Get Mystery Box with random crypto!

አድኅነነ እግዚኦ እስመ ሃልቀ ሔር

የቴሌግራም ቻናል አርማ dnhayilemikael — አድኅነነ እግዚኦ እስመ ሃልቀ ሔር
የቴሌግራም ቻናል አርማ dnhayilemikael — አድኅነነ እግዚኦ እስመ ሃልቀ ሔር
የሰርጥ አድራሻ: @dnhayilemikael
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.11K
የሰርጥ መግለጫ

#መሰረታዊ_የቤተክርስቲያን_ክርስቲያን_ትምህርት /
#የተለያዩ_ተከታታይ_ትምህርት '
#ስንክሳር_የቅዱሳን_ገድል_በየዕለቱ !
#ስዕለ_አድህኖ !
#ምስባክ
#የየበአላቱ_ዋዜማና_ሥርተ_ማህሌት
#መዝሙር
#ግጥም
#ለመናፍቃን_ጥያቄ_መልስ
እና የተለያዩ የቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ
ሌሎች መንፈሳዊ ጽሁፎች
ይለቀቁበታል
Administration

@zearsema_dn

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-06-17 19:23:54 አባታችን ሆይ እንዴት ትላለህ?

እንደ ልጅ ካልኖርህ እንዴት "አባት" ትለዋለህ?
ሌላውን ጠልተህ ራስ ወዳድ ከሆንክ እንዴት አባት "አችን" ብለህ በአንድነት ትጠራዋለህ?
ምድራዊ ነገር ብቻ እያሰብህ እንዴት "በሰማያት የምትኖር" ትለዋለህ?
ልብህ ከእርሱ ርቆ በአንደበትህ ብቻ እየጠራኸው "ስምህ ይቀደስ" እንዴት ትለዋለህ?

ሥጋዊና መንፈሳዊውን እየቀላቀልህ "መንግሥትህ ትምጣ" ለምን ትለዋለህ?
መከራን በጸጋ የማትቀበል ከሆነ "ፈቃድህ ይሁን" ለምን ትላለህ?
ለራስህ ሆድ እንጂ ለተራቡት ግድ የማይሰጥህ ከሆነ ለምን "እንጀራችንን ሥጠን" ትላለህ?

በወንድምህ ላይ ቂም ይዘህ "እኛም የበደሉልን ይቅር እንደምንል" እንዴት ትላለህ?
የኃጢአትን አጋጣሚዎች ሳትሸሽ "ወደ ፈተና አታግባን" እንዴት ትላለህ?
ክፉን ለመቃወም አንዳች ሳታደርግ "ከክፉ አድነን" እንዴት ትላለህ?

ጸሎቱን ከልብህ ሳትሰማውስ እንዴት አሜን ትላለህ?

#ዲያቆን_ሄኖክ_ኃይሌ
ቻነላችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/dnhayilemikael
3.1K viewsedited  16:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 11:15:00
333 views08:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 11:14:58
303 views08:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 11:14:35 ☞ ከ3 ቢሊየን ብር በላይ የሚፈጅው #የቅዱስ_ያሬድ ግዙፍ ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ።
.
ቅዱስ ያሬድ የምድሪቱ የዜማ ሊቅ የመጀመሪያው ደራሲ እና የዕውቀት ሊቅ መሆኑ ይታወቃል። ይሁን እንጂ ይህ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ሊቅ እንደስሙ እና እንዳበረከተው አስተዋፅዖ ቋሚ የሆነ ማስታወሻ የለውም፡፡ ስለሆነም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዕውቅና የተሰጠው የደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም ህንፃ አሰሪ ኮሚቴ የቅዱስ ያሬድን ግዙፍ ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል።
.
ኮሚቴው ፕሮጀክቱን በማስመልከት ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ የቅዱስ ያሬድን ግዙፍ ፕሮጀክት ከ3 ቢሊየን ብር በላይ እንደሚፈጅ በውስጡም የቅዱስ ያሬድ #የጥናትና ምርምር እና #የቱሪዝም ማዕከል ለመገንባት የሚያስችል መሆኑን በመግለጫው ተነግሯል፡፡ ይህ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ ለኢትዮጵያ ምልክት የሆነውንና ኢትዮጵያዊነትን
በጥበብ ያነጸ ሊቅ አስተምህሮን ከማስረጽ ባሻገር የኢትዮጵያን መጻዒ ዕድል ለመወሰን በሚያስችሉ ዐበይት ጉዳዮች ላይ ትውልድ ግንዛቤ የሚጨብጥበት እንደሚሆን ይታመናል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ውለታዋ ዋጋ አግኝቶ በትውልዱ የሚዘከርበትንና ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት የሚቀነቀንበትን ወርቃማ ዘመን ለመዋጀት እንደሚረዳም በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡
.
በተጨማሪም ለጥበብ ሥራዎቹ የሚመጥንና ለሌሎቹ አብያተ ክርስቲያናት ናሙና ሊሆን የሚችል ይዘትና ቅርጽ ያለው #ቤተ_ክርስቲያን በስሙ ይታነጻል፡፡ እንዲሁም የቅዱስ ያሬድ አምስቱን ጸዋትወ ዜማና ድርሰቶቹን ጨምሮ አጠቃላይ ስራዎቹን መሠረት አድርጎ የታሪክ፣ የፍልስፍና፣ የስነ ውበትና ክዋኔ ጥበብ ጥናትና ምርምር ሊካሄድበት የሚችል የልህቀት ማዕከል ይገነባል ተብሏል። የአምስቱ ጸዋትዋ ዜማ ምስክር ቤት፣ የቅዱስ ያሬድ ሥራዎች የወግ ቁሶችና ቅርሶች እንክብካቤ የሚደረግበት የሚጠበቅበትና ለጥናትና ምርምር የሚውሉ #ሙዚየም እና #ቤተመጽሐፍት እንደሚገነባም ተገልጿል፡፡
.
#ሰኔ 19 ቀን 2014 ዓ.ም #በኤሊያና ሆቴል ይፋዊ የፕሮጀክት ማስተዋወቅ እና #የገቢ_ማሰባሰቢያ መርሐግብር እንደሚያካሂድ ኮሚቴው አስታውቋል፡፡
……
https://t.me/dnhayilemikael
306 views08:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 10:42:52
እግዚአብሔር ዓሣን ሲፈጥር "ሕይወት ያላቸውን አስገኝ" ብሎ ባሕርን ተናገረው

እግዚአብሔር ዛፎችን ሲፈጥር ደግሞ ዛፍ እንድታበቅል መሬትን ተናገራት

ሰውን ሲፈጥር ግን የተናገረው ለራሱ ነበር

እግዚአብሔርም አለ "ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር"

ልብ አድርጉ :-

ዓሣ ከባሕር ከወጣ ወዲያውኑ ይሞታል
ዛፍም ከምድር ላይ ከተነቀለም ይሞታል

ሰውም ከእግዚአብሔር ከተለየ ይሞታል:: ባሕር ለዓሣ መሬት ለዛፍ ተፈጥሮአዊ መጠለያቸው እንደሆነ የሰው ልጆች ተፈጥሮአዊ መጠጊያችንም እግዚአብሔር ነው:: የተፈጠርነው ከእርሱ ጋር ልንኖር ነው:: ሕይወት ያለን ከእርሱ ጋር ነውና መኖር የምንችለው በእርሱ ብቻ ነው::

ይህንንም እናስታውስ

ዓሣ ያለ ባሕር ምንም ነው:: ባሕር ግን ያለ ዓሣ ያው ባሕር ነው:: ዛፍ ያለ መሬት ምንም ነው መሬት ግን ያለ ዛፍ ያው መሬት ነው:: ሰው ያለ እግዚአብሔር ምንም ነው:: እግዚአብሔር ግን ያለ ሰው ያው እግዚአብሔር ነው::

ቅዱስ ባስልዮስ እንዲህ እንዳለ :-

"ጌታ ሆይ የአንተ አምላክነት ለእኔ ያስፈልገኛል እንጂ የእኔ ፍጡርነት ለአንተ አያስፈልግህም"

https://t.me/dnhayilemikael
295 viewsedited  07:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 05:53:26 የመጻህፍት ማዕድ

መጻህፍትን በኦዲዮ

ውድ ኦርቶዶክሳውያን መጽሐፍ ለማንበብ ጊዜ አጥተዋል? ወይስ የሚያስፈልጎትን እና የሚፈልጉትን መጽሐፍ አላገኙም?
እንግዲያውስ ለሁለቱም የሚሆን አማራጭ አቀረብንልዎ። ባሉበት ሆነው ስራ እየሠሩ ጊዜ ሣይገድብዎ ገድላት፣ ታሪክ እና መንፈሳዊ ይዘት ያላቸውን መጽሐፍት በኦድዮ ያድምጡ። መጽሐፍትን ጓደኛ ያድርጉ።
ቻናላችንን Subscribe በማድረግ ይቀላቀሉን። Like,comment and share በማድረግ ያበረታቱን። ቻናላችንን Subscribe በማድረግ ኦርቶዶክሳዊ ተራኪዎችን እንድታበረታቱ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን። ስለምታሳዩንም ቅን የሆነ ማበረታቻ እግዚአብሔር ይስጥልን። የሠማነውን በተግባር እንድንኖር እና የመንግስቱ ወራሽ እንድንሆን የክርስቶስ ቸርነት አይለየን።
341 views02:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ