Get Mystery Box with random crypto!

'ብሞት ይሻለኛል!' • እስከ ሕይወቴ ፍጻሜ ድረስ የምከተለው ዓላማ ሳይኖረኝ ከምኖር 'ብሞት ይሻ | የኤማሁስ መንገደኞች........ channel )

"ብሞት ይሻለኛል!"

• እስከ ሕይወቴ ፍጻሜ ድረስ የምከተለው ዓላማ ሳይኖረኝ ከምኖር "ብሞት ይሻለኛል"!

• ራሴን፣ ዓላማዬንና ስራዬን በማሻሻል ላይ ከማተኮር ይልቅ ስለሰዎች ሳስብና ሳወራ ከምኖር "ብሞት ይሻለኛል"!

• ቢያንስ በአንድ ሰው ላይ መልካም ተጽእኖ ሳላሳድር ከምኖር "ብሞት ይሻለኛል"!

• በየእለቱ ሳልለወጥ በአንድ አይነት አመለካከት፣ ስፍራና ልምምድ እየረገጥኩ ከምኖር "ብሞት ይሻለኛል"!

• መንቀሳቀስ እስከማልችል ድረስ በፍርሃት ታስሬ ከምኖር "ብሞት ይሻለኛል"!

• በሰዎች ላይ ቂም ይዤ እነሱን ካልተበቀልኩኝ በስተቀር ውስጤ አላርፍ እያለኝና እየነደደ ከምኖር "ብሞት ይሻለኛል"!

• አንድ ሰው ስለገፋኝና ትቶኝ ስለሄደ ብቻ ነገን ማየት እስከማልችል ድረስ የወደቀ ስሜት ይዤ ከምኖር "ብሞት ይሻለኛል"!

• ይህንን የ”ብሞት ይሻለኛል” አቋም ካነበነብኩት በኋላ ከመፈክር ባላለፈ ሁኔታ ለውጥን ሳላመጣ ራሴን እዚያው ነገር ላይ ከማገኘው "ብሞት ይሻለኛል"!

https://t.me/Emmausmengdgnch
https://t.me/Emmausmengdgnch
https://t.me/Emmausmengdgnch