Get Mystery Box with random crypto!

#ለሕልማችሁ #ቆራጦች #ሁኑ አንድት ሴት ከባሏ ጋር ጥሩ ትዳር እንዲኖራት እና በባሏ ልብ ውስጥ ን | የኤማሁስ መንገደኞች........ channel )

#ለሕልማችሁ #ቆራጦች #ሁኑ
አንድት ሴት ከባሏ ጋር ጥሩ ትዳር እንዲኖራት እና በባሏ ልብ ውስጥ ንግሥት ለመሆን ፈልጋ እንድረዳት አንድ አዋቂ ዘንድ ትሄዳለች ። አዋቂውም ከባልሽ ጋር ፍቅር ያለው ትዳር እንደምትመሰርቺ ብቻ ሳይሆን በባልሽ ልብ ውስጥም መንገሥ እንደምትችዪ ልረዳሽ እችላለሁ አላት ። ይህንን ለማድረግ ግን አንድ ነገር ማድረግ እንዳለባትና የሚላትን ነገር ለማድረግ ቃል እንድትገባለት ጠየቃት ።

ሴትዮዋም በጣም በመደሰት "ብቻ የትዳሬን ችግር ፍታልኝ እንጂ ያዘዝከኝን ነገር ያለ ምንም ድርድር ለማድረግ ቃሌን እሰጥሃለሁ " ትለዋለች ። ቃሏን በመጠበቅ እንድታደርግለት ይፈልግ የነበረውም አንድ የአንበሳ ጸጉር ከአንበሳ ፊት ላይ ይዛ እንድትመጣ ነበር ። እሷም የአንበሳን ጸጉር ማምጣቷ እንዴት አድርጎ የትዳሯን ችግር ሊፈታላት እንደምችል ባይገባትም የምትታዘዘውን ነገር ሁሉ ለማድረግ ቃል ሰለገባች ያለ ምንም ጥያቄ የታዘዘቸውን የአንበሳ ጸጉር ለማምጣት ሄደች።

ከተወሰነ ጊዜ በኃላ ሴትዮዋ አንድ አዲስ ከአንበሳ ፊት የተነቀለ ጸጉር ይዛ ወደ አዋቂው ትመለሳለች። አዋቂው ሴትዮዋ ያመጣችው የአንበሳ ጸጉር ከአንበሳ ፊት የተነቀለና እሷ ራሷ የነቀለች መሆኑን ካረጋገጠ በኃላ አንድ ጥያቄ ጠየቃት ።


እንዴት አድርገሽ ነው ከአንበሳው ፊት ጸጉር መንቀል የቻልሺው? ጠየቃት እሷም በመደመሪያ አንበሶች የሚገኙበትን ቦታ በመፈለግ ሰለ አንበሶችጨባህሪ ጥናት በማድረግ ጀመርኩ ። በመቀጠል ከሁሉም አንበሶች ውስጥ በመምረጥ ለአንበሳው በየቀኑ ምግብ መውሰድ ጀመርኩ ። ከተወሰነ ጊዜ በኃላም አንበሳው ለመደኝና ወደ እኔ መጠጋት ጀመረ ከዚያም ከቆይታዎች በኃላ ከኔ ጋር መጫወት ጀመረ እኔም አንድ ቀን አብሮኝ ከተጫወተ በኃላ ደክሞት ሲተኛ ከፊቱ ላይ አንድ ጸጉር ነቅዬ ወደ አንተመጣሁ በማለት ታሪኳን አጫወተችው።

አዋቂውም ' በዚያ የአራዊት ሁሉ ንጉስ በሆነው አንበሳ ልብ ውስጥ በፍቅር መንገሥ ከቻልሽ አንዴት አድርገሽ በባልሽ ልብ ውስጥ መንገሥ እንደምትችዪ አንቺ ራስሽ ጠንቅቀሽ ታወቂያለሽ ብሎ መለሰላት ። አዋቂው ለሴትዮዋ ብቻ ሳይሆን ለሁላችንም የሚሆን ምክር ነው የሰጠውጨ። ህልማችንን የምንፈልገው ከሆነና ህልማችንን ለማሳካት መከፈል ያለበትን መሥዋዕትነት የምንከፍል ከሆነ ማንኛውንም ችግር ዕንቅፍት መከራ ፍራቻ በማሸነፍ ህልማችንን በእጃችን መጨበጥ እንችላለን።
“ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።”
— ፊልጵስዩስ 4፥13
ለሚወዱ 10 ጓደኛው ሼር ያድርጉ
https://t.me/Emmausmengdgnch
https://t.me/Emmausmengdgnch