Get Mystery Box with random crypto!

አድኅነነ እግዚኦ እስመ ሃልቀ ሔር

የቴሌግራም ቻናል አርማ dnhayilemikael — አድኅነነ እግዚኦ እስመ ሃልቀ ሔር
የቴሌግራም ቻናል አርማ dnhayilemikael — አድኅነነ እግዚኦ እስመ ሃልቀ ሔር
የሰርጥ አድራሻ: @dnhayilemikael
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.11K
የሰርጥ መግለጫ

#መሰረታዊ_የቤተክርስቲያን_ክርስቲያን_ትምህርት /
#የተለያዩ_ተከታታይ_ትምህርት '
#ስንክሳር_የቅዱሳን_ገድል_በየዕለቱ !
#ስዕለ_አድህኖ !
#ምስባክ
#የየበአላቱ_ዋዜማና_ሥርተ_ማህሌት
#መዝሙር
#ግጥም
#ለመናፍቃን_ጥያቄ_መልስ
እና የተለያዩ የቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ
ሌሎች መንፈሳዊ ጽሁፎች
ይለቀቁበታል
Administration

@zearsema_dn

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-27 16:30:52 #ቤተ_ክርስቲያን_የመሳለም_ሥርዓት

ጠዋትና ማታ ቤተ ክርስቲያን ለመሳለም መትጋት ያስፈልጋል። (ምሳ.8:34)
ወደ ቤተክርስቲያን ሲገባ ከቅፅረ ቤተክርስቲያን በር ላይ ሲደርሱ መሳለም ይገባል።

መዝ.28፥2፣ 95፥9፣ ኤር.26፥2፣ ሕዝ.46፥3፣ ፊልጵ 2፥9-10
ሁላችሁም አስተውሉ ስንሳለም እንደት ነው????

መጀመሪያ ቀኝ እጅን ላይ ዋ ጣታችንን ቀጥ እናደርጋለን
ከዛ እረጅም ወይም የመሀል ጣታችንን እጥፍ እናደርጋለን ከ ዋ ጣት ጋር ስናገናኘው መስቀል ይሰራል ከዋላ ያሉትን ሁለት ጣቶች እንዲመቸን አጠፍ አጠፍ እናደርጋቸዋለን።

#ምሳሌያቸው

በቀኝ እጅ መሳለማችን ገነትን በመሻት ወይም እግዚአብሔር በገነት ስለሆነ ያለው ገነትን ለማመልከት ነው።

መስቀል መስራችን ደግሞ መዳናችንን ለማመልከትና እንደተሰቀለ ለመመስከር ነው።

ስንሳለም በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ማለት አለብን።
ትርጉሙም፥ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ነው ማለት ነው።

ስንሳለም፥ መጀመሪያ መስቀል እንደሰራን በቀኝ እጃችን ግንባራችን ላይ እናደርጋለን።

#ምሳሌው፥ እግዚአብሔር በሰማይ እንደሚኖር እንደማይመረመር ለመግለፅ ነው።

ከዛ፥ ወደ ታች እደረታችን እና ሆዳችን አካባቢ እናደርጋለን።

ምሳሌው፥ ጌታ ከሰማየ ሰማያት መውረዱን ከድንግል ማርያም መወለዱን ለመግለ ነው።

ከዛ፥ ወደ ግራ ጎንአችን ከጡታችን በላይ እናደርጋለን።

#ምሳሌው፥ አዳም አባታችን የሞትን ሞት እንደሞተ እና ሲኦል እንደ ገባ ለመግለፅ ነው።

በመጨረሻም፥ ወደ ቀኝ ጎናችን እናደርጋለን።

#ምሳሌው፥ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳምን ከገነት ይዞ ጠላታችን ዲያቢሎስን አስፎ ወደ ገነት መግባቱን ለመግለፅ ነው።

ወደ ቤተክርስቲያን ሲገቡ ጫማን አውልቆ ወገብን ታጥቆ አደግድጎ መግባት ነው። ጫማ አድርጎ ቤተ ክርስቲያን መግባት ክልክል ነው።
ዘፀ 3፥5- ዮሐ.ሥ 7፥33
ኢያ 5፥ 15 ፍት፡መን፡12

ሃሳብን በመንፈሳዊ ነገር ወስኖ ወደ ውጪ ወደ አለማዊ ነገር እንዳይሄድ መግታትና መቆጣጠር ያስፈልጋል።
ከካህን ቀርቦ መስቀል መሳለምና በረከትም መቀበል ያሻል።

በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተስለው የሚገኙትን የሥላሴን ፣ የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ፣ የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያምን ፣ የመላእክትን ፣
የነቢያትን ፣ የፃድቃንን ፣ የሰማዕታትን ፣ የደጋጎች ቅዱሳንን ሥዕሎች እጅ መንሳትና የአክብሮት ስግደት መስገድ ይገባል።

በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አስተውሉመሳቅ
ሥለ አለማዊ ሥራ መነጋገር ክልክል ነው።

ከገቡ በኋላ:ዝምታ:ፀጥታ
ፍርሃት የእግዚአብሔርን ምህረት በጥብዓተ ልብ መፈለግ አለብን።


ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያን የመዘምራንን ማሕሌት፣ የቅዱሳን መላእክትን ምስጋና ፣ የነቢያትን ትንቢት ፣ የሐዋርያትን ስብከት መስሚያና የልዑል እግዚአብሔርን ነገር መማሪያ ቦታ ስለሆነች ነው።

ከዚህም በላይ የሥጋ ወደሙ ምስጢር የሚፈፀምበት ቦታ ስለሆነች ነው።
ዘሌ. 26፥2

#አስተውሉ
አጭርና ያደፈ ልብስ ለብሶ ወደ ቤተክርስቲያን መሔድ ክልክል ነው። ረዘም ያለ እና ንፁህ ልብስ ለብሶ መሔድ ያስፈልጋል።
ዘፀ. 19፥10-11

በተለይ #ሴቶች እራሳችንን ተከናንበን እንዲንፀልይ ታዘናል።

በመጨረሻም ወደ ቤተክርስቲያን ባዶ እጅ መሔድ አይገባም ። መባዕ፣ ምፅዋት ይዞ መሔድ ይገባል። ዘጸ.34፥20

ወሰብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን ይቆየን

https://t.me/dnhayilemikael
197 views13:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 10:26:33 ዘፈን በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ

ክፍል 1

ዘፈን ጥበብ ነውን
?

ዘፈን ጥበብ ነው የሚሉ አሉ። አዎን ጥበብ ነው ከእግዚአብሔር ሳይሆን ከሰይጣን የተገኘ ጥበብ ነው፤ ቅዱስ ሳይሆን ርኩስ ጥበብ ነው፤ መዳኛ ሳይሆን መጥፊያ ጥበብ ነው፤ የህይወት ሳይሆን የሞት ጥበብ ነው፡፡ ይህን ሳስብ ቅዱስ ጳውሎስ የዚች ዓለም ጥበብ በእግዚአብሔር ዘንድ ሞኝነት ነው ያለው ትዝ አለኝ

እግዚአብሔር ድምፅ የሰጠን እሱን እንድናመሰግንበት እሱን እንድናወድሰው፣ እሱ የፈቀደላቸውን እሱ ያከበራቸውን ቅዱሳኑን እንድናመሰግንበት ነው እንጂ ለሰው እንድንዘፍን አይደለም። ወይ የእግዚአብሔር ወይም የዓለም ልንሆን ግድ ይለናል፤ ሁለት ጌታ የለም።  ዘፈን መዝፈን ኃጢያት ነው

አሁን ባለንበት ዘመን ዘፈን ኃጢያት እንደሆነ፤ የዲያቢሎስ ታላቅ መሳሪያ እንደሆነ፤ ዘፋኝነት ከክርስቶስ ማህበር እንደሚለይ በግልጽ እየተመለከትን ነው። ዘፈን ስራ ነው የሚሉ አሉ አዎን ለዘፋኝ መዝፈን ስራው ነው፤ ለሌባም መስረቅ ስራው ነው፤ ለዝሙት አዳሪዋም ዝሙት ስራዋ ነው፤ ለቅጥረኛ ነፍሰ ገዳይም መግደል ስራው ነው ግን ደግሞ ኃጢያት ናቸው ስራዬ ነው ብሎ ኃጢያትነቱን ማስቀረት አይቻልም፡፡ እንግዲህ ምን እንላለን ኃጢያትን ስራ ነው ብለን ሙግት እንገጥማለንን ?

እየመረጥን ብንዘፍንስ ለመልካም የተዘፈኑ ዘፈኖች አሉ የሚሉም ብዙ ናቸው። ዘፈን ሀጥያት ነው በቃ ምንም ጥያቄና መልስ የለውም ቴዲ ስለዘፈነው መዝሙር መሆን አይችልም ስለ ሀገር ሆነ ስለምን.. ስለ ሀገር ጸልዩ እንጁ ዝፈኑ አልተባለም፣ እናት ቢዘፈንላትስ ይላል ደሞ አንዱ፣ እድሜህ እንዲረዝም እናትና አባትህን አክብር ይላል እንጂ ዝፈንላቸው አይልም!! ብዙ ሰው ጥብቅና ለቆመለት ሰው ቃሉ ይህን ይላል

<< ዘፋኝነት፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜም እንዳልሁ፥ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም!!።">>(ወደ ገላትያ ሰዎች 5:21)

አንድ ሌባ ሰርቆ የተራበ ቢያበላ ጽድቅ ነውን??? የተቸገሩ ሰዎችን ከችግራቸው ያላቅቅ ዘንድ አጥብቆ የሚተጋ አንድ ሰው ሌሎችን ለመርዳት የሚያስፈልገውን ገንዘብ ለማግኘት ዝሙትን መፈጸም ግድ ቢሆንበት እርሱም ሰውነቱን አርክሶ ዝሙትን ፈጽሞ ገንዘቡን ቢቀበል ችግረኞቹንም ከችግራቸው ቢያላቅቅ መልካም አደረገ እንለዋለንን??? ዘፈን ያስደስታል፣ ዘና ያደርጋል፣ ደስታ ይፈጥራል ... ወዘተ ምክንያቶች እየደረደርን ጥብቅና አንቁም! መልካምን ነገር ለማድረግ በኃጢያት ውስጥ ማለፍ አይጠበቅብንም፤  ኃጢያትን ያደረገ ኃጢያተኛ እንጂ ጻድቅ ሊባል አይችልም፡፡ ነገሩ ከዝንጀሮ ቆንጆ ምን ይመራርጡ ነው እንዲያ ካልሆነማ፤ ከኃጢያት ከተመረጠማ ለዘፈን ብቻ ለምን ?

የዘፈነው ለመልካም ነው፤ ፍቅርን ለመስበክ ነው፤ አንድነትን ለማምጣት ነው ካልን ሌባውም የሰረቀው የተቸገሩትን ሊያበላ ነው፤ ሰውየውም ዝሙት የፈጸመው ችግረኞችን ለመርዳት ነው፣ ነፈሰ ገዳዩም እንጀራ ሆኖበት ነው። ስለዚህ እነዚህም አብረው ይጽደቁ? እንዲህ ከሆነ ደግሞ ኃጢያተኛ ሁሉ ጻድቅ ሆነ ማለት ነው። ራሳችንን ከማታለል እንውጣ፤ ከአዚም እንላቀቅ አትግደል ከተባለ አትግደል ነው፤ አትስረቅም አትስረቅ ነው፤ አትዝፈን ሲልም አትዝፈን ነው፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ተመራጭ አገዳደል፤ ተቀባይነት ያለው ስርቆት፤ የሚወደድ ዘፈንም የለም ... ይቀጥላል

https://t.me/dnhayilemikael
2.7K views07:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 10:04:01 ብሒላዊ ምክር

መርገም-= አቅም ሲያንስ ወደላይ የሚወረወር የዴማ ሰዎች
ቀስት ነው:
መሳደብ= ህሊናን የሚያቆስል ቁስሉ ቶሎ የማይድን አቅም የሌላቸው ሰዎች ዱላ ነው:
ዋዛ ፈዛዛ- በስልት የሚቃኙት የሥራ ፈቶች በገና ነው
የማይገባ ሣቅ= ሐላፊ አግዳሚውን የሚያጠምዱበት አመንዝሮች ወጥመድ ነው::
መሳለቅ= በአካል ጉዳተኛ ሰው ላይ የሚዘብቱበት የመርገም ስንቁ ወግ ነው
ዘፈን= ለዝሙት የሚያነቃ ልብ የሚወጋ ክፉ ፍላፃ ነው።
319 views07:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 21:02:31 ቡሄ ማለት ምን ማለት ነው
ችቦ ለምን እና መቼ ይበራል
ሙልሙል ልምን ይታደላል
በቡሄ ወቅት ጅራፍ ለምን ይጮሃል

​​​​ቡሄ


ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል የሚዘከርበት እና ለበዓሉም ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል በማለት የቡሄ በዓል እንላለን፡፡ ወቅቱ የክረምት ፤ጨለማ አልፎ የብርሃን የሚወጣበት፤ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቅት ነው፡፡ “ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት” እንዲሉ፡፡ በሌላ በኩልም “ቡኮ/ሊጥ” ተቦክቶ ዳቦ የሚጋገርበት “ሙልሙል” የሚታደልበት በዓል በመሆኑ ቡሄ ተብሏል፡፡

ጅራፍ

በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ምስጢር፤ በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ምስጢራዊ ሞቱ ነው፡፡ ጅራፍ መገመድ(መጥለፍ) እና ጅራፍ ማጮኽ ሁለት ዓይነት ምስጢር የያዘ ትውፊታዊ ተግባር ነው፡፡

የመጀመሪያው ግርፋቱንና ሞቱን እናስብበታለን፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ፤ድምፁን ስንሰማ የባሕርይ አባቱን የአብን ምስክርነት ቃል፤ እንደ ነጎድጓድ ድምፅ ያስታውሰናል፡፡

የጅራፍ ትውፊታዊነት /ውርስ/፣ መጽሐፋዊ ትምህርትና ምስጢር ጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ጨዋታውን በተራራማ አካባቢ፣ ከመኖሪያ ቤት ርቆና፣ በሜዳ ማድረጉ ጠቃሚ ነው፡፡ ጅራፍን #በርችት መቀየር የሚያመጣውን የምስጢር ተፋልሶ ብቻ መመልከት ከማኅበራዊ ጎጂ ገጽታው በላይ እንድናስወግደው ያስገድደናል፡፡

ችቦ

ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥ የሚያመለክት ነው፡፡ በመሆኑም ችቦ ለኩሰን በዓሉን እናከብራለን፡፡ የዚህ ትውፊታዊ አመጣጥ በብርሃኑ ድምቀት የቀኑን መምሸት ያልተረዱ እረኞች በሜዳ ቀርተዋልና ወላጆች ከመንደር ችቦ ለኩሰው ልጆቻቸውን ፍለጋ ሔደዋልና ታሪኩን እያዘከርን በዓሉት እናከብራለን፡፡

የችቦው መንደድም ሌላ ትርጉም አለው፡፡ አንድ ምእመን ለሌላው ምእመን መካሪ አስተማሪ መሆኑን፣ መከራ እየተቀበለም አርአያ፣ ምሳሌ፣ ብርሃን መሆኑን ያሳያል፡፡ በሃይማኖትም አርአያ ምሳሌ ይሆንላቸዋል፡፡ ከዚህ ጋርም ተያይዘዞ ችቦ በ13 ምሽት ይበራል ፣ብርሃኑ የተገለጠው በዚችው ዕለት ነውና ፡፡

ሙልሙል

በችቦ ብርሃን ልጆቻቸውን ፍለጋ የወጡ ወላጆች ዳቦ ጋግረው ይዘውላቸው ወጥተዋል፡፡ ስጦታው ቤተሰባዊነትን፣ ፍቅርንና መተሳሰብን መግለጫ ነው፡፡ ወደ ቤታችን “ ቡሄ ” እያሉ ለሚመጡ አዳጊዎችም፤ ዘምረው እንዳበቁ የሚሰጥ “ሙልሙል” ዳቦ አለ፡፡ ሕፃናቱም ሊዘምሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ አይደለም፡፡

ሕፃናቱ የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ ሐዋርያት “የምሥራች” ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋርያት በገቡበት አገር አስተምረው አጥምቀው የጸጋ ልጅነትን አሰጥተው በረከት አድለው እንደሚሔዱም፣ ልጆችም ዘምረው፣ አመስግነው፣ መርቀው “ውለዱ ክበዱ፣ ሀብት አግኙ፣ የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ….” ይላሉ፡፡

በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከእነዚህ ምስክር ካላቸው ትምህርቶቹ፣ ምሥጢር ከሚራቀቅባቸው ትርጓሜያቱና ከትውልድ ትውልድ በቅብብል በተላለፈው ቅዱስ ትውፊት ጋር ሃይማኖታዊ ባሕል ሆኖ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡

ይህን ማድረግ የሚቻለው ግን አዳጊዎች ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ይዘው እንዲያድጉ ጥቆማ በመስጠት፣ ግጥም በመግጠምና ምሥጢሩን በማብራራት የመጀመሪያዎቹ ባለድርሻዎች ወላጆች ናቸው፡፡

አንዳንድ ጊዜ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ፣ ፌዝና ሥላቅ የተቀላቀለባቸው ይሆናሉ፡፡ ሕፃናቱም ዝማሬውን ሲጀምሩ “ከሰጡን እንነሣ ከነሱን እናርዳ” ብለው ይጀምሩታል፡፡ ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን በማለት፡፡

አሳሳቢው ነገር ደግሞ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛነት የቀየሩ ሁኔታዎች መታየታቸው ነው፡፡ ዳቦ /ሙልሙል/ ትምህርቱንም፣ ምስጢሩንም፣ ትውፊቱንም በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል።

ከዚም ጋር ተያይዞ ሰንበት ት/ት ቤታችን ለበረካታ ዓመታት ሲወርድ የመጣውን የዝማሬ ሥርዓት ለአጥብያው ምእምን በየቤቱ በመሄድ የብሄን ዝማሬ ከነሥርዓቱ በመዘመር አገልግሎት ይሰጣል ፤የደብር ታቦርን በዓል በተመለከትም የወረቀት ጽሑፎችን ይበትናል በዝማሬ መኃል ያድላል፡፡

ቤተክርስቲያን የምሥጢር ግምጃ ቤት ናት፤ የምታከናውነውን ሁሉ ከበቂ መረጃ ጋር ነው ተግባራዊ የምታደርገው፡፡ በተለይ ወጣቱ ክፍል ይህንን አውቀን ተረድተን ለቀሪው ትውልድ ማስተላለፋ እንችል ዘንድ ከክፉ ጠላት ከሰይጣን ፈተና፣ በሽታ ከመሳሰሉት ችግሮች ለመዳን ወደ ተራራዋ ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በመሸሽ ከክፉ ነገሮች ሁሉ ማምለጥ ይቻላል፡፡

በቤተ ክርስቲያን ጥላ ሥር የሚጠለሉ ሁሉ ዕድሜያቸው ይረዝማል፡፡ አስተዋዮችም ይሆናሉ ሁሉን ማየትና የሚጠቅማቸውን መምረጥ ይችላሉ በሥነ-ምግባር የታነፁ አገርንና ወገንን የሚጠቅሙ ወደ
ቅድስት ቤተክርስቲያን በመጠጋት ከክፉ ሁሉ የሚያመልጡ ይሆናሉ ለዚህም የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡

https://t.me/dnhayilemikael
1.6K views18:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 20:52:39 አንድ ክርስቲያንም እውነተኛ ክርስቲያን የሚባለው ምን ሲሆን ነው ???

ፀሐይ ብርሃን ካልሰጠች ፀሐይ አትባልም፤ ብርሃን አለመስጠት ተፈጥሮዋ አይደለምና፡፡ እንስሳት ካልተነፈሱ እንስሳት አይባሉም፤ መተንፈስ ተፈጥሮአቸው ነውና፡፡ ዓሣ ከውኃ ከወጣ ሕይወት ያለው ዓሣ መኾኑ ይቀርና ይሞታል፡፡ አንድ ክርስቲያንም እውነተኛ ክርስቲያን የሚባለው፡-

#ሲጸልይ_ነው፡፡ ክርስቲያን ማለት በወልድ ውሉድ በክርስቶስ ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስም መንፈሳዊ መባል ነውና፡፡ ልጅ ከኾኑ ደግሞ አባትን ማናገር ክርስቲያናዊ ተፈጥሮ ነውና፡፡

#ሲያመሰግን_ነው፡፡ ክርስቲያን ማለት እግዚአብሔር ፈጣሬ ዓለማት ነው ብሎ ማመን ነውና፡፡ ስለዚህ ለአንድ ክርስቲያን የሰማይና የምድር ውበት እየተመለከተ እግዚአብሔርን ማመስገኑ ክርስቲያናዊ ተፈጥሮው ነው፡፡

#ሲመጸውት_ነው፡፡ ክርስቲያን ማለት ሀብት ኹሉ ከእግዚአብሔር እንደ ኾነ መመስከር ነውና፡፡ ስለዚህ ራስን እንደ መልእክተኛ አድርጎ በመቁጠር ያለውን ለሌላው ማካፈል ክርስቲያናዊ ተፈጥሮው ነውና፡፡

#ቅዱሳት_መጻሕፍትን_ሲያነብ_ነው፡፡ ክርስቲያን ማለት በመንፈስ ቅዱስ ሀብት ደስ የሚሰኝ ነውና፡፡ይህን ለማድረግ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ በቅዱሳት መጻሕፍት በኩል ሲናገር መስማት ለአንድ ክርስቲያን ክርስቲያናዊ ተፈጥሮው ነውና፡፡

https://t.me/dnhayilemikael
475 views17:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 16:08:13 "አንተ ሰው ምን ትመልስ ይሆን ? !!!"

"በቅምሻ የሚቀር እድሜ ስንቶችን ከፈጣሪ ለየ !!
የምንሞት ቀርቶ የምናረጅ እንኳን አይመስለን። ታዲያ ሞት አንደሆነ ቀጠሮውን አያሳልፍ ። ስራውም እንዲሁ ይኸው ነው። ከአቤል ጀምሮ እስካሁን በሚገባ ትዕዛዙን ሲወጣ እኛ ግን ይኸንንም ለማሰብ ጊዜ የለንም!!እስኪ ልብ እንበል ማነው የዚችን አለም ጣዕሟን ይከ ነው ብሎ መናገር የሚችል..በሚገባ ለመቅመስ እንኳን ጣሟን አትሰጠንም።
ወንድሜ ሁሉም አይቀርም ይሄዳል አጠራሩ ሊለያይ አንጂ መጨረሻ ሞትም መሞቱ አይቀር።
ታዲያ ሁሉም ሔያጅ ተሆነ እኛ ዘላለም በምድር የምንኖር ለምን ይመስለናል።
ሞት አንደሁ እንኳን እኛ በዚች ከሰማንያንያ አመት ለማታልፍ እድሜያችን ይቅርና ማቱሳላንም አልቶወው ። በመጠኑ ኖረን እስኪ እንደ ሰው እንሙት!!እንደሰው ተፈጥረን ለምን እንደእንስሳ ለመሞት እንሽቀዳደማለን?እሱም እሚጠቅመን በሆነ በተከተልነው !!!እሳትንና ፍትፍትን በማይለየው እጃችን ዘወትር ስንጎርስ ኖርን። ከንቱ ነገርስ ለምን እንመለከታለን? እንሰማለንስ? የምናይበት አይናችን የምንሰማበት ጆሮስ የማነው??እኛ እንኳን የራሳችን አይደለንም ከሆንን እራሳችንን ከየት አመጣነው? ሁላችንም ዋጋ አለብን ሁላችንም የተገዛን ነን ።
በደስታ እንኳን አይደል በስቃይ
በገንዘብ እንኳን አይደል በደም
በእረፍት እንኳን አይደል በስቃይ
በሰላምታ እንኳን አይደለ በግርፋት
በመከበር እንኳን አይደል በእንግልት በሞት በስቅላት
ታዲያ የዚክን ዋጋ ምን ብለን እንመልሳለን?
ዘወትር ሰውን ስሳደብ ከምዕመን እስከ ጳጳስ ያሉትን ሰዎች ስተች ኖርኩልህ እንለው ይሆንን?
ዘወትር በአካሌ በመልኬ ስነግድ ኖርኩልህ ትለው ይሆንን?
ዘወትር በየአደባባዩ ጨፍሬልሀለሁ ቲያትር ሰራሁ እንለው ይሆንን
ዘወትር ከሺሻ ቤት ሺሻ ቤት ስዘልህ ነበር እንለው ይሆንን
ዘወትር ቅጠል እንደፍየል ሳባርር ኖርኩ እንለው ይሆንን
ዘወትር ስንቱን ደናግል ከክብር አሳነስኩልህ እንለው ይሆንን
ዘወትር ከብዙ ቆንጆዎች ጋር በዝሙት ስረክስልህ ነበር ትለው ይሆንን?
ብዙ ገንዘብ አጠራቀምኩልህ ቤት ሰራሁ መኪና ገዛሁ ትለው ይሆንን?
ዘወትር አይኔን በፊልም አደከምኩልህ ትለው ይሆንን?
ዘወትር የአለም ህዝብ ፊልም እንዲያዩ አዳረስኩልህ ትለው ይሆንን
በየገዳማቱ የተነሳሀቸውን ብዙ ፎቶዎች አጠራቅመህ ይከው ላንተ የተነሳሁልህ ትለው ይሆንን?
ዘወትር በየሆቴሉ ስጋ እንደ ድመት ሳሳድድልህ ኖርኩ ትለው ይሆንን?
የባህታዊ እከለ የመምህር እከለ ደጋፊ ነኝ ትለው ይሆንን!?
ዘወትር በየእስፖርት ቤቱ በመዞር ድንጋይ በመግፋት እራሴን አደለብኩልህ አፈረጠምኩልህ ትለው ይሆንን?
ዘወትር እራቁቴን በመሄድ የብዙ ወንዶችን ቀልብ ሳብኩ ነፍሳቸውንም ተጠያቂ አደረኩ ትይው ይሆንን?
ሌሊቱንበሙሉ እንደ እንስሳ ተኝቼ አደርኩልህ ትለው ይሆንን?
እስከ መቼ የተለሰነ መቃብር ሁነን??
ተው ይበቃሀል ተመለስ!!!
አንዲት የእንባ ዘለላ ከአይንህ አፍልቅ።በእርሷ እግዚአብሔርን ማየት ትችላለሕ።
ወዳጄ ጊዜሕ አሁን ብቻ ናት!!!!

" *ዝንቱ ዘመን ድልው ውእቱ ለዘይፈቅድ ንሰሀ "*
"ይህ ዘመን መልካም ነው ንስሀን ለፈለገ ሰው"
ዮሐነስ ዘእስክንድርያ
═════════❁ሰናይ ቀን❁ ═════════
https://t.me/dnhayilemikael
441 views13:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 15:41:51
ከንጉሥ ካህን ይበልጣል!

የንጉሥ ሥልጣን በሥጋ ላይ ነው፤
የካህን ሥልጣን ግን በነፍስ ላይ ነው፡፡
ንጉሥ ይቅር ቢል የገንዘብን ዕዳ ነው፤
ካህን ይቅር ሲል ግን የበደል የኃጢአት ዕዳን ነው፡፡
ንጉሥ ያዝዛል፤
ካህን ግን ያስተምራል ይዘክራል፡፡
ንጉሥ ያስገድዳል፤
ካህን ግን ነጻ ፈቃድን ያያል፡፡
ንጉሥ ቁሳዊ የጦር ዕቃ መሣሪያ አለው፤
ካህን ግን ረቂቅ (መንፈሳዊ) የጦር ዕቃ መሣሪያ አለው፡፡
ንጉሥ የጦር ዕቃ መሣሪያውን ቢሰብቅ አንገዛም ብለው ባመፁት (እንዲሁም ከወራሪዎች ሥጋውያን ደማውያን) ላይ ነው፤
ካህን ግን ውጊያው ከጨለማ አበጋዞች ከአጋንንት ጋር ነው፡፡

ስለዚህ ሥልጣነ ክህነት ከሥልጣነ መንግሥት ይበልጣል፡፡ እንዲህም በመኾኑ ንጉሥ አንገቱን ለካህናት እጅ ያጎነብሳል፡፡
442 views12:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 21:04:25 ሃሌ-ሉያ አንተ ሰው ሆይ

ሃሌሉያ አንተ ሰው ሆይ (4)
ቡሄ መድረሱን ሰምተሃል ወይ
ሀሌሉያ አንተ ሰው ሆይ
መስማቱንማ ሰምቼ ነበር
ሀሌሉያ አንተ ሰው ሆይ
ከዚያ ቢያደርሰኝ ልዑል እግዚአብሔር
ሃሌሉያ አንተ ሰው ሆይ

እናቴ ሆይ.......... ሆ
ይህን ባየሻ ........ሆ
በቁርማ ዳቦ .......ሆ
ሲጥለኝ ውሻ........ሆ
ደጓ ጫማዋን ......ሆ
አውልቃዋለች.......ሆ
ውሃ ሲጠማ.........ሆ
አጠጥታዋለች......ሆ
የስዋ ውዳሴ .......ሆ
ሆኖኛል ውይን ......ሆ
ዘሬም ብዘምር ......ሆ
እኖራለሁኝ ...........ሆ
ዘምር በለው ተነሳ በገናን አንሳ (4)

በእምነት እንውጣ .ሆ
ከተራራው ላይ......ሆ
ይታይ ብርሃኑ........ሆ
ክብሩ ኤልሻዳይ....ሆ
ሙሴን እንጠይቅ...ሆ
የጥንቱን ነገር .......ሆ
ምን እንደሚለው ...ሆ
ጌታን ሲያናግር......ሆ
ድምጹን እንስማ ....ሆ
እንደ ትሁትነቱ.......ሆ
እንቀበለው ..........ሳ
እኛም በትሩን .......ሆ
ዘምር በለው ተነሳ በገናን አንሳ (2)
ተቁኙለት በልልታ ላዳኙ ጌታ(2)

ተራራውማ ..........ሆ
ነውና አምሳል.......ሆ
ለቤተ ክርስቲያን...ሆ
መንበረ ልዑል........ሆ
ወጥተን እንጠይቅ .....ሆ
ኤልያስን.............ሆ
እንድንዳስሰው.....ሆ
ጸጓራር ክንዱን....ሆ
ሰማይ በትለጉም...ሆ
ባህር ቢከፍል.......ሆ
እሳት ብታወርድ.....ሆ
ጠላትም ቢርድ......ሆ
በሰረገላ ..............ሆ
የተነጠከው...........ሆ
ይህ ሁሉ ክብር .....ሆ
በማን ስልጣን ነው....ሆ
ለሁላችን መልካም ነው በዚህ መኖር(4)

የእመብርሃን .........ሆ
የምዬ ልጅ............ሆ
ተጥሎ ላይቀር .....ሆ
ተረስቶ ደጅ...........ሆ
ሰአሊ ለነ .............ሆ
ባለበት አፉ...........ሆ
የጭንቁን እለት.....ሆ
ተሰብሮ ሰልፉ......ሆ
እንዳባቶቹ ............ሆ
ቅኔን ተቀኘ.............ሆ
ድንግል ስትረዳው....ሆ
አይኑ ስላየ..............ሆ
ተፈስሂ ደብረ ታቦር(2)
ተፈስሂ አርሙኒየም (2)
ባንቺ ላይ ታየ እግዚአብሔር
ተፈስሂ አርሙንየም

ሙሴ ስላለ ............ሆ
መና ያውርዳል........ሆ
ቅዱስ ኤልያስ.........ሆ
ስጋ ያመጣል..........ሆ
ዮሃንስንም............ሆ
ጌታ ይወዳል.........ሆ
መድኃኒታችን........ሆ
ፈውስ ይሆነናል.....ሆ
በዚህ እንድንኖር ...ሆ
ዳሱን ጥለናል .....ሆ
ዘምር በለው ተነሳ በገናን አንሳ (4)

አባቴም ቤት..........ሆ
አለኝ ለከት.............ሆ
እናቴም ቤት ...........ሆሆ
አለኝ ለከት...,..........ሆ
ፍልሰታ ስትሆን.......ሆ
የቆምኩባት............ሆ
በድብረ ታቦር .........ሆ
ያጌጥኩባት...........ሆ
ዘምር በለው ተነሳ በገናን አንሳ(2)
ተቀኙለት በልልታ ላዳኙ ጌታ(2)

አመት አውዳመት "ድገምና" አመት "ድገምና"
ያባብዬን ቤት "ድገምና" አመት "ድገምና"
ይግባ በረከት "ድገምና" አመት "ድገምና"
የማምዬ ቤት "ድገምና" አመት "ድገምና"
ይትረፍረፍ በእውነት "ድገምና" አመት "ድገምና"
ነሩ በሀይማኖት
ጽኑ በጸሎት
በተዋህዶ ቤት(4)

የሰማይ ሰራዊት "በእምነት" ያድርጋችሁ "አሜን"
አማኑኤል በጸጋ "በእምነት" ያኑራችሁ "አሜን"
ከስጋ ወደሙ "በእምነት"
ያድላችሁ "አሜን"
ዘርን እደ አብርሃም "በእምነት"
ያብዛላችሁ "አሜን"
ይባረክ በእግዚአብሔር በእምነት ዘመናችሁ "አሜን"/2/
እድሜና ጤናውን በእምነት ያድላችሁ "አሜን" (2)




እን_ዘም_ር
https://t.me/dnhayilemikael
https://t.me/dnhayilemikael
https://t.me/dnhayilemikael
435 views18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 20:47:29 ወደ እግዚአብሔር መገስገስ

"የማወቅ ጥማትህ እግዚአብሔርን ለማወቅ የማይፈልግ ከሆነ ከንቱ ነው ፡፡ ስለ ምድር አውቀህ ስለ ሰማይ ዝንጉ ከሆንህ ፣ ስለሚጠፋው እንቅልፍ አጥተህ ስለማይጠፋው ከደነዘዝህ በእውነት ከንቱ ነህ ፡፡ የሚያውቀህን አምላክ ትተህ የማያውቁህን ዝነኞች ስታስስ መዋል ፣ ገና ፈሳሽ ሳለህ ሳትረጋ ያወቀህን ጌታ ገሸሽ ብለህ የካዱህን ስታስብ መኖር ፣ ወላጆችህ ሳያዩህ በዓይነ ምሕረት ያየህን እግዚአብሔር አለማየት ፣ ዓለም ሳይፈጠር የመረጠህን ምርጫህ አለማድረግ በእውነት ከንቱ ነው ፡፡ ደስታ የሌለው እውቀት ፣ ዕረፍት የሌለው ጥበብ እግዚአብሔርን ማወቅ የሌለበት ነው

የተደበቁ ነገሮችን መሰርሰር ትፈልጋለህ ፣ በአደባባይ የተሰቀለውን ጌታ ለማየት ግን ዓይንህን ትጨፍናለህ ፡፡ ትንሽ ቆይቶ ቋንጣ የሚሆነውን ዜና ተሻምተህ ትሰማለህ የዘላለሙን ምሥጢር ግን ችላ ትላለህ ፡፡ የመድኃኒት ሰዓትህን ለማስታወስ ማንቂያ ደወል ትሞላለህ ፣ ቅዳሴ ለመሄድ ግን ሲቀሰቅሱህ ትቆጣለህ ፡፡ የኤምባሲ ቀጠሮህን አትረሳም ፣ ሞትን ረስተህ ግን እንዳሻህ ትናገራለህ

ጦም መቼ ይያዛል የሚለውን ታውቃለህ ፣ ለምን እንደሚጦም ግን አትጠይቅም ፡፡ ፋሲካ መቼ ነው ? ብለህ በግ ትገዛለህ ፣ የታረደውን በግ ክርስቶስን ግን ገሸሽ ትላለህ ፡፡ ዘመን ሲለወጥ እንኳን አደረሳችሁ ትላለህ ያደረሰህን አምላክ ግን ከልብ አታመሰግንም ፡፡ ዘመን ሲጨመርልህ ከመለወጥ ያልጨረስከውን ክፋት ለመፈጸም እንደ ገና ታስባለህ፡፡ እባክህን አንተ ተወዳጅ ሆይ እግዚአብሔርን ማወቅ ሕይወት ልዑሉንም ማስተዋል ጥበብ ነው ፡፡ እርሱን ስታውቅ በማይናወጠው መንግሥቱ ያሳርፍሃል ፡፡ በማይለወጥ ባሕርዩ ያጸናሃል

https://t.me/dnhayilemikael https://t.me/dnhayilemikael

https://t.me/dnhayilemikael
319 views17:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 20:49:50
#ይህን_ያውቁ_ኖሯል?
ሼር አድርጉት
አሐዱ ተብሎ ቅዳሴ ከተገባ በኃላ (በቅዳሴ ሰአት)፡-

- ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መዘዋወር፣
- ቅዳሴ አቋርጦ መውጣት
- የግል ፀሎት ማድረግ፣
- የጸሎት መጽሐፍትን ማንበብ፣
- ሳቅ፣ ወሬ፣
- ሞባይል ማስጮህና ማነጋገር
- ምግብ ይዞ ወደ ቤተ መቅደስ መግባት
- ወደ አውደ ምህረት አካባቢ መጠጋት
- እህቶች ሱሪ አድርገው መምጣት እንዲሁም ፀጉርን በሚገባ ሳይከናነቡ ለቅዳሴ ጸሎት መቆም
- ልጆችን ያለ ነጠላ ማቁረብ
- ቅዱስ ቁርባን በሚሰጥበት ግዜ ስነ-ስርአቱን በቪዲዮ፣ ፎቶ ካሜራ እና በሞባይል መቅረጽና ማንሳት ፈጽሞ የተከለከለ መሆኑን
- በተጨማሪ ህፃናትን ማቁረብ ሲያስቡ በተቻለ መጠን ካህናት ቅዳሴ ከመግባታቸው በፊት ይዘዋቸው ወደ ቤተ-መቅደስ ቢደርሱ መልካም ነውና ዘወትር ይህንን ተግባራዊ ያድርጉ።

#ለሰው_ሳይሆን_ለጌታ_እንደምታደርጉ
#የምታደርጉትን_ሁሉ_በትጋት_አድርጉ


https://t.me/dnhayilemikael
376 viewsedited  17:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ