Get Mystery Box with random crypto!

#እኔ_የአለም_ብርሃን_ነኝ =============================== ዮሐንስ | የኤማሁስ መንገደኞች........ channel )

#እኔ_የአለም_ብርሃን_ነኝ
===============================
ዮሐንስ 8 (John)
12፤ ደግሞም ኢየሱስ፡— እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም፡ ብሎ ተናገራቸው።
ወደ ፍጥረት መጀመሪያ ስንሄድ በዘፍጥረት 1:2-3" እግዚአብሔር በቃሉ ይሁን ብሎ የፈጠረው ምድር በአንዳች ምክንያት ይበላሻል (በሰይጣን መውደቅ ምከንያት) ምድርም ባዶ፣ቅርጽ አልባና #በጨለማ ተውጣ ነበር። የእግዚአብሔርም መንፈስ በውሆች ላይ ሰፍፎ ነበር።
እግዚአብሔርም ብርሀን ይሁን ሲል መንፈስ ቅዱስ የተበላሸውን ነገር ማስተካከል መስመር ማስያዝ ምድርን ማስዋብ ከጨለማ ማውጣት ጀመረ።
ይህ በዘፍጥረት 1:3 ላይ የተገለጠው ብርሀን ያልተፈጠረ ፥ የነበረ ፥ መፍጠርና ማስተካከል የሚችል ነገር ሳይሆን ማንነት(person) የሆነ ነው። እግዚአብሔር የሚፈጥረውም ፍጥረት ሲበላሽ የሚያስተካክለውም በዚህ ማንነት በሆነ ብርሃን (በኢየሱስ ክርስቶስ) ነው።
ፍጥረት ሲበላሽ የሚስተካከለው በተፈጠረበት መንገድ ነው።
ይሁን ተብሎ የተፈጠረ ፍጥረት ሲበላሽ የሚስተካከለው ይሁን በማለት ነወ።
እኛም በኀጢአት ምክንያት ማንነታችን ተበላሽቶ ነበር መልክና ምሳሌአችን ተበላሽቶ በእግዚአብሔር መልክ ሳይሆን ኃጥያተኛ በሆነው በአዳም መልክና ምሳሌ ነው የተወለድነው። ሲቀጥል በአየር ላይ በምድር ላይ በውሀ ውስጥ የሚንቀሳቀሰውን ግዛ ተብሎ ስልጣን ተሰቶት ነበር በኃጢአት ምክንያት ስልጣኑን ለሰይጣን አሳልፎ ሰጥቶ ባዶ አደረገን በመጨረሻም ብርሀን ከሆነው አምላክ ርቆ ከሰይጣን ጋር ተባብሮአልና የሰው ልጆች ሁሉ ጨለማ ነበርን ይላል መጽሐፍ ቅዱስ።
ኤፌሶን 5 (Ephesians)
8፤ ቀድሞ ጨለማ ነበራችሁና፥ አሁን ግን በጌታ ብርሃን ናችሁ፤
ፍጥረት ሲበላሽ የሚስተካከለው በተፈጠረበት መንገድ ነው።
ይሁን ተብሎ የተፈጠረ ምድር ሲበላሽ የሚስተካከለው ይሁን በማለት ነው።ለዛም እግዚአብሔር ብርሃን ይሁን ብሎ አስተካክሏል የሰው ልጅ ግን ይሁን ተብሎ አልተፈጠረምና ይሁን ተብሎ ሊስተካከል አይችልም።
እግዚአብሔር ሰውን ከምድር አፈር ወርዶ አበጀው ይላል ወርዶ የሰራው ፍጥረት ሲበላሽ ወርዶ ነው የሚያስተካክለው ለዛም ነው ይህ ብርሃን የሆነ ጌታ እኛን ለማዳን በባህሪው አምላክ ሆኖ ሳለ መተካከልን እንደመቀማት ሳይቆጥር የባሪያን መልክ ይዞ በኀጢአተኞች መካከል የተገኘው።ስሙ ይባረክ። ሳይጸየፈን ወደ እኛ የመጣ፥ በጨለማችን ላይ ብርሃን ሆኖ የተገለጠ ፥ጨለማችንን ገፎ የህይወት ብርሃን የሆነልን፥ ከጨለማ ወደሚደነቀው ብርሃኑ ያመጣን ፥ዘላለማችንን በድምቀቱ ያስዋበ ፥የማይጨልመው የህይወት ብርሃናችንን የናዝሬቱ ኢየሱስ ነው
ዮሐንስ 1 (John)
4፤ በእርሱ ሕይወት ነበረች፥ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች።
5፤ ብርሃንም በጨለማ ይበራል፥ ጨለማም አላሸነፈውም።
ዮሐንስ 1 (John)
9፤ ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም ይመጣ ነበር።
ዮሐንስ 8 (John)
12፤ ደግሞም ኢየሱስ፡— እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም፡ ብሎ ተናገራቸው።
ማቴዎስ 5 (Matthew)
14፤ እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም።
ዮሐንስ 12 (John)
46፤ በእኔ የሚያምን ሁሉ በጨለማ እንዳይኖር እኔ ብርሃን ሆኜ ወደ ዓለም መጥቻለሁ።
ኤፌሶን 5 (Ephesians)
8፤ ቀድሞ ጨለማ ነበራችሁና፥ አሁን ግን በጌታ ብርሃን ናችሁ፤
“በክርስቶስ ፊት እግዚአብሔር የክብሩን ዕውቀት ብርሃን ይሰጠን ዘንድ፣ “በጨለማ ብርሃን ይብራ” ያለው እግዚአብሔር ብርሃኑን በልባችን አብርቶአልና።”
— 2ኛ ቆሮንቶስ 4፥6 (አዲሱ መ.ት).
ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለሁላችንም ይሁን።
የወንጌል እውነት ቤተክርስቲያን ጅማ
https://t.me/Emmausmengdgnch