Get Mystery Box with random crypto!

አድኅነነ እግዚኦ እስመ ሃልቀ ሔር

የቴሌግራም ቻናል አርማ dnhayilemikael — አድኅነነ እግዚኦ እስመ ሃልቀ ሔር
የቴሌግራም ቻናል አርማ dnhayilemikael — አድኅነነ እግዚኦ እስመ ሃልቀ ሔር
የሰርጥ አድራሻ: @dnhayilemikael
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.11K
የሰርጥ መግለጫ

#መሰረታዊ_የቤተክርስቲያን_ክርስቲያን_ትምህርት /
#የተለያዩ_ተከታታይ_ትምህርት '
#ስንክሳር_የቅዱሳን_ገድል_በየዕለቱ !
#ስዕለ_አድህኖ !
#ምስባክ
#የየበአላቱ_ዋዜማና_ሥርተ_ማህሌት
#መዝሙር
#ግጥም
#ለመናፍቃን_ጥያቄ_መልስ
እና የተለያዩ የቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ
ሌሎች መንፈሳዊ ጽሁፎች
ይለቀቁበታል
Administration

@zearsema_dn

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-07-01 09:25:23 #አንተ_አንቺ_ማለት ...

ፀሀይዋን ተመልከታት አታምርም ? ጨረቃዋስ ከዋክብቱስ ዛፎቹ ወንዙና ተራራውስ አያምሩም ? ያምራሉ እኚ ሁሉ ግን ያልፉሉ አንተ ግን በሞት ከዚህ አለም ብትለይ እንኳን በሰማይ ለዘላለም ትኖራለህ ፈጣሪ ፍጥረታትንን ሁሉ በቃሉ በመናገር እና በሀሳብ (በሀልዮ) ሲፈጥር አንተን ግን በእጁ አሽሞንሙኖ ፈጥሮሀል አንተ ማለት ክርስቶስ እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለው ማንም ሚከፍትልኝ ቢኖር ገብቼ እራቴን ከእርሱ ጋር እበላለው ብሎ የተናገረልህ ነህ ፈጣሪ አለምን ከፈጠረበት ጥበብ ይልቅ አለምን ያዳነበት ጥበቡ ይበልጣል ተብሎ የተነገረልህ ዋጋ የከፈለልህ የመንግስቱ ወራሽ ውድ ልጁ ነህ ምን አልባት ዛሬ በተለያየ ሱስ ተይዘህ ይሆናል ምን አልባት ስራ በማጣት ፍቅረኛ በማጣት ትሰቃይ ይሆናል ምን አልባት ቤተሰብህ ወገንህ ተስፉ ቆርጦብህ ይሆናል ምን አልባት ሞትህን እየተመኘህ ይሆናል ግን አይዞህ ፈጣሪ በአንተ የጀመረውን ስራ ሳይጨርስ አትሞትም

ሰው ተስፉ ቢቆርጥብህ እራስህም ተስፉ ብትቆርጥ የፈጠረህ በአንተ ላይ ተስፉ አይቆርጥብህምና አይዞህ 1 ጠጠር አንስተህ ተራራ ላይ ብትወረውር ተራራው ምንም አይሆንም ጠጠሩ ተንከባሎ እግሩ ስር ይሆናል ያን ጠጠር አንስተህ መስታወት ላይ ብትወረውረው ግን መስታወቱ ይሰባበራል ጠጠሩን በችግር እንመስለውና ችግር ወዳንተ ሲመጣ እንደ መስታወቱ አትሰባበር እንደ ተራራው በቁጥጥር ስር አውለው 1 የተለኮሰ የክብሪት እንጨት ጭድ ላይ ብትጥለው ይቀጣጠላል ውሀ ላይ ብትጥለው ግን ውሀው ያጠፉዋል የሚያቃጥሉ ነገሮች በህይወትህ ውስጥ ሲከሰቱ እንደ ጭድ አትቀጣጠል እንደ ውሃው አጥፉቸው

እህቴ ምን አልባት ለስራ ጉዳይ በተለያየ ሀገር ውስጥ ሆነሽ ይሆናል ያለሽው መፈጠርሽ ሴትነትሽም አስጠልቶሽ ይሆናል። ግን ክርስቶስ ወደ አለም ሲመጣ ምድራዊ እናት እንጂ አባት አላስፈለገውም የሴት ልጅ ተብሎ እስኪጠራ ድረስ ማርያም ብቻዋን ነው ያሳደገችው። በኛ ቤተክርስቲያን ህንፃ ቤተክርስቲያኑ ተሰርቶ አለቀ የሚባለው ጉልላቱ ተሰርቶ ሲያልቅ ነው ። ፈጣሪም ፍጥረትን ሁሉ ፈጥሮ ሲጨርስ አዳምን ፈጠረ በመጨረሻም ከጎኑ ሄዋንን ወይም አንቺን የስነ ፍጥረት ጉልላት አርጎ ፈጠረሽ ስለዚህ እህቴ ክብርት ፍጥረት ነሽና ደስ ይበልሽ



@dnhayilemikael
@dnhayilemikael
@dnhayilemikael
307 views06:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 19:49:32 አንድ ክርስቲያንም እውነተኛ ክርስቲያን የሚባለው፡-


ፀሐይ ብርሃን ካልሰጠች ፀሐይ አትባልም፤ ብርሃን አለመስጠት ተፈጥሮዋ አይደለምና፡፡ እንስሳት ካልተነፈሱ እንስሳት አይባሉም፤ መተንፈስ ተፈጥሮአቸው ነውና፡፡ ዓሣ ከውኃ ከወጣ ሕይወት ያለው ዓሣ መኾኑ ይቀርና ይሞታል፡፡

አንድ ክርስቲያንም እውነተኛ ክርስቲያን የሚባለው፡-

1. #ሲጸልይ ነው፡፡ ክርስቲያን ማለት በወልድ ውሉድ በክርስቶስ ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስም መንፈሳዊ መባል ነውና፡፡ ልጅ ከኾኑ ደግሞ አባትን ማናገር ክርስቲያናዊ ተፈጥሮ ነውና፡፡

2. #ሲያመሰግን ነው፡፡ ክርስቲያን ማለት እግዚአብሔር ፈጣሬ ዓለማት ነው ብሎ ማመን ነውና፡፡ ስለዚህ ለአንድ ክርስቲያን የሰማይና የምድር ውበት እየተመለከተ እግዚአብሔርን ማመስገኑ ክርስቲያናዊ ተፈጥሮው ነው፡፡

3.#ሲመጸውት ነው፡፡ ክርስቲያን ማለት ሀብት ኹሉ ከእግዚአብሔር እንደ ኾነ መመስከር ነውና፡፡ ስለዚህ ራስን እንደ መልእክተኛ አድርጎ በመቁጠር ያለውን ለሌላው ማካፈል ክርስቲያናዊ ተፈጥሮው ነውና፡፡

4. #ቅዱሳት #መጻሕፍትን #ሲያነብ ነው፡፡ ክርስቲያን ማለት በመንፈስ ቅዱስ ሀብት ደስ የሚሰኝ ነውና፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ በቅዱሳት መጻሕፍት በኩል ሲናገር መስማት ለአንድ ክርስቲያን ክርስቲያናዊ ተፈጥሮው ነውና፡፡

እግዚአብሔር የተግባር ሰዎች ያድርገን!!

ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ

@dnhayilemikael
@dnhayilemikael
@dnhayilemikael


https://t.me/dnhayilemikael
2.0K views16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 13:08:26 #ልብ_ብለው_ያንብቡ

#ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ዘእንዚናዙ ለንስሓ ልጁ በሰርጓ ቀን መገኘት ባለመቻሉ የላከላት ደብዳቤ


“ልጄ! ለሰርግሽ የነፍስ አባትሽ እኔ ጐርጐርዮስ ይህን ግጥም ስጦታ አድርጌ ልኬልሻለሁ፡፡ አባት ለሚወዳት ልጁ ሊሰጣት የሚችለው የተሻለው ምክርም ይህ እንደ ኾነ አምናለሁ፡፡

“ኦሎምፒያታ ሆይ፥ እውነተኛ ክርስቲያን ለመኾን ያለሽን ፍላጎት ዐውቃለሁና በደንብ አድምጪኝ! እውነተኛ ክርስቲያን እንዲሁ መኾንን የሚመኝ ብቻ ሳይኾን እንደዚያ ለመኾን ሊጥር ይገባዋል፡፡

“ከኹሉም በላይ፥ እግዚአብሔርን ልታከብሪውና ልትወጂው ይገባሻል፡፡ ከእርሱ ቀጥሎም በቅዱስ ወንጌል እንደ ታዘዘው እንደ ጌታችንና መድኃኒታችን [ኢየሱስ ክርስቶስ] አድርገሽ ባልሽን ልታከብሪውና ልትወጂው ይገባሻል፡፡ ስለዚህ እጠይቅሻለሁ! ጌታዋንና ፈጣሪዋን [ኢየሱስ ክርስቶስን] የማታከብርና የማትወድ ሴት በዚህ መንገድ ባልዋን እንዴት አድርጋ ልታከብረውና ልትወደው ትችላለች?

“በጋብቻሽ ውስጥ የትዳር አጋርሽ ይኾን ዘንድ እግዚአብሔር መርጦ ለሰጠሽ ባል ያለሽ መውደድ፣ ስሜትና ፍቅር እጅግ ኃያል ሊኾን ይገባዋል፡፡ ይህ ሰው አሁን የሕይወትሽ ዓይን፣ የልብሽም ደስታ ነውና፡፡

“እግዚአብሔርን እንደምትወጂው፥ ባልሽንም ያለ ቅድመ ኹኔታ ልታከብሪውና ልትወጂው ይገባሻል፡፡ አንቺ ሴት እንደ ኾንሽና ታላቅ የኾነ ዓላማና ግብ እንዳለሽ፥ ኾኖም ዓላማሽና ግብሽ የቤትሽ ራስ ሊኾን ከሚገባው ባልሽ የተለየ እንደ ኾነ ዕወቂ፤ ተረጂም፡፡ ባንቺ ዕድሜ ላይ ያሉት አንዳንዶች ኹለቱም ፆታዎች እኩል [ራስ ናቸው] ብለው የሚሰብኩትን አትስሚ፤ የጋብቻንም ግዴታ [ወይም ዋና ዓላማ] አስቢ፡፡ እነዚህን ግዴታዎች [ወይም ዓላማዎች] ስታውቂ የቤተሰብሽን ተግባራት ለማከናወን እንደ ምን ያለ ትዕግሥትና ጽናት እንደሚያስፈልግሽ ታውቂያለሽና፡፡ እንደ ሚስት እጅግ ጥንካሬን ገንዘብ የምታደርጊውም በዚህ መንገድ ነው፡፡

“ወንዶች እንዴት በቀላሉ የሚቈጡ መኾናቸውን በርግጥ ልታውቂ ይገባሻል፡፡ አይችሉም፤ ብዙ ጊዜም እንደ በረኻ አንበሳ ይኾናሉ፡፡ እንግዲህ ሚስት ጸንታ ልትቆምና የነፍስ ልዕልናዋን ልታሳይ የሚገባት በዚህች ቅጽበት ነው፡፡ አንበሳን የማስለመድ ሥራ መሥራት አለብሽ፡፡ አንበሳን የሚያስለምድ ሰው አንበሳ ሲያገሳ የሚያደርገው ምንድን ነው? ከየትኛውም ጊዜ በላይ ዝም ጸጥ ይላል፡፡ በጸጥታውና በርጋታውም የአንበሳውን ቊጣ ይቈጣጠራል፡፡ በርጋታና በለሆሳስ ኾኖ ያናግረዋል፤ ይደባብሰዋል፤ በቀስታ ያሻሸዋል፤ በጥቂት በጥቂቱም አንበሳው ቊጣውን ይተዋል፡፡

“ባልሽ ስሕተት ሲሠራ በፍጹም ልትነቅፊው፣ ልትንቂው ወይም ልታስነውሪው አይገባም፡፡ በተመሳሳይ መንገድ አንድ መሥራት ያለበትን ነገር ባይሠራና ከዚሁ የተነሣም ውጤቱ ደስ የማያሰኝ ቢኾን፣ ወይም እጅግ የምትፈልጊውና አግባብ ነው ብለሽ የምታስቢውን ባያደርግ እንኳን ባልሽን መናቅ ከአንቺ ልታርቂ ይገባል፡፡ ክፉዎች አጋንንት ዘወትር ቤታችሁን ለማፍረስና የጥንዶች መንፈሳዊ አንድነትን ለመበተን እንደሚሞክሩ ዕወቂ፡፡”

( #ከገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ ከትንሿ ቤተክርስቲያን መጽሐፍ የተወሰደ)
https://t.me/dnhayilemikael

# ይቀላቀሉ እና ይማሩ
https://t.me/dnhayilemikael
294 views10:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 05:58:18
ደህና አደራችሁ ?


እግዚአብሔር ይመስገን በሉ



https://t.me/dnhayilemikael
338 viewsedited  02:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 21:45:07 የወጣቶች ሕይወት (ሕይወተ ወራዙት)

በቀሲስ ሕብረት የሺጥላ
#ክፍል_1


ሕልመ ሌሊት ምንድነው ?

በዐፍላ የጉልምስና ወቅት አባለ ዘርዕ ወደ ሙሉ የዕድገት ደረጃ መድረስ ብቻ ሳይሆን መስራትም ይጀምራል ። በዚህ ጊዜ ከኀፍረተ አካል ዘርዐ ብእሲ (የወንድ ዘር ) ይወጣል ። ወንድና ሴት ግንኙነት በሚያደርጉበት ጊዜ ወደ ሴቲቱ ማኀፀን በመግባት ፅንስ እንዲፈጠር የሚያደርገው ይህ ፈሳሽ ንጥረ ነገር ነው ። ለዘር የበቁ ወጣቶች ዘር የሚወጣቸው በተለያየ መንገድ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ግን ተኝተው ሳለ በጠለቀ እንቅልፍ ሆነው ሕልም በሚያልሙበት ወቅት ነው ። ይህ ሲሆን በሳይንስ እንደ ጤናማ የተፈጥሮ ሂደት ይቆጠራል ። የዚህ አይነቱን ሕልም መፅሐፈ መነኮሳት በአንድ ስፍራ #ሕልመ_ጽምረት በሌላ ቦታ ደግሞ #መስቆርርተ_ሕልም ሲለው ይገኛል። ሕልሙን ያየው ሰው ደግሞ #ዝንየት መታኝ ወይም #ሕልመ_ሌሊት አገኘኝ ይላል

ሕልመ ሌሊት ኃጢአት ነውን ?

በጠለቀ እንቅልፍ ላይ ሳሉ የሚከሰት ሕልመ ሌሊትን እንደ ኀጢአት እንዲቆጠርና እንዳይቆጠር የሚያደርጉ የተለያዩ ሁኔታዎች አሉ ።ስለዚህ ሕልመ ለሊትን በጥቅሉ ኃጢአት ነው ወይም አይደለም ማለት አይቻልም ። እንደ ኃጢአት እንዲቆጠር የሚያደርጉ ሁኔታዎችን በጥቂቱ ለማየት ያህል

ሀ. አጋንንት የሰው ልጆችን በልዩ ልዩ መንገድ ክፋኛ ይዋጓቸዋል ። የሰው ልጆች ሲያንቀላፉ አጋንንት ግን ለቅጽበት እንኳን አያሸልቡም ። ያንቀላፋው ሰው እስኪነቃ ድረስ እንኳን አይጠብቁም ። አጋንንት የሰውን ልጅ በተኛበት ክፋ ክፋ ሕልም በማሳየት ይፈትኑታል ። አንድ ጊዜ የተራቆተ የሴት ገላ ፣ በሌላ ጊዜ ደግሞ እንደ ወንድና ሴት ግንኙነት ሲያደርጉ በምትሐት ያሳዩታል። በዚህ ጊዜ እርሱም በዝሙት ሐሳብ ይሳብና በሕልሙ ዝሙት ሲፈፅም ያድራል ። መፅሐፈ መነኮሳት "ሰይጣናት የሰውን ልጅ ቀን ቀን ክፋ ሐሳብ በማሳሰብና በማሰራት በሌሊት ደግሞ ዝሙት የሞላበት አስጸያፊ ሕልም በማሳየት ይዋጉታል " ይላል። በዚህ ጊዜ ሰይጣናት ያቀረቡለትን ረቂቅ ፈተና ከመቃወም ፣ ከመፀፀትና ከመቆጨት ይልቅ ደስ እያለው የሚያጣጥም ከሆነ ፤ በደስታ ስለ ዝሙት የሚያሰላስል ፣ የሚዳራ ፣ የሚዛለል ፣ ወደ ዝሙት ከሚያመሩ ማናቸውም ነገሮች የማይሸሽ ሰው እነዚህን ነገሮች ነቅቶ ሳለ ያልተቃወማቸውን ተግባራት በሕልሙ በፈፀማቸው ጊዜ በተግባር እንደ ፈፀማቸው ይቆጠራል ።ሌላው ከሥራ ብዛት ሕልም እንዲታይ ጠቢቡ ሰሎሞን[ " ሕልም በሥራ ብዛት ይታያል " በማለት የተናገረው ያስረዳል (መክ5:3) እንደዚሁም ሁሉ ከምኞት ብዛትም ሕልም ሊከሰት ይችላል። ክፋ ምኞት በሕልምም ማርከሱ አይቀርም ። ሐዋርያው ይሁዳ " እያለሙ ሥጋቸውን ያረክሳሉ " ያለው ለዚህ ይጠቀሳል ። (ይሁዳ 1:8) እንደሚታወቀው ነፍስ አትተኛም ። ስለዚህ ነፍስ በእንቅልፍ ልቤ ነው ብላ ማመካኘት አትችልም ። ነፍስ በረከሰ ሕልም ምክንያት ከተጠያቂነት ነጻ መሆን የምትችለው ሥጋ ከእንቅልፍ ውጭ በሚሆንበት ጊዜ ተግባረ ዝሙትን በመቃወምና በመጥላት ከእግዚአብሔር ጋር መሆኗን ስታስመሰክር ብቻ ነው ። ሌላው ሕልመ ለሊትን እንደ ኀጢአት የሚያስቆጥረው ሁኔታ አብዝቶ መመገብ ነው ። ጾም ለፅድቅ ስራ ሁሉ መሰረት እንደሆነው እንደዚሁም አብዝቶ መመገብ የኀጢአት ሁሉ መሰረት ነው ። "እህል ጉልበትን ያጠነክራል ተብሏልና ።ሰው ሁሉ ለቁመተ ስጋ ያህል ብቻ መመገብ ያሻዋል ። ከዛ ውጭ ግን አብዝቶ መመገብ "ሆዳቸው አምላካቸው " እንደ ተባለው ለህልመ ለሊት ያጋልጠናል ።
... ይቀጥላል ...

@dnhayilemikaelb
@dnhayilemikael
@dnhayilemikael
313 views18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 12:19:55 ሕይወተ ወራዙት / የወጣቶች ሕይወት
(በቀሲስ ሕብረት የሺጥላ)

መግቢያ

ወጣቶችና ፆሮቻቸው (የወጣቶች ፈተና
በቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አስተምህሮ መሰረት ምእመናን በ#5 መደብ ይመደባሉ ። ይህም መደብ "ፆታ ምዕመናን "ይባላል ። 5ቱ ፆታ ምዕመናን የሚባሉት ካህናት ፣ መነኮሳት ፣ አዕሩግ (አረጋውያን) ፣ ወራዙት (ወጣት ወንዶች ) እና አንስት (ሴት ወጣቶች) ናቸው ። አምስቱም ፆታ ምእመናን በየራሳቸው የሚቸገሩበት ዓቢይ ፈተና አለ

"ፆር " በመባል የሚታወቀው ይህ ዓቢይ ፈተና ነው ።የካህናት ፆራቸው ትዝህርት (ትዕቢት) ነው ፤ የመነኮሳት ፆር ስስት ሲሆን ፤ የአረጋውያን ፆራቸው ደግሞ ፍቅረ ንዋይ ነው ። ቀሪዎቹ ወጣት ወንዶች ሲሆኑ ዐቢይ ፆራቸው ዝሙት ነው ። የወጣት ሴቶች ዓቢይ ፆር ደግሞ ትውዝፍት (የምንዝር ጌጥን መውደድ ) ነው ። ይህ ማለት ግን ዋና ዋና ፈተናቸውን አንጓሎ ለመናገር ነው እንጂ እያንዳንዱ ፆታ ምዕመን የሚፈተነው በአንድ ነገር ብቻ ነው ማለት አይደለም ።" ሰውነቱ በደዌ የተጠቃን ሰው ጉንፋን እንኳን እንደሚያይልበት " እንዲሁ በዋና ፈተናው ድል የተደረገ ምዕመን ሌሎች ጥቃቅን ፈተናዎች ይረባረቡበታል

ነገር ግን ዋናውን ፆሩን ድል ካደረገ የሚመጡበትን ሌሎች ፈተናዎች በቀላሉ ድል ለማድረግ ይቻለዋል ። ወጣቶች ልዩ ልዩ ፆር (ፈተና) እንዳለባቸው ነገር ግን ዕድሜያቸው እየገፋ በመጣ ቁጥር ወጣትነታቸው ሲያልፍ የወጣትነት ፈተናቸውን አብሮ እንደሚያልፍ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ሲል ተናግሯል ። "ሥጋን ንዳድ ሌላም ልዩ ልዩ ደዌ በያዘው ጊዜ ምንም ብርቱ ቢሆን እንደሚደክምና ከበሽታው በዳነ ጊዜ ግን ኃይሉ እንደሚመለስለት እንደዚሁ ነፍስም በወጣትነት ወራት በደዌ ኀጢአት ትያዛለች

ትዕቢተኛነት ፣ ሥጋዬ ይድላው ማለት ፣ በፆታ መፈላለግና ይህን የመሳሰለ ብዙ የምኞት ጣዕም ያድርበታል ። የእርጅና ወራት በደረሰ ጊዜ ግን ፈቃደ ሥጋ ፈፅሞ ከሰውነት ይርቃል " ብሏል ። ስለዚህ ወጣትነታችንን በጥበብ እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኝ ሁኔታ ልናሳልፍ ይገባል ። የዚህ ፅሁፍ አላማም ፈተናዎቹን አውቀን እንዴት ማለፍ እንዳለብን መንገድ ማመላከት ነው ።

... ይቀጥላል ...

https://t.me/dnhayilemikael
https://t.me/dnhayilemikael
https://t.me/dnhayilemikael
329 views09:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 11:37:28
እስካሁ ስንቴ ንስሃ ገብታችሁ ታውቃላችሁ?
Anonymous Poll
45%
ገብቼ አላውቅም (ምክኒያታችሁን ንገሩኝ
24%
አንዴ ገብቻ አውቃለሁ
13%
ሁለቴ ገብቼ አውቃለሁ
5%
አራቴ ገብቼ አውቃለሁ
14%
ብዙ ግዜ ንስሐ ገብቼ አውቃለሁ
797 voters377 views08:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 14:59:45 #ክርስቲያን_የሆነ_ሰው_ሳያነብ_እንዳያልፍ!!!

#ስንት_ዓመት_ተማርን?

❖አሁን የምንሰራው ስራ ለሥጋዊ ኑሮ የሚሆን የሚጠቅም ነው በዚች ምድር ላይ ሳለን እንዳይርበን እንዳይጠማን እንዳይበርድን ኑሮአችን ለማመቻቸት እንወጣለን እንወርዳለለን
✟ ✥ከሕፃንነታችን ጀምሮ እንማራለን
ሶስት ዓመት ጊዜ ወስደን መዋእለ ሕፃናት ተምረናል
አስራ ሁለት ዓመት ጊዜ ሰጥተን 12 ክፍል ጨርሰናል(አቋርጠንም ያለን ልንኖር እንችላለን
አምስት ዓመት በላይ ጊዜ ሰጥተን በድግሪ በማስተር ተመርቀናል
ባጠቃላይ የሥጋ ሥራ ለመያዝ ከሃያ ዓመት በላይ ተምረናል
እንደዚህም ተምረን ስራ አጥተን በስራ ፍለጋ ደክመናል ወንድሜ(እህቴ) ሆይ አሁን ከ20 ዓመት በላይ የተማርነው ትምህርት ለስንት ዓመት ያሰራናል ?
ጡረታ እስክንወጣ ነው ከዛ በሇላ የተማርነው ትምህርት አያገለግለንም
ከ20 ዓመት በላይ ስንማር የፈተፈተነው ጊዜ እናስብ ጭንቀቱን ድካሙን እንቅልፍ ማጣቱን
ከትምህርት ቤት ለመድረስ የእግር ጉዞውን ሁሉ አንርሳ ያ ሁሉ ደክመን የተማርከው ስንሞት አይጠቅመንም
ሥጋችን መቃብር ሲገባ ምድራዊ እውቀታችን አብሮ ይቀበራል
በህይወት እያለን ጡረታ የምንወጣው መስራት አትችሉም ተብለን ነው
ከ20 ዓመት በላይ በተማርነው ትምህርት ብንሰራበት 30 ዓመት ቢሆን ነው ያም እድሜ ከታደለህ ነው።
ወንድሜ(እህቴ) ሆይ እስቲ ልጠይቃችሁ
ለሥጋችን ስራ ለመስራት ከ20 ዓመት በላይ ተምረናል
#ለነፍሳችን ስንት ዓመት ተማርን?
ለነፍሳችን የተማርነው ትምህርት ጡረታ የለውም
በሥጋ የተማርነው የመንግሥት ስራ ያስይዘናል
በነፍስ የተማርነው የእግዚአብሔር ስራ ያስይዘናል
የነፍስ ትምህርት ምን ይመስለናል ቃለ እግዚአብሔር ነው
✥#የእግዚአብሔርን ቃል በወር ስንት ሰዓት ተምረናል ?
✥በዓመት ስንት ቀን ይሆናል የተማርንበትም ጊዜ እስቲ እንደምረው?
✥ባጠቃላይ የተማርንበት ጊዜ እስክንሞትስ ስንት ዓመት ይሆናል?
✥ መቼም የሥጋውን የተምህርት ጊዜ አያክልም
✥በነፍስ የተማርነው ትምህርት ስንት ዓመት እንደሚያሰራልን እናውቃለን ?
✥ቁጥር የማይደርስበት ጊዜ ነው
ዘመናት አልፈነው እንሰራበታለን ለዘላለም ጡረታ አያወጣንም
✥እኛ ግን ይሄን ረስተናል ቀኑን ሙሉ ለሥጋችን እንሮጣለን ለነፍሳችን የምንማርበት ጌዜ አጥተናል በሚያልፈው ነገር እራሳችንን ቢዚ አድርገናል ::
✥ሁለት ሰኣት ቁጭ ብለን የተለያዩ ፊልም እናያለን 30 ደቂቃ ቁጭ ብለን ወንጌል መማር ይሰለቸናል::
✥ሁለት ሰአት ቆመን እያጨበጨብን ኳስ እንደግፋለን 2 ሰአት ቆመን ቅዳሴ ማስቀደስ አቅቶን በዕለተ ሰነበት ተኝተን እናረፍዳለህን
✥ልብ ወለድ ዝሙታዊ የሆኑ መጻፎችን በየቀኑ እናነባለን የእግዚአብሔር እስትንፋስ የሆኑ ቅዱሳት መጻሕፍን ለማንበብ ይሰለቸናል
✥ለዘፈን የከፈትነውን አፋችንን ለምስጋና ይዘጋል
✥ለሀሜት የሚፈጥነው አፋችን ለጸሎት ይዘገያል
✥ለእስፓርት የጠነከረው ጉልበታችን ለስግደት ይዝላል
✥ለስርቆት የሚላከው እጃችን ለምጽዋት አይታዘዝም
✥ወደጭፈራ ቤት የሚገሰግሰው እግራችን ወደ ቤተክርስቲያን ለመሄድ ይተሰሰራል
✥ሀሜት የሚሰማው ጆሮአችን ወንጌል ለመስማት ይደነቁራል
✥የዝሙት ሸቶ የሚያሸተው አፍንጫችን የመቅደሱን እጣን ሽታ ይፀየፈዋል
✥ጫት የለመደው አፋችን ሥጋውን እና ደሙን ረስቶአል
✥አልኮል የለመደው አፋችን ፀበሉን ተፀይፎታል
✥ ቂም የሚቋጥረው ልባችን ፍቅርን ረስቷል
✥ስናጣ እግዚአብሔርን እንቀርበዋለን ስናገኝ ግን እንርቀዋለን
ስንጨነቅ አምላካችንን እንጠራዋለን ስንደሰት እንረሳዋለን
✥ወንድሜ(እህቴ) ሆይ በህይወታችን አንቀልድባት
✥ከእኛ በፊት የነበሩት ተዋቂው አዋቂው ሁሉ የት አሉ? ✥መቃብር ውስጥ አይደሉምን ?
✟✥✟ይህንን አስበን ከፈጣሪያችን ጋር የሚያገናኝ ስራ እንስራ
✟✥✟ በአዲስ ዓመት አዲስ እቅድ ያስፈልገናል
✟✥✟ወደቤተ ክርስቲያን ሄደን ዘወትር ወንጌል እንማር
✟✥✟ ለማስቀደስ ለመፆም ለመስገድ እንትጋ
✟✥✟ ለንስሐ እንዘጋጅ ቅድሚያ ለነፍሳችን ሁሉን ነገር እናድርግ
❖አንደበታችን ለጸሎት ይትጋ
❖እጅአችን ለምጽዋት ይዘርጋ
❖ልባችን ለምህረት ይነሳሳ
❖ሥጋውን እና ደሙን ለመቀበል እንወስን

✥ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔም ጸልዩ!
✥"ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን

#ሌሎች_እንዲያነቡትና_እንድማሩበት_አስተማሪ_ሆኖ_ካገኛችሁ_ሼር_ያድርጉ!
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@dnhayilemikael
@dnhayilemikael
@dnhayilemikael
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══
4.9K views11:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 20:37:55 የአባ ዘወንጌል የትንቢት እውነታዎች
የኖኅ መርከብ መድረሻ
የትንቢቱ ፍፃሜዎች
የ666 ደባ በኢትዮጵያ ላይ
,መጽመፈ ሔኖክ
የዕፀ መሰወር ጥናታዊ ፁፍ
ታቦተ ፅዮን
ነጋዴው ታምሪን

open.........open .........open
Open........"open .........open
Open.........open...........open
Open........open............open
407 views17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 19:25:49 አባታችን ሆይ እንዴት ትላለህ?

እንደ ልጅ ካልኖርህ እንዴት "አባት" ትለዋለህ?
ሌላውን ጠልተህ ራስ ወዳድ ከሆንክ እንዴት አባት "አችን" ብለህ በአንድነት ትጠራዋለህ?
ምድራዊ ነገር ብቻ እያሰብህ እንዴት "በሰማያት የምትኖር" ትለዋለህ?
ልብህ ከእርሱ ርቆ በአንደበትህ ብቻ እየጠራኸው "ስምህ ይቀደስ" እንዴት ትለዋለህ?

ሥጋዊና መንፈሳዊውን እየቀላቀልህ "መንግሥትህ ትምጣ" ለምን ትለዋለህ?
መከራን በጸጋ የማትቀበል ከሆነ "ፈቃድህ ይሁን" ለምን ትላለህ?
ለራስህ ሆድ እንጂ ለተራቡት ግድ የማይሰጥህ ከሆነ ለምን "እንጀራችንን ሥጠን" ትላለህ?

በወንድምህ ላይ ቂም ይዘህ "እኛም የበደሉልን ይቅር እንደምንል" እንዴት ትላለህ?
የኃጢአትን አጋጣሚዎች ሳትሸሽ "ወደ ፈተና አታግባን" እንዴት ትላለህ?
ክፉን ለመቃወም አንዳች ሳታደርግ "ከክፉ አድነን" እንዴት ትላለህ?

ጸሎቱን ከልብህ ሳትሰማውስ እንዴት አሜን ትላለህ?

#ዲያቆን_ሄኖክ_ኃይሌ
ቻነላችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/dnhayilemikael
199 views16:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ