Get Mystery Box with random crypto!

ወደ እግዚአብሔር መገስገስ 'የማወቅ ጥማትህ እግዚአብሔርን ለማወቅ የማይፈልግ ከሆነ ከንቱ ነው ፡ | አድኅነነ እግዚኦ እስመ ሃልቀ ሔር

ወደ እግዚአብሔር መገስገስ

"የማወቅ ጥማትህ እግዚአብሔርን ለማወቅ የማይፈልግ ከሆነ ከንቱ ነው ፡፡ ስለ ምድር አውቀህ ስለ ሰማይ ዝንጉ ከሆንህ ፣ ስለሚጠፋው እንቅልፍ አጥተህ ስለማይጠፋው ከደነዘዝህ በእውነት ከንቱ ነህ ፡፡ የሚያውቀህን አምላክ ትተህ የማያውቁህን ዝነኞች ስታስስ መዋል ፣ ገና ፈሳሽ ሳለህ ሳትረጋ ያወቀህን ጌታ ገሸሽ ብለህ የካዱህን ስታስብ መኖር ፣ ወላጆችህ ሳያዩህ በዓይነ ምሕረት ያየህን እግዚአብሔር አለማየት ፣ ዓለም ሳይፈጠር የመረጠህን ምርጫህ አለማድረግ በእውነት ከንቱ ነው ፡፡ ደስታ የሌለው እውቀት ፣ ዕረፍት የሌለው ጥበብ እግዚአብሔርን ማወቅ የሌለበት ነው

የተደበቁ ነገሮችን መሰርሰር ትፈልጋለህ ፣ በአደባባይ የተሰቀለውን ጌታ ለማየት ግን ዓይንህን ትጨፍናለህ ፡፡ ትንሽ ቆይቶ ቋንጣ የሚሆነውን ዜና ተሻምተህ ትሰማለህ የዘላለሙን ምሥጢር ግን ችላ ትላለህ ፡፡ የመድኃኒት ሰዓትህን ለማስታወስ ማንቂያ ደወል ትሞላለህ ፣ ቅዳሴ ለመሄድ ግን ሲቀሰቅሱህ ትቆጣለህ ፡፡ የኤምባሲ ቀጠሮህን አትረሳም ፣ ሞትን ረስተህ ግን እንዳሻህ ትናገራለህ

ጦም መቼ ይያዛል የሚለውን ታውቃለህ ፣ ለምን እንደሚጦም ግን አትጠይቅም ፡፡ ፋሲካ መቼ ነው ? ብለህ በግ ትገዛለህ ፣ የታረደውን በግ ክርስቶስን ግን ገሸሽ ትላለህ ፡፡ ዘመን ሲለወጥ እንኳን አደረሳችሁ ትላለህ ያደረሰህን አምላክ ግን ከልብ አታመሰግንም ፡፡ ዘመን ሲጨመርልህ ከመለወጥ ያልጨረስከውን ክፋት ለመፈጸም እንደ ገና ታስባለህ፡፡ እባክህን አንተ ተወዳጅ ሆይ እግዚአብሔርን ማወቅ ሕይወት ልዑሉንም ማስተዋል ጥበብ ነው ፡፡ እርሱን ስታውቅ በማይናወጠው መንግሥቱ ያሳርፍሃል ፡፡ በማይለወጥ ባሕርዩ ያጸናሃል

https://t.me/dnhayilemikael https://t.me/dnhayilemikael

https://t.me/dnhayilemikael