Get Mystery Box with random crypto!

#ይህን_ያውቁ_ኖሯል? ሼር አድርጉት አሐዱ ተብሎ ቅዳሴ ከተገባ በኃላ (በቅዳሴ ሰአት)፡- - ከአን | አድኅነነ እግዚኦ እስመ ሃልቀ ሔር

#ይህን_ያውቁ_ኖሯል?
ሼር አድርጉት
አሐዱ ተብሎ ቅዳሴ ከተገባ በኃላ (በቅዳሴ ሰአት)፡-

- ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መዘዋወር፣
- ቅዳሴ አቋርጦ መውጣት
- የግል ፀሎት ማድረግ፣
- የጸሎት መጽሐፍትን ማንበብ፣
- ሳቅ፣ ወሬ፣
- ሞባይል ማስጮህና ማነጋገር
- ምግብ ይዞ ወደ ቤተ መቅደስ መግባት
- ወደ አውደ ምህረት አካባቢ መጠጋት
- እህቶች ሱሪ አድርገው መምጣት እንዲሁም ፀጉርን በሚገባ ሳይከናነቡ ለቅዳሴ ጸሎት መቆም
- ልጆችን ያለ ነጠላ ማቁረብ
- ቅዱስ ቁርባን በሚሰጥበት ግዜ ስነ-ስርአቱን በቪዲዮ፣ ፎቶ ካሜራ እና በሞባይል መቅረጽና ማንሳት ፈጽሞ የተከለከለ መሆኑን
- በተጨማሪ ህፃናትን ማቁረብ ሲያስቡ በተቻለ መጠን ካህናት ቅዳሴ ከመግባታቸው በፊት ይዘዋቸው ወደ ቤተ-መቅደስ ቢደርሱ መልካም ነውና ዘወትር ይህንን ተግባራዊ ያድርጉ።

#ለሰው_ሳይሆን_ለጌታ_እንደምታደርጉ
#የምታደርጉትን_ሁሉ_በትጋት_አድርጉ


https://t.me/dnhayilemikael