Get Mystery Box with random crypto!

#ደህንነት_እና_አክሊል ========================= ክፍል ሁለት (2) ------ | የኤማሁስ መንገደኞች........ channel )

#ደህንነት_እና_አክሊል
=========================
ክፍል ሁለት (2)
---------------
2 ጢሞቴዎስ 2:15
የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ።
በክርስትናው አለም ስለ ዘላለም ሕይወትና ስለ አክሊል ግልጽ የሆነ ትምህርት ካለመኖሩ የተነሳ በቅዱሳን መካከል ብዙ ግራ መጋባቶች ይታያሉ፡፡
ይህንን ትምህርት የምናጠናበት ምክንያት የእግዚአብሔር ቃል እንደሚገባ በማጥናት በዘላለም ሕይወትና በአክሊል መካከል ያሉትን ልዩነቶች በማወቅና ግራ ላለመጋባት፡፡
ያለ አላማና ያለ ግብ ላለመኖርና የድሉን ሽልማት (አክሊልን) እንደሚቀበል ሯጭ በክርስቶስ ያለውን ሩጫ እንደሚገመባ ለመሮጥና ከክርስቶስ አክሊልን (ሽልማትን ፣ ብድራትን) ለመቀበል፡፡
በደህንነት(በዘላለም ህይወት) እና በሽልማት መካከል ያሉ ልዩነቶች፡፡
==================================
2) ደህንነት(የዘላለም ሕይወት) ቅጽበታዊ ነው፡፡
----------------------------
ዮሐ 3:18,36, ዮሐ 5:24, 1ዮሐ 5:13
በክርስቶስ የቤዛነት ስራ ባመንበት ቅጽበት የሚፈጸምና የምንቀበለው ነው፡፡
ዮሐንስ 5 (John)
24፤ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን #የዘላለም_ሕይወት_አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።
1 ዮሐንስ 5 (1 John)
11፤ እግዚአብሔርም #የዘላለምን_ሕይወት_እንደ_ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው።
12፤ #ልጁ_ያለው_ሕይወት_አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።
13፤ #የዘላለም_ሕይወት_እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁ።
2) አክሊል ወደ ፊት የሚፈጸም ነው::
------------------------
2 ጢሞ 4፡8,ራዕ 22:12,1ጴጥ 5:4,ሉቃ 14:14
በክርስቶስ የቤዛነት ስራ አምነው የዳኑና የጸደቁ ቅዱሳን በሕይወታቸው የጽድቁን ኑሮ እየተለማመዱ የጌታ ኢየሱስን በክብር መገለጥ በናፍቆት ለሚጠባበቁ ሁሉ የሚሰጥ አክሊል ነው፡፡
2 ጢሞቴዎስ 4 (2 Timothy)
7፤ መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤
8፤ #ወደ_ፊት_የጽድቅ_አክሊል_ተዘጋጅቶልኛል፥ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፥ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም።
ይቀጥላል.......
ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ሰላም ብዙ ምህረት ለሁላችንም ይብዛ። አሜን
https://t.me/Emmausmengdgnch
https://t.me/Emmausmengdgnch