እንዲበዛ ይህን እጸልያለሁ።" ፊሊጺስዮ.1፥9-11

,ስለዚህ በእምነት ከተቀበልነው የጽድቅ ዘር ከክርስቶስ የተነሳ "ጻድቃንና ቅዱሳን" ተብለን መጠራታችን የመጀመሪያው ደረጃ ሲሆን፣ ይህ በእምነት የተቀበልነው የጽድቅ ዘር፣ የጽድቅ ፍሬ የሚሆንበት፣ ወይም በሕይወት አካሄዳችን የሚገለጥበት ደረጃ ደግሞ ሁለተኛው ነውይህንንም #Imparted_Righteousness ይሉታል፨ በእኛ ያለውን ክርስቶስና ሕይወቱን የምንካፈልበትና የምንኖርበት ደረጃ ነው፨ በእምነት "ጻድቃንና ቅዱሳን  ተብለው የተጠሩት ያመኑ  ክርስቲያኖች፣ ጽድቃቸውና ቅድስናቸው የሆነው ክርስቶስ በሕይወት አካሄዳቸው እንዲገለጥ፣ በነፍሳቸው ጥልቀት ውስጥ የተዘራው የጽድቅና የቅድስና ዘር - ክርስቶስ የኑአሮቸው ፍሬ እንዲሆን....  "ቅዱሳን ሁኑ፣ ትቀደሱ ዘንድ ፈልጉ፣ ሰውነታችሁን ቅዱስና ሕያው መስዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ...." እየተባሉ ዕለት - ዕለት ይማራሉ፣ ይመከራሉ፣ ይገሰጻሉ፣ ይበረታታሉ!! ይህም በሚገባ አርሶና ጎልጉሎ መልካሙን ዘር የዘራበትን መሬት እንደሚንከባከበው ገበሬ፣ የቃሉ አገልጋዮች የዕለት ተዕለት ሥራ ነው፨

,እግዚአብሔር በተለይ በወንድማችን ጳውሎስ በኩል በተሰበከው ወንጌል የገለጠው ምሥጢር አንድ ነው፨ እርሱም #የጽድቅ_ዘር_የሆነው_ክርስቶስ_በእኛ ውስጥ መሆኑንና በሕይወት አካሄዳችንም የኑሮአችን ፍሬ ሆኖ የሚገለጠው ክርስቶስ ራሱ መሆኑን ነው፨ የተወደደው ሐዋርያ ይህንን የጽድቅ ዘር በወንጌሉ የዘራባቸውን ቅዱሳን “#እናንተ_የእግዚአብሔር_እርሻ ናችሁ” እያለ፤ ክርስቶስ በእነሱ እስኪሳል ወይም ሕያው ሆኖ እስኪገለጥና የሕይወት አካሄዳቸው ደግሞም የኑሮቸው ፍሬ እስኪሆን ድረስ ዕለት ዕለት እንደ ትጉ ገበሬ አገልግሎቱን ይፈጽም ነበር፨ የተጋድሎውንም ዓላማ "#በክርስቶስ_ፍጹም_የሚሆን_ሰው_ማቅረብ" ብሎታል፨ ይህም የመንፈሳዊው ገበሬ የድካሙ የመጨረሻ ውጤት ወይም #ፍሬው ነው፨
https://t.me/Emmausmengdgnch
https://t.me/Emmausmengdgnch
28 views🇩aኒ Revival , 08:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-16 22:08:53 ስማኝ ልጄ!!
1. ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትውደቅ ማለት አይደለም ወድቀህ መነሳትንም ልመድ ማለት እንጂ!!!!
2. ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም ሌሎችን ለመስማት ጆሮ ስጥ ማለት እንጂ!!!!
3. ሆዳም አትሁን ማለት አትብላ ማለት አይደለም በሰው ሀቅ አትለፍ ማለት እንጂ!!!!
4. አትቆጣ ማለት ስሜት አይኑርህ ማለት አይደለም ከቁጣ ቶሎ ተመለስ ማለት እንጂ!!!!
5. ይቅርታ አድርግ ማለት አልተጎዳህም ማለት አይደለም በሆድህ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ስለሆነ እንጂ!!!!
6. ጠላትህን ውደድ ማለት ጠላት ጥሩ ነው ማለት አይደለም ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር ስለሚያሸንፍ!!!
7. ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ማለት አይደለም ባለህ ነገር ደስ ይበልህ ማለት እንጂ!!!!
8. ስራህን ውደድ ማለት የምትሰራው ስራ ጥሩ ነው ማለት አይደለም ነገ ጥሩ ስራ እንዲኖርህ ዛሬ የምትሰራውን ስራ ውደድ ማለት እንጂ!!!!
9. ወረኛ አትሁን ማለት አታውራ ማለት አይደለም ምንም ስለማታውቀው ነገር አታውራ ማለት እንጂ!!!!
10. ትሞታለህ ማለት አትስራ ማለት አይደለም ምንም ቁም ነገር ስትሰራ አትሙት ማለት እንጂ!!!!
11. ብቸኛ አትሁን ማለት ሮጠህ ትዳር ያዝ ማለት አይደለም ልብህን ግዜህን ያለህን ሁሉ አሳልፈ ለመስጠት ዝግጁ ሁን ማለት እንጂ!!!!
12. እውነተኛ ሁን ማለት ሰዎች ባሉበት ብቻ እውነትተናገር ማለት አይደለም ለራስህም የእውነት ኑሮ ኑር ማለት ማለት እንጂ!!!!
13. አትጣላ ማለት ከሰው ጋር አትኑር ማለት አይደለም ቂም ይዘህ አትቆይ ማለት እንጂ!!!!
14. ኩራተኛ አትሁን ማለት አትዘንጥ ማለት አይደለም ሌሎችን አትናቅ ማለት እንጂ!!!
15. ቆንጆ ነህ ማለት ከሌሎች የተሻልክህ ነህ ማለት አይደለም አምሮብሃል ማለት እንጂ!!!!
16. አዋቂ ሁን ማለት እንደገና ት/ቤት ሂድ ማለት አይደለም ብልህ ሁን ማለት እንጂ!!!!
https://t.me/Emmausmengdgnch
https://t.me/Emmausmengdgnch
https://t.me/Emmausmengdgnch
1.0K views🇩aኒ Revival , 19:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 10:44:10 የተረጋጋ ህይወት እንዲኖርህ መፅሀፍትን አንብብ ብዙ አታውራ ማውራት ሲኖርብህ ግን ዝም አትበል ምክርና አስተያየት ለመቀበል አትፍራ ለተደረገልህ ጥሩ ነገር አመስግን ፤ በቂ እንቅልፍ ተኛ የማታውቀውን ጠይቅ ፤ በየወሩ ካለህ ገቢ ላይ ትኝሽም ቢሆን ቆጥብ ዛሬ መስራት የምትችለውን ዛሬውኑ ስራ።

የሠው ልጅ ሲቸግረው ልብሱን የቤቱን ዕቃ፤ ኩላሊቱንም ሳይቀር ሊሽጥ ይችላል ህሊናውን ከሸጠ ግን በጠና ቸግርታል ማለት ነው።

ዶ/ር ምህረት ደበበ
https://t.me/Emmausmengdgnch
https://t.me/Emmausmengdgnch
639 views🇩aኒ Revival , 07:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-29 14:03:47 ባልፈራ ኖሮ . . .

• “መጀመር የምፈልገው አንድ ዓላማ ነበር” የምትሉት ነገር አለ?

• “ስለማውቀው እውነት በቅንነት ልሞግተው የምፈልገው ሰው ነበር” ብላችሁ ታስባላችሁ?

• “እውነቱን ነግሬ ይቅርታ መጠየቅ ያለብኝ ሰው ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ?

• “ለአንድ ሰው እውነቱ ተናግሬ እርዳታ ማግኘት ያለብኝ የሆነ አጉል ልምምድ እንዳለኝ አውቃለሁ” ብላችሁ ታስባላችሁ?

• “እንደማፈቅራት/ረው ልነግራት/ረው የምፈልገው አንድ ሰው ነበር” ብላችሁ ታስባላችሁ?

እነዚህንና መሰል ትክክለኛ የሆኑ እርምጃዎች ከመውሰዳችሁ በፊት ፍርሃታችሁ እንዲወገድ የምትጠብቁ ከሆነ መቼም እንደማታደርጓቸው ላስታውሳችሁ፡፡ ድፍረት ማለት ፍርሃትን አልፎ መሄድ ማለት ነው እንጂ የፍርሃት አለመኖር ማለት አይደለም፡፡

https://t.me/Emmausmengdgnch
https://t.me/Emmausmengdgnch
294 views🇩aኒ Revival , 11:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-19 11:28:41
#በባህርይ #ለውጥ #ማደግ
አንድ አንጥረኛ የሚታነጥረው ብር ሆኗል የሚትለው መቼ ነው? የሚል ጥያቄ ቀረበለት ፦ እርሱም ምስሌን በውስጡ ስመለከት ብሎ መለስ።
ሕይወትህ በመከራ ውስጥ በሚጠራበት ጊዜ ሰዎች የኢየሱስን ምስል አንተ ውስጥ ይመለከታሉ
የባህርያችን ምስል በትምህርት ሲታይ ቅርጹ ግን በመከራ ይገለጣል
ሴይጣንን በባህሪይ ለውጥ እንጂ በተቃውሞ ብዛት አታሸንፈውም
የትኛውም ፈተና የሚላከው ወደ ባህርያችን ነው
ኃጢአትም ሆነ ጽድቅ የሚገለጠወ በባህርያችን በኩል ነው
ሰለዚህ ለአንድ ክርስትያን የባህርይ ለውጥ ማምጣት የግድ ነው ክርስትና የባህርይ ለውጥ እንጂ መዘመር የመቻልና የመጸለይ ጉዳይ አንደለም
ይህም የባህርይ ለውጥ የአንድ ጀንበር ሳይሆን ሂደታዊ ነው ይህ ደግሞ ጽናትን ይጠይቃል
የጽናት ምስጢሩ ሥቃይህ ጊዜያዊ ዋጋህን ዘላለማዊ መሆኑን ማስታወስ ነው ዕብ 11: 26 2ቆሮ 4:17
ትልቁ ታምር የሽባ መተርተር ሳይሆን የክርስቶስ ባህርይ በእኛ ውስጥ መገለጥ ሲጀምር ነው ያ ነው ወንጌል
https://t.me/Emmausmengdgnch
https://t.me/Emmausmengdgnch
https://t.me/Emmausmengdgnch
43 views🇩aኒ Revival , edited  08:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-17 13:12:39
ከባድ ነው

☞ ካለ መንፈስ ቅዱስ ቀኖች ከባድ ናቸው

☞ ካለ መንፈስ ቅዱስ መፀለይ ከባድ ነው

☞ ካለ መንፈስ ቅዱስ ማገልገል ከባድ ነው

☞ ካለ መንፈስ ቅዱስ መዘመር ከባድ ነው

☞ ካለ መንፈስ ቅዱስ መኖር ራሱ ከባድ ነው

ለመንፈሳዊ ሰው ህይወት ሊከብደው የሚችለው ገንዘብ ባጣ ጊዜ ሳይሆን የመንፈስ ቅዱስን መገኘት በህይወቱ ላይ ሳይሰማው በሚቀርበት ጊዜ ነው፤ መንፈስ ቅዱስ ለህይወታችን በጣም ይጠቅመናል ከምንለው አየር ይበልጥ እንደሚያስፈልገን ማወቅ አለብን።
መንፈስ ቅዱስ ሆይ ታስፈልገናለህ
በ2015 ዓ,ም ላይ መንፈስ ቅዱስ መመላለስ እና አብሮ መስራት ይሁንላችሁ
https://t.me/Emmausmengdgnch
https://t.me/Emmausmengdgnch
109 views🇩aኒ Revival , edited  10:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-16 11:48:05 መዝሙር 27 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁷ እግዚአብሔር ሆይ፤ ድምፄን ከፍ አድርጌ ስጮኽ ስማኝ፤ ራራልኝ፤ ስማኝም።
⁸ “ፊቴን ፈልጉ” ባልህ ጊዜ፤ ልቤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ፊትህን እሻለሁ አለች።
ይህ ዘመን የእግዚአብሔርን ፊት የምንሻበት ክብሩን የምናይበት ይሁን
የማይቋረጥ የፊቱ ብርሃን የክብሩ ደመና ህይወታችሁንና ቤታችሁን ይሙላ
https://t.me/Emmausmengdgnch
https://t.me/Emmausmengdgnch
61 views🇩aኒ Revival , edited  08:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ