Get Mystery Box with random crypto!

የኤማሁስ መንገደኞች........ channel )

የቴሌግራም ቻናል አርማ emmausmengdgnch — የኤማሁስ መንገደኞች........ channel )
የቴሌግራም ቻናል አርማ emmausmengdgnch — የኤማሁስ መንገደኞች........ channel )
የሰርጥ አድራሻ: @emmausmengdgnch
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 316

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-09-10 21:42:49 #ሩት

የአህዛብ ሴት/ሞዓባዊት

ሩት 1 (Ruth)
4፤ እነርሱም #ከሞዓባውያን ሴቶች ሚስት አገቡ፤ የአንዲቱ ስም ዖርፋ የሁለተኛይቱም ስም #ሩት ነበረ። በዚያም አሥር ዓመት ያህል ተቀመጡ።

ሞዓብ ደግሞ ሎጥ ከመጀመሪያ ሴት ልጁ የወለደው

ዘፍጥረት 19 (Genesis)
36፤ የሎጥም ሁለቱ ሴቶች ልጆች ከአባታቸው ፀነሱ።
37፤ #ታላቂቱም ወንድ ልጅ ወለደች ስሙንም #ሞዓብ ብላ ጠራችው፤ እርሱም እስከ ዛሬ #የሞዓባውያን አባት ነው።

ሞዓባዊያን የእስራኤልን መብዛትና ሰላማቸውን የማይፈልጉ ጠላቶች ናቸው ሰለዚህም #እርግማን ሊያደረጉባቸው ፈለጉ

ዘኍልቍ 22 (Numbers)
16-17፤ ወደ በለዓምም መጥተው፡— የሴፎር ልጅ ባላቅ፡— ክብርህን እጅግ ታላቅ አደርገዋለሁና፥ የተናገርኸውንም ሁሉ አደርግልሃለሁና እባክህ፥ ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ ምንም አይከልክልህ፤ እባክህ፥ ና፥ ይህን ሕዝብ #ርገምልኝ አለ፡ ብለው ነገሩት።

የተወዳዳችሁ ወንድሞቼ #ሩት አህዛብ ነች ይህ ብቻ አይደለም የምትኖረው በርግማን የሚታወቅ ንጉስ በሚገዛበት ከተማ ነው።

በአንድ አጋጣሚ ከይሁዳ ቤተልሔም ወጥተው ወደ ሞዓብ የሄዱ ቤተሰቦች ነበሩ

ሩት 1 (Ruth)
1፤ እንዲህም ሆነ፤ መሳፍንት ይፈርዱ በነበረ ጊዜ በአገሩ ላይ ራብ ሆነ። አንድ ሰውም ከሚስቱና ከሁለቱ ልጆቹ ጋር #በሞዓብ ምድር ሊቀመጥ #ከቤተ ልሔም #ይሁዳ ተነሥቶ ሄደ።
2፤ የሰውዮውም ስም አቤሜሌክ፥ የሚስቱም ስም ኑኃሚን፥ የሁለቱም ልጆች ስም መሐሎንና ኬሌዎን ነበረ፤ #የቤተ ልሔም #ይሁዳም የኤፍራታ ሰዎች ነበሩ። ወደ #ሞዓብም ምድር መጡ በዚያም ተቀመጡ።

እነዚህ ቤተሰቦች ይኖሩበት የነበረው ከተማ የምስጋና/ይሁዳ እንዲሁም የእንጀራ ቤት/የሚበላ ያለበት/ቤቴልሔም ከተማ ውስጥ ነበር።

እንግዲህ ከምስጋናና ሁሉ ከሞላበት ከተማ ወጥተው ወደ እርግማን ከተማ ሞዓብ ሲሂዱ ያተረፉት ሞት ነበር።

ሩት 1 (Ruth)
3፤ የኑኃሚንም ባል አቤሜሌክ #ሞተ፤ እርስዋና ሁለቱ ልጆችዋ ቀሩ።
5፤ መሐሎንና ኬሌዎንም ሁለቱ #ሞቱ፤ ሴቲቱም ከሁለቱ ልጆችዋና ከባልዋ ተለይታ ቀረች።

የሩት መጽሐፍ ስናነብ ኑኃሚን እና ሩት ከዚህ ሁሉ በኋላ ከሞዓብ ወደ ይሁዳ ቤተልሔም ለመምጣት ተነሱ ፤ ወዳጆቼ ወደ ቤቴልሔም ቢመጡ ኑኃሚን የቀድሞ ከተማዋ ነወ፣ቤተሰብ አላት፣ ረስት ነበራት ነገር ግን #ሩት ወገን አልነበረችም፣ ለእስራኤል ቤት የተሰጠው ተስፋ የላትም፣በእነርሱ ዘንድ ርስት የላትም ፣ለከተማው እንግዳ ነች/ባለገር አይደለችም

#ሩት በይሁዳ ርስትን ታገኝ ዘንድ ርስትን ሊሰጣት ፈቃደኛ የሚሆን ቤዛ/የሚቤዣት ያስፈልጋት ነበር ለዚህም ቦዔዝ ርስትን ይስጣት ዘንድ ሩት ሚስቱ አድርጎ ወሰዳት/ተቤⶳት።

አማኝ ልክ እንደ ሩት ነው።

ኤፌሶን 2 (Ephesians)
11፤ ስለዚህ እናንተ አስቀድሞ #በሥጋ #አሕዛብ የነበራችሁ፥ በሥጋ በእጅ የተገረዙ በተባሉት ያልተገረዙ የተባላችሁ፥ ይህን አስቡ፤
12፤ በዚያ ዘመን #ከእስራኤል #መንግሥት #ርቃችሁ #ለተስፋውም #ቃል #ኪዳን #እንግዶች ሆናችሁ በዚህም ዓለም #ተስፋን #አጥታችሁ #ከእግዚአብሔርም #ተለይታችሁ ያለ ክርስቶስ ነበራችሁ።
13፤ #አሁን #ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል።

ቆላስይስ 2 (Colossians)
13፤ እናንተም በበደላችሁና ሥጋችሁን ባለመገረዝ ሙታን በሆናችሁ ጊዜ፥ ከእርሱ ጋር ሕይወትን ሰጣችሁ። በደላችሁን ሁሉ ይቅር አላችሁ።

ወንድሞች እኛ በክርስቶስ ቤዛነት ከእርግማን ወደ በረከት ከአንዳች ወደ ሙሉነት ከሞት ወደ ህይወት ከጨለማ ወደ ብርሃን መለኮታው ልውውጥ ተደርጎልናል!!!
https://t.me/Emmausmengdgnch
https://t.me/Emmausmengdgnch
820 views🇩aኒ Revival , 18:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 14:37:31 * ዕድልን ጠብቃት! *

ዕድል ቱታ ስለለበሰች እና ሥራን ስለምትመስል ለብዙ ሰዎች አትገለጥም። ቶማስ ኤዲሰን

እንቅስቃሴ ላይ ከሆንክ ዕድልን በቀላሉ መለየትና መጠቀም ትችላለህ። እንዲሁ ቁጭ ብለህ የምትጠብቃት ከሆነ ግን እድልን አታገኛትም። ምክንያቱም ዕድል የምትገለጠው በእንቅስቃሴ ላይ ለሆኑ ሰዎች ብቻ ነው።

እናም ወዳጄ ሆይ ዕድለኛ ለመሆን የምትፈልግ ከሆነ ሁልጊዜም ሥራ ላይ መሆን አለብህ። ሥራ ላይ ሆንክ ማለት ዕድል እየጠበቅህ ነው ማለት ነው። እሷም አታሳፍርህም ትመጣልሃለች።

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
https://t.me/Emmausmengdgnch
https://t.me/Emmausmengdgnch
41 views🇩aኒ Revival , 11:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 20:48:20
https://t.me/Emmausmengdgnch
https://t.me/Emmausmengdgnch
https://t.me/Emmausmengdgnch
179 views🇩aኒ Revival , edited  17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 17:48:46 ይህን ሃሳብ አስታውስ . . .

1መኖር ካለ መሳሳትና መውደቅ አለ፣ መሳሳትና መውደቅ ካለ ደግሞ ልምድ፣ ትምህርትና መሻሻል ይከተላሉ፡፡ ይህ የስኬታማ ሰዎች ልምምድ ነውና እውነታውን ተቀበለው፡፡
https://t.me/Emmausmengdgnch
https://t.me/Emmausmengdgnch
55 views🇩aኒ Revival , edited  14:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 19:46:07 Channel photo updated
16:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 19:25:45 #ለሕልማችሁ #ቆራጦች #ሁኑ
አንድት ሴት ከባሏ ጋር ጥሩ ትዳር እንዲኖራት እና በባሏ ልብ ውስጥ ንግሥት ለመሆን ፈልጋ እንድረዳት አንድ አዋቂ ዘንድ ትሄዳለች ። አዋቂውም ከባልሽ ጋር ፍቅር ያለው ትዳር እንደምትመሰርቺ ብቻ ሳይሆን በባልሽ ልብ ውስጥም መንገሥ እንደምትችዪ ልረዳሽ እችላለሁ አላት ። ይህንን ለማድረግ ግን አንድ ነገር ማድረግ እንዳለባትና የሚላትን ነገር ለማድረግ ቃል እንድትገባለት ጠየቃት ።

ሴትዮዋም በጣም በመደሰት "ብቻ የትዳሬን ችግር ፍታልኝ እንጂ ያዘዝከኝን ነገር ያለ ምንም ድርድር ለማድረግ ቃሌን እሰጥሃለሁ " ትለዋለች ። ቃሏን በመጠበቅ እንድታደርግለት ይፈልግ የነበረውም አንድ የአንበሳ ጸጉር ከአንበሳ ፊት ላይ ይዛ እንድትመጣ ነበር ። እሷም የአንበሳን ጸጉር ማምጣቷ እንዴት አድርጎ የትዳሯን ችግር ሊፈታላት እንደምችል ባይገባትም የምትታዘዘውን ነገር ሁሉ ለማድረግ ቃል ሰለገባች ያለ ምንም ጥያቄ የታዘዘቸውን የአንበሳ ጸጉር ለማምጣት ሄደች።

ከተወሰነ ጊዜ በኃላ ሴትዮዋ አንድ አዲስ ከአንበሳ ፊት የተነቀለ ጸጉር ይዛ ወደ አዋቂው ትመለሳለች። አዋቂው ሴትዮዋ ያመጣችው የአንበሳ ጸጉር ከአንበሳ ፊት የተነቀለና እሷ ራሷ የነቀለች መሆኑን ካረጋገጠ በኃላ አንድ ጥያቄ ጠየቃት ።


እንዴት አድርገሽ ነው ከአንበሳው ፊት ጸጉር መንቀል የቻልሺው? ጠየቃት እሷም በመደመሪያ አንበሶች የሚገኙበትን ቦታ በመፈለግ ሰለ አንበሶችጨባህሪ ጥናት በማድረግ ጀመርኩ ። በመቀጠል ከሁሉም አንበሶች ውስጥ በመምረጥ ለአንበሳው በየቀኑ ምግብ መውሰድ ጀመርኩ ። ከተወሰነ ጊዜ በኃላም አንበሳው ለመደኝና ወደ እኔ መጠጋት ጀመረ ከዚያም ከቆይታዎች በኃላ ከኔ ጋር መጫወት ጀመረ እኔም አንድ ቀን አብሮኝ ከተጫወተ በኃላ ደክሞት ሲተኛ ከፊቱ ላይ አንድ ጸጉር ነቅዬ ወደ አንተመጣሁ በማለት ታሪኳን አጫወተችው።

አዋቂውም ' በዚያ የአራዊት ሁሉ ንጉስ በሆነው አንበሳ ልብ ውስጥ በፍቅር መንገሥ ከቻልሽ አንዴት አድርገሽ በባልሽ ልብ ውስጥ መንገሥ እንደምትችዪ አንቺ ራስሽ ጠንቅቀሽ ታወቂያለሽ ብሎ መለሰላት ። አዋቂው ለሴትዮዋ ብቻ ሳይሆን ለሁላችንም የሚሆን ምክር ነው የሰጠውጨ። ህልማችንን የምንፈልገው ከሆነና ህልማችንን ለማሳካት መከፈል ያለበትን መሥዋዕትነት የምንከፍል ከሆነ ማንኛውንም ችግር ዕንቅፍት መከራ ፍራቻ በማሸነፍ ህልማችንን በእጃችን መጨበጥ እንችላለን።
“ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።”
— ፊልጵስዩስ 4፥13
ለሚወዱ 10 ጓደኛው ሼር ያድርጉ
https://t.me/Emmausmengdgnch
https://t.me/Emmausmengdgnch
34 views🇩aኒ Revival , edited  16:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 14:02:25 #ይራራልናል
የሚራራልን ደካማ ስለሆንን ነው፤ በኃጢአት ለመውደቅ በጣም ቅርብ ስለሆንን እንዳንወድቅ ይደግፈናል።

“ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም።”
— ዕብራውያን 4፥15

''ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው'' የሚለው ሃሳብ የሚያሳየን፥ ኢየሱስ ንፁህ መሆኑንና በእኛ ኃጢአት ምክንያት የመጣውን ፈተና በሙሉ መፈተኑን የሚያሳይ ነው። ለምን? መሰላችሁ፤ እኛ ተፈትነን አንዱንም ፈተና ማለፍ አንችልም፤ ኢየሱስ ግን በምድር ላይ መጥቶ ፈተናችንን ሁሉ ተፈተነ፤ ለዚህ ነው የሚራራልን፥ አሜን።

ኢየሱስ በድካማችን፣ ይራራልናል
መንፈስ ቅዱስ ደግሞ፥ በድካማችን ያግዘናል
እግዚአብሔር አብ ደግሞ እጁን ዘርግቶ ያወጣናል፤ አባታችን ነውና

በየትኛውም ፈተና ውስጥ ብትሆኑ ለብቻችሁ አይደላችሁም፤ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው። አሜን
ከተባረኩበት ለሚወዱት 5 ወዳጆ
ሼር ያድርጉ ....ሼር ሰላደረጉ ጌታ በዚህ ሳምንት የለመንከውን ይመልስልህ ሰታናግረው ይስማህ
https://t.me/Emmausmengdgnch
https://t.me/Emmausmengdgnch
https://t.me/Emmausmengdgnch
26 views🇩aኒ Revival , edited  11:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 20:31:39 "ብሞት ይሻለኛል!"

• እስከ ሕይወቴ ፍጻሜ ድረስ የምከተለው ዓላማ ሳይኖረኝ ከምኖር "ብሞት ይሻለኛል"!

• ራሴን፣ ዓላማዬንና ስራዬን በማሻሻል ላይ ከማተኮር ይልቅ ስለሰዎች ሳስብና ሳወራ ከምኖር "ብሞት ይሻለኛል"!

• ቢያንስ በአንድ ሰው ላይ መልካም ተጽእኖ ሳላሳድር ከምኖር "ብሞት ይሻለኛል"!

• በየእለቱ ሳልለወጥ በአንድ አይነት አመለካከት፣ ስፍራና ልምምድ እየረገጥኩ ከምኖር "ብሞት ይሻለኛል"!

• መንቀሳቀስ እስከማልችል ድረስ በፍርሃት ታስሬ ከምኖር "ብሞት ይሻለኛል"!

• በሰዎች ላይ ቂም ይዤ እነሱን ካልተበቀልኩኝ በስተቀር ውስጤ አላርፍ እያለኝና እየነደደ ከምኖር "ብሞት ይሻለኛል"!

• አንድ ሰው ስለገፋኝና ትቶኝ ስለሄደ ብቻ ነገን ማየት እስከማልችል ድረስ የወደቀ ስሜት ይዤ ከምኖር "ብሞት ይሻለኛል"!

• ይህንን የ”ብሞት ይሻለኛል” አቋም ካነበነብኩት በኋላ ከመፈክር ባላለፈ ሁኔታ ለውጥን ሳላመጣ ራሴን እዚያው ነገር ላይ ከማገኘው "ብሞት ይሻለኛል"!

https://t.me/Emmausmengdgnch
https://t.me/Emmausmengdgnch
https://t.me/Emmausmengdgnch
47 views🇩aኒ Revival , edited  17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 07:56:38 #ደህንነት_እና_አክሊል
=========================
ክፍል ሁለት (2)
---------------
2 ጢሞቴዎስ 2:15
የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ።
በክርስትናው አለም ስለ ዘላለም ሕይወትና ስለ አክሊል ግልጽ የሆነ ትምህርት ካለመኖሩ የተነሳ በቅዱሳን መካከል ብዙ ግራ መጋባቶች ይታያሉ፡፡
ይህንን ትምህርት የምናጠናበት ምክንያት የእግዚአብሔር ቃል እንደሚገባ በማጥናት በዘላለም ሕይወትና በአክሊል መካከል ያሉትን ልዩነቶች በማወቅና ግራ ላለመጋባት፡፡
ያለ አላማና ያለ ግብ ላለመኖርና የድሉን ሽልማት (አክሊልን) እንደሚቀበል ሯጭ በክርስቶስ ያለውን ሩጫ እንደሚገመባ ለመሮጥና ከክርስቶስ አክሊልን (ሽልማትን ፣ ብድራትን) ለመቀበል፡፡
በደህንነት(በዘላለም ህይወት) እና በሽልማት መካከል ያሉ ልዩነቶች፡፡
==================================
2) ደህንነት(የዘላለም ሕይወት) ቅጽበታዊ ነው፡፡
----------------------------
ዮሐ 3:18,36, ዮሐ 5:24, 1ዮሐ 5:13
በክርስቶስ የቤዛነት ስራ ባመንበት ቅጽበት የሚፈጸምና የምንቀበለው ነው፡፡
ዮሐንስ 5 (John)
24፤ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን #የዘላለም_ሕይወት_አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።
1 ዮሐንስ 5 (1 John)
11፤ እግዚአብሔርም #የዘላለምን_ሕይወት_እንደ_ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው።
12፤ #ልጁ_ያለው_ሕይወት_አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።
13፤ #የዘላለም_ሕይወት_እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁ።
2) አክሊል ወደ ፊት የሚፈጸም ነው::
------------------------
2 ጢሞ 4፡8,ራዕ 22:12,1ጴጥ 5:4,ሉቃ 14:14
በክርስቶስ የቤዛነት ስራ አምነው የዳኑና የጸደቁ ቅዱሳን በሕይወታቸው የጽድቁን ኑሮ እየተለማመዱ የጌታ ኢየሱስን በክብር መገለጥ በናፍቆት ለሚጠባበቁ ሁሉ የሚሰጥ አክሊል ነው፡፡
2 ጢሞቴዎስ 4 (2 Timothy)
7፤ መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤
8፤ #ወደ_ፊት_የጽድቅ_አክሊል_ተዘጋጅቶልኛል፥ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፥ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም።
ይቀጥላል.......
ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ሰላም ብዙ ምህረት ለሁላችንም ይብዛ። አሜን
https://t.me/Emmausmengdgnch
https://t.me/Emmausmengdgnch
24 views🇩aኒ Revival , edited  04:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 14:05:14
https://t.me/Emmausmengdgnch
https://t.me/Emmausmengdgnch
https://t.me/Emmausmengdgnch
19 views🇩aኒ Revival , edited  11:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ