Get Mystery Box with random crypto!

አድኅነነ እግዚኦ እስመ ሃልቀ ሔር

የቴሌግራም ቻናል አርማ dnhayilemikael — አድኅነነ እግዚኦ እስመ ሃልቀ ሔር
የቴሌግራም ቻናል አርማ dnhayilemikael — አድኅነነ እግዚኦ እስመ ሃልቀ ሔር
የሰርጥ አድራሻ: @dnhayilemikael
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.11K
የሰርጥ መግለጫ

#መሰረታዊ_የቤተክርስቲያን_ክርስቲያን_ትምህርት /
#የተለያዩ_ተከታታይ_ትምህርት '
#ስንክሳር_የቅዱሳን_ገድል_በየዕለቱ !
#ስዕለ_አድህኖ !
#ምስባክ
#የየበአላቱ_ዋዜማና_ሥርተ_ማህሌት
#መዝሙር
#ግጥም
#ለመናፍቃን_ጥያቄ_መልስ
እና የተለያዩ የቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ
ሌሎች መንፈሳዊ ጽሁፎች
ይለቀቁበታል
Administration

@zearsema_dn

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-13 04:35:00
" የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ፥ እንደ ሰዶም በሆንነ እንደ ገሞራም በመሰልነ ነበር። "
(ትንቢተ ኢሳይያስ 1:9)


ይህቺ ለመዳናችን ምክንያት የሆነች ዘር ዛሬ የተጸነሰችበት ቀን ነ ው
እንኳን ለንጽህተ ንጹሃን ቅድስተ ቅዱሳን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለጽንሰት በአል በሰላም አደረሳችሁ


በረከቷ አማላጅነቷ ረድኤቶ አይለየን
ፍቅሯ በልባችን
ጣዕሟ በልባችን
ይደርብን
አሜን አሜን አሜን



https://t.me/dnhayilemikael
404 viewsedited  01:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 21:14:06 #ነሐሴ ሰባት ጽንሰታ
#ለማርያም_ድንግል


#ጴጥርቃ እና #ቴክታ የሚባሉ ሰዎች በኢየሩሳሌም በአንድነት ተጋብተው ይኖሩ ነበር፡፡ እነዚህም በእግዚአብሔር የሚያምኑ የተወደዱ ጻድቃን ደግ ሰዎች ነበሩ፡፡ እነዚህም ሰዎች በእግዚአብሔርም በሰውም ዘንድ የተመሰከረለላቸው ባለጸጎች ነበሩ:: ነገር ግን የሚወርሳቸው ልጅ አልነበራቸውምና መካን ነበሩ፡፡
✣ ✣
አንድ ቀን ጴጥርቃም ቴክታን እህቴ ሆይ ይህን ሁሉ የሰበሰብነውን ገንዘባችንን ምን እናደርገዋለን ልጅ የለን የሚወርሰን ፤ አንቺም መካን ነሽ እኔም ካንቺ በቀር ሌላ ሴት አላውቅም አላት፡፡ እርሷም ወንድሜ ሆይ አምላከ እስራኤል ለእኔ ልጅ ቢነሳኝ አንተም እንደኔው ሆነህ ትቀራለህን? ከሌላ ደርሰህ ውለድ እንጂ ብላ ብታሰናብተው እንደዚህ ያለ ነገር እንኳንስ ላደርገው በልቦናዬ እንዳላስበው አምላከ እስራኤል ያውቅብኛል አላት እሷም አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን የሚያውቅ የለም ትላንትና ማታ በህልሜ #ነጭ ጥጃ ከማህጸኔ ስትወጣ ያችም ነጭ ጥጃ ሌላ #ነጭ ጥጃ ስትወልድ እንዲሁ እስከ #7ት ትውልድ ሲዋለድ ሰባተኛይቱ ጨረቃን ስትወልድ #ጨረቃዋም #ፀሐይን ስትወልድ አየሁ አለችው::
✣ ✣ ✣
እርሱም በጠዋት ከህልም ፈቺ ዘንድ ሂዶ የነገረችውን ሁሉ ነገረው፡፡ ያም ህልም ፈቺ እግዚአብሔር በምህረቱ አይቷችኋል በሳህሉ መግቧችኋል 7 አንስት ጥጆች መውለዳቹ 7 ሴቶች ልጆች እና የልጅ ልጆች ትወልዳላቹ ከቤታቹ ሰባተኛይቱ #ጨረቃ መውለዷ ከሰው የበለጠች ከመላእክትም የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላችሁ #የፀሐይ ነገር ግን አልታወቀኝም አለው፡፡ እርሱም የነገረውን ሁሉ ሄዶ ነገራት እርሷም እንጃ አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን ማን ያውቃል ብላ ዝም አለች:፡
✣ ✣ ✣
ከዚያም ፀንሳ ሴት ልጅ ወለደች፡፡ ስሟንም ሄሜን ብለው አወጡላት፤ ሄሜንም አድጋ ለአካለ መጠን ስደርስ አጋብተዋት ሴት ልጅ ወለደች በስምንተኛ ቀኗም ዴርዲ ብለው ስም አወጡላት ፤ #ዴርዲም አድጋ እንዲሁ ሴት ወለደች እና #ቶና አለቻት፤ቶናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሲካር አለቻት #ሲካርም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሴትና አለቻት፤ #ሴትናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ# ሄርሜላ አለቻት ፤ ሄርሜላም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ንጽህት ቅድስት ክብርት የምትሆን እመቤታችንን የምትወልደችውን #ሃናን ወለደች:: ከጴጥርቃና ከቴክታ የተወለዱ 67 ወንዶች ልጆች አሉ የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ትውልድ ለመቁጠር ትንቢት አልተነገረላቸውም ሱባኤ አልተቆጠረላቸውምና አልተፃፈም፡፡ ይህቺም ሃና በስርዓት በቅጣት አደገች፡፡ ለአእምሮ ስትበቃ አካለ መጠን ስትደርስ ከቤተ መንግስት ወገን ከነቅዱስ #ዳዊት ወገን ከሆነው ከቅዱስ #እያቄም ጋር አጋቧት::
✣ ✣ ✣
እነዚህ ቅዱሳን ኢያቄም እና ሃና በአንድነት ተጋብተው ሲኖሩ ልጅ አጡ፤ ከእለታት አንድ ቀን ወደ ቤተ እግዚአብሔር ሂደው ሲፀልዩ ሲያዝኑ ዋሉ፡፡ ሃዘናቸው እንዴትስ ነው ቢሉ ፡-
ኢያቄም:-"አቤቱ ጌታዬ ያባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለሁ አትጣለኝ አትናቀኝ ፀሎቴን ስማኝ ፈቃዴን ፈጽምልኝ፤ ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የሚሆን የተባረከ ወንድ ልጅ ስጠኝ" ብሎ ሲለምን ዋለ:፡
ሃናም በበኩሏ "አቤቱ ጌታዬ የአባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለሁ፤ ስማኝ ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የምትሆነኝ የተባረከች ሴት ልጅ የማህፀኔን ፍሬ ስጠኝ" ብላ ስትለምን ዋለች፡፡ እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲጸልዩ ውለው ርግብ ከልጆቿ ጋር ስትጫወት አይታ አቤቱ ጌታዬ ለዚች ግእዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ ምነው ለኔ ልጅ ነሳኸኝ ብላ ምርር ብላ አለቀሰች፡፡ እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲፀልዩ ውለው ከዘካርያስ ከሊቀ ካህናቱ ሄደው አቤቱ ጌታችን ሆይ ወንድ ልጅ ብንወልድ ተምሮ ቤተ እግዚአብሔርን አገልግሎ እንዲኖር እንሰጣለን፤ ሴት ልጅም ብንወልድ ማይ(ውሃ) ቀድታ መሶብ ወርቅ ሰፍታ መጋረጃ ፈትላ ካህናትን አገልግላ እንድትኖር እንሰጣለን ብለው ስዕለት ገቡ:: ዘካርያስም እግዚአብሔር ጸሎታችሁን ይስማችሁ ስእለታችሁን ይቀበልላችሁ ጻህቀ ልቦናችሁን ይፈጽምላችሁ ብሎ አሳረገላቸው።
✣ ✣ ✣
ከዚያም በኋላ ቅድስት ሃና እና ቅዱስ እያቄም ዕለቱን ራእይ አይተው ነገር አግኝተው አደሩ፡፡ ራእዩም እንዴት ነው ቢሉ ኢያቄም 7ቱሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ አላት ፤ ወፍ የተባለው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ፤ ነጭነቱ ንጽሐ ባህሪው ነው ፤ ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ ማለቱ ፤ የኢያቄምን ( የሰውን) ባህርይ ባህርይ እንዳደረገው እወቅ ሲል ነው ፤ 7ቱ ሰማያት የተባሉ የጌታችን ልዩ ልዩ ባህርይው፤ ምልአቱ፣ ስፍሃቱ፣ ርቀቱ፣ ልእልናው፣ ዕበዩና መንግስቱ ናቸው፡፡
✣ ✣ ✣
ሃናም እኔም አየሁ አለችው፤ ምን አየሽ ቢላት፡፡ ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማሕጸኔ ስትተኛ አየሁ አለችው:: ርግብ የተባለች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት:ነጭነቱ ንጽህናዋ : ቅድስናዋ ድንግልናዋ ነው፡፡ ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ አየሁ ማለቷ ብስራተ ገብርኤልን በጆሮዋ ሰምታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችንን መጽነሷን ነው፡፡ ይህንኑም ራእይ ያዩት ሐምሌ 30 ዕለት ነው::
✣ ✣ ✣
እነሱም እንዲ ያለ ራዕይ ካየን ነገር ካገኘን ብለው ዕለቱን በሩካቤ ሥጋ አልተገናኙም፤ ፈቃደ እግዚአብሔር ቢሆን ብለው አዳምንና ሄዋንን ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሏት ብሎ ያበሰረ አምላክ ለኛስ ይልክልን የለምን? ብለው ዕለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ 7ቀን ድረስ ለየብቻቸው ሰነበቱ፡፡ ነሐሴ ሰባት በሰባተኛው ቀን ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላቹህ ብሎ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ለሃና ነገራት በፈቃደ እግዚአብሔር በብስራተ መልአክ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እሁድ ዕለት #ነሐሴ_7 ቀን ተፀነሰች፡:
✣ ✣ ✣
እመቤታችን ከተፀነሰች በኋላ አይሁድ ቀንተው ተነሱባቸው ቅናቱ እንዴት ነው ቢሉ፡፡ ሳሚናስ የሚባል የጦሊቅ ልጅ ከኤዶቅ ካጎቱ ቤት ሄዶ ሞተ እነርሱም እንቀብራለን ብለው ባልጋ ይዘው ሲሄዱ ከመንገድ አሳረፉት ፤ የሃናም የአጎቷ ልጅ ነበርና ለማልቀስ ብትደርስ ዘመዶቿ ሁሉ ተሰብስበው ሲላቀሱ ቆዩአት ፤ እርሷም አብራ እየዞረች ስታለቅስ ጥላዋ ቢያርፍበት መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ብድግ ብሎ ተነስቶ ስብሃት ለኪ ማርያም እሙ ለፀሃየ ጽድቅ ለአብ ሙሽራው ለወልድ ወላዲቱ ለመንፈስ ቅዱስ ጽርሃ ቤቱ ተፈስሂ ደስ ይበልሽ ብሎ ሰገደላት፤አይሁድ ከዛ ነበሩና ምነው ሳሚናስ ምን አየህ? ምን ትላለህ? ቢሉት ከዚች ከሃና ማህፀን የምትወለደው ሕፃን ሰማይ ምድርን እመቅ አየርን የፈጠረ አምላክን ትወልዳለች እያሉ መላእክት ሁሉ ሲያመሰግኑአት ሰማኋቸው እኔንም ያነሳችኝ የፈወሰችኝ ያዳነችኝ እርሷ ናት አላቸው ፤ በል ተወው ሰማንህ ብለው ቅናት ጀመሩ::
እመቤታችን እግዝትእነ ማርያም በተፀነሰች በ9 ወር ከአምስት ቀን የግንቦት መባቻ ዕለት ግንቦት 1 ተወለደች::

https://t.me/dnhayilemikael
473 views18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 17:03:25 Watch "ተሰምቶ የማይጠገብ ''የብርሃን እናት-እመብርሃን'' የተሰኘ አዲስ ዝማሬ➤በዘማሪት እምነ ሙሉጌታ @Rama Tube ll ራማ ቲዩብ Zemari Tadewos" on YouTube
https://youtube.com/clip/Ugkxf71DEswAm1GCrfQ-pQKtmQMc4hzNzRRH
2.8K views14:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 09:45:18 የጾም ትርጉም በቤተ ክርስቲያን

የቤተ ክርስቲያናችን የሥርዓት መድብል የሆነው ፍትሐ ነገሥት ጾምን እንዲህ ይተረጉመዋል፡-

ጾምስ በታወቀው ዕለት፣ በታወቀው ሰዓት ሰው ከምግብ የሚከለከልበት መከልከል ነው፡፡

አንድም ጾም ሰውን ከምግብ መከልከል ነው፡፡

ይህም ኃጢአቱን ለማስተሰረይ፣ ዋጋውን ለማብዛት እርሱ ወዶ ፈቅዶ ሕግን ለሠራለት እየታዘዘ የፈቲውን ኃይል ያደክም ዘንድ ሥጋን ለነባቢት ነፍስ ትታዘዝ ዘንድ ማዘጋጀት ማብቃት ነው፡፡
ፍት.ነገ.ፍት. መ. አንቀጽ15፣564

በዚህ መሠረት ጾም ማለት ከጥሉላተ መባልዕት /ሥጋ ፣ ቅቤ፣ ወተት፣ እንቁላል እንዲሁም የአልኮል መጠጦች/ መታቀብ ነው፡፡

ጾም ከክፉ ሐሳብ፣ ከክፉ ሥራ ማሰብም መራቅም ነው።

ጾም እግርና እጅን፣ ልብንና ሕሊናን ከመጥፎ ቦታዎች ማቀብ /ወደ መጠጥ ቤት፣ ጭፈረና ዘፋኝ ቤት፣ ጥንቆላና ባዕድ አምልኮ ከመትወስድ መንገድ የምትከለክል ናት።

ጾም ከመንፈሳዊ ተጋድሎዎች አንዱ ነው፡፡

ጾም ለፈቃደ ሥጋም መንፈሳዊ ልጓም ነው፡፡

ጾም ሰው ፈቃደ ሥጋውን እየገታ ነፍሱን የሚያለመልምበት ስንቅ ነው፡፡

ጾም ቁስለ ነፍስን የምትፈውስ፣ ኃይለ ፍትወትን የምታደክም፣ የበጎ ምግባራት ሁሉ መጀመሪያ ናት።

ጾም ጸጋ እግዚአብሔርን የምታሰጥ፣ የጽሙዳን ክብራቸው፣ የድንግልና የንጽሕና ጌጣቸው መገለጫቸው፣ የጸሎት ምክንያት /እናት/፣ የእንባ መገኛ ምንጭ፣ አርምሞን የምታስተምር፣ ለበጎ ሥራ ሁሉ የምታነቃቃ፣ ሰውነትን በእግዚአብሔር ፊት በማዋረድ ትኅትናን ገንዘብ ለማድረግ የምትረዳ መድኃኒተ ነፍስ ናት፡፡


@https://t.me/dnhayilemikael
586 views06:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 09:59:19 ቅበላ_ዓላማው_ምንድን_ነው?
#አንብቡት

ስለ ቅበላ ያለን አመለካከት በልማዳችን ውስጥ የተንሸዋረረ ነው
ከጾም ጋር ተያይዞ በሕዝበ ክርስቲያኑ ዘንድ ከሚፈጸሙ ተግባራት መካከል በአጽማት መግቢያ የሚደረገው የአቀባበለ ሥነ ሥርዓት ነው። ይህ ሥርዓት በራሱ መጸሐፍ ቅዱሳዊ ይዘት ያለውና በጥንታዊቷ ቤተክርስቲያንም የተለመደ ትውፊታዊ ቅብብሎሽ ያለው ሥርዓት ነው። ይህ ግን አሁን ከምንፈጽመው የቅበላ ሥርዓት የተለየ ነበር። ጥቂት ማሳያዎችን እንመልከት።

https://t.me/dnhayilemikael

➪ በመጸሐፍ ቅዱስ አይሁድ ቀዳሚት ሰንበት ከመግባቷ በፊት በዋዜማው የተለየ አቀባበል ያደርጉ ነበር። ዓርብ ፀሐይ ሲገባ ካህኑ ደውል
ይደውላሉ አሊያም በቤት ያለ የቤቱ አባወራ የሰንበት
መግቢያ ሰዓት መቃረቡን ድምጽ በማሰማት ያሳውቃል፡፡ በአካባቢው ያሉ ሁሉ ይሰበሰባሉ፡፡ በአንድ ላይ ሆነው ወደ ፀሐይ መውጫ ይሰግዳሉ፡፡ ጸሎት ይደረጋል፡፡ ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ እስራኤል፣አሥርቱ ቃላት ሌሎችም ንባባት ይደገማሉ፡፡ ማብራት ተይዞ “ዕለተ ሰንበት እንኳን
ደህና መጣሽ” ብለው ያከብሯታል፡፡ ከሦስት ሰዓት በኋላእራት ይበላሉ፡፡ ሌሊቱን በሙሉ እግዚአብሔርን
ሲያመሰግኑ ያድራሉ፡፡" ከዚህም ጎን ለጎን ከግብጽ ባርነት መውጣታቸውን ምክንያት በማድረግ ለሚያከብሩት የፋሲካ ሏዓል በታዘዞት መሠረት ጠቦት አዘጋጅተው አቀባበል ያደርጉለት ነበር። ኦዘጸ 25:12

❷➪ ትክለኛው ቅበላ ግን ከሕሊና ዝግጅት ጋር ተያያዥነት ያለው ነው። ቀደምት አበው አጽዋማት ከመግባታቸው በፊት ለቤተመቅደስ አገልግሎት የሚሆኑ መገልገያዎችን ያዘጋጃሉ እነርሱም እራሳቸውን ለአገልግሎት ያዘጋጃሉ። ምእመኑም ሱባኤውን የሚያሳልፍበትን ቦታ መርጦ ይጠብቃል ንሰሐ ገብቶ እራሱን ለቅዱስ ቁርባን ያዘጋጃል። የቀማውን ይመልሳል የበደለውንም ይክሳል። ማጠናቀቅ ያለበትን ተግባረ ሥጋ ፈጽሞ ይጠብቃል። በጥቅሉ በጾም ወቅት ሊሟሉ የሚገቡ ውጫዊና ውስጣዊ ዝግጅቶችን በዋዜማው ይፈጽማሉ። ካገኙ በመጠኑ መቀበያ የፍስክ ምግብ ይመገባሉ ካላገኙ ግዴታ ስላልሆነ ጥሬ ቆሬጥመው ውሀ ተጎንጭተውም ቢሆን ይቀበሉታል።

❸➪ አሁን ያለው ደግሞ ፍጹም የተለየ አቀባበል ነው
። በጾሙ ላይ ተሳትፎ የሌለውም ያለውም በጠቅላላ የህሊና ዝግጅት የለውም አቀባበል ሲባል ቀጥታ ግንኙነት ያለው ከመብላትና ከመጠጣት ጋር ይመስለዋል። በየቦታው ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሲበላ ሲጠጣ ሲያልፍም ወዳልተገባ ሥጋዊ ስሜት ውስጥ ይገባል። ብዙ ነዳያን የሚቀምሱት ባጡበት ዘመን ከገደብ ያለፈ የአመጋገብ ሥርአት በቅበላ ወቅት የተለመደ ነው። ይህ ከክርስትናው ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለውም ሰው ለፈቃደ ስጋው ሲያደር የፈጠረው እንጂ። እግዚአብሔር ለቅበላው ስለበላነው እና ስላልበላነው ጉዳይ ሳይሆን ሚያሰበው የእኛ በኃጢአት መኖር መሆኑን ልብ እንበል። ስጋ በልቶ የተቀበል ቆሎ በልቶ ከተቀበለው ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ብልጫ የለውም። ከሁሉ ሚያሳዝነው በቅበላውም በፍቺውም የፍስከ ምግቦች ለመብላት የሚሰለፉት ማይጾሙት መሆናቸው ነው። ስለዚህ በቅበላ ጊዜ "የግድ እነዚህን ካለበላችሁ የሚል ህገ የለም ያገኘም በመጠኑ እና በማያስነውር መልኩ ቢመገብም ነውር የለውም። በአጽማት ስጋ መብሊት አለመብላት ግዴታ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ ዝግጅቶች ምናደርግበት ነው።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን ይቆየን

ተቀላቀሉ ቴሌግራም➘ https://t.me/dnhayilemikael
3.3K views06:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 20:19:14 ጾመ ፍልሰታ

ፍጹም ያላደፉ ~ እንከን አልባ ገጾች
ከበረድ የነጹ ~ ጸአዳ ፍጥረቶች
በቤትህ ሊፈሱ ~ ከመቅደሱ ደጆች
ይኸው ከዋዜማው~ ታዩ የአንተ መልኮች

አይገርም ፍልሰታ ~ ለእነሱ የተባለች
በአዋጅ ተደንግጋ ~ ተሰድራ ያለች
የሆነች ይመስል ~ ወላጅ ቀርቶ ኋላ
እነሱ ፊት ናቸው ~ ከኪዳኗ ጥላ

እንኳንም ግን መጡ ~ ይሙሉ በመቅደሱ
በልማድ ባልሆነ ~ በዕውቀት ይታደሱ

ከወዲሁ እንኳን አደረሰን ልጆቻችን ብቻ ሳይሆኑ እኛም የምንከብርበት ከነፍስ ሞት የምናመልጥበት የጾም ሳምንታት ይሁንልን

የጾም ጊዜውን የበረከት የጸሎት የስገደት ከአምላካችን ጋር የምንነጋገርበት የምንሻውን የምናገኝበት ችግራችን የምፈታበት ከኃጢአት ውጭ የልባችን መሻት የምናገኝበት ግዜ እንዲሆንልን የእረሱ መልካም ፈቃድ ይሁንልን


አግዚአብሔር አምላክ በሰላም አስጀምሮ በሰላም በደስታ ያስፈጽመን
የእሜቤታችን ፍቅሯ በረከት ረድኤቷ አይለየን
1.0K views17:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 15:36:21 Watch "ተሰምቶ የማይጠገብ ''የብርሃን እናት-እመብርሃን'' የተሰኘ አዲስ ዝማሬ➤በዘማሪት እምነ ሙሉጌታ @Rama Tube ll ራማ ቲዩብ Zemari Tadewos" on YouTube


4.4K views12:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 21:11:01 ሱባዔ ምንድ ነው

አንብቡት አጭር ነው

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ሱባኤ በሰዋሰው ትርጉሙ "ሰባት"ማለት ሲሆን በመንፈስ አተረጋጎም አንድ ሰው ከዚህ ቀን እስከ ዚህ ቀን በጸሎት ከፈጣሪየ ጋር እገናኛለሁ ብሎ የሚያቅደው መንፈሳዊ ዕቅድ ነው ፡፡ ሰባት ቁጥር በእስራኤላውያን ዘንድ በሥራም በቃልም የሚገለጥ ፍጹም ቁጥር ነው፡፡ ለምሳሌ ፦ ፈጣሪ አለማት እግዚአብሔር በሰባተኛው ቀን ሥነ ፋጥረትን ከመፋጠር ማረፋ ፥ለጸሎት የሚተጉ ምዕመናን በቀን ለሰባት ጊዜ ማመስገናቸው የሰባት ቁጥር ፋጹምነት ያመለክታል ፡፡ [ዘፍ 2*2 , መዝ 118*164 ] አንድ ሰው 7 ቀናት ቢጾም "አንድ ሱባኤ ጾመ" ይባላል ፡፡

☞ ሱባኤ መቼ ተጀመረ?

የተጀመረው ከውድቀት በሓላ በመጀመርያው ሰው በአዳም ነው፡፡ ቅዱሳን መላእክት አዳምን ጸሎት እንዳስተማሩት የቤተ ክርስቲያናችን መዛግብት ያስረዳሉ በምላሹም ከልጅ ልጅህ ተወልጄ ስጋን ለብሼ ከ 5 ቀን ተኩል በኋላ አድንሃለሁ የሚለውን ቃል ኪዳን የሰማው ሱባኤ በመግባቱ ነው፡

https://t.me/dnhayilemikael

☞ ሱባኤ ለምን ?

የሰው ልጅ ሓጢአት በሚስማማው የሥጋ ሰውነቱ ዘወትር ፈጣሪውን ይበድላል ፡፡ በፈፀመው በደል ኀሊናው ይወቅሰዋል ይጸጸታል ፡፡በመጀመርያ ደፋሮ በሰራው ሀጥያት በኋላ ይደነግጣል ይህ በማንኛውም ሰብአዊ ፋጥረት ኀሊና ውስጥ የሚፈራረቅ ክስተት ነው ፡፡ በዚህ ግዜ የፈጣሪውን ይቅርታ ለማግኝት ያስባል ይተክዛል፡፡ ሰው በደፋርነቱ የኃያሉን አምላክ ትእዛዝ ተላልፎ አለም ሲያስጨንቀው ሸክሙን የሚያቃልልበትና የሚያስወግድበት መንፈሳዊ ጥበብ ከቸሩ ፈጣሪ ተሰጥቶታል፡፡ ይህውም በጥቂት ድካም ሥጋ ያልተወሰነ ጸጋ እግዚአብሔር የሚያገኝበት ሥርዓት ሱባኤ ነው፡፡

➊ እግዚአብሔርን ለመማጸን

ማንኛውም ሰው ሱባኤ ሲገባ በቁርጥ ወደ ፈጣሪው የሚያቀርበው ተማፅኖ ሊኖረው ይገባል ፡፡ ምንም የምንጠይቀው ( የምንማፀነው) ነገር ሳይኖር ሱባዔ ብንገባ የምናገኝው መልስ አይኖርም ፡፡ ስለዚህ ሱባኤ ከመግባታችን በፊት ፦ሱባዔ የምንገባው ለምንድን ነው ? በማለት እራሳችንን መጠየቅ ይኖርብናል ፡፡

➋ የቅዱሳንን በረከት ለመሳተፍ

ቅዱሳን አባቶችና እናቶች የተጋደሉትን ተጋድሎ በማዘከር ቃል ኪዳን በተሰጣቸው ገዳማትና አድባራት የሚገባ ሱባኤ የቅዱሳን በረከት ተካፋይ ያደርጋል፡፡ በጾመ ነብያት የነብያትን ፤ በጾመ ሀዋርያት የሀዋርያትን ፤በጾመ ፋልሰታ የእመቤታችንን በረከት ለመሳተፋ ሱባኤ መግባት የነበረ ነው፡፡

☞ የሱባኤ አይነቶች

1 የግል ሱባኤ ( ዝግ ሱባኤ) ፦ አንድ ሰው ብቻውን አመች ቦታ ማንም ሳያየው በግሉ የጸሎት በአቱን ዘግቶ በሰቂለ ኀሊና ሆኖ ፈጣሪው ብቻ እንዲያየው በኀቡዕ የሚፈፅመው ሱባኤ ነው ፡፡
2 ,የማህበር ሱባኤ ፦ ካህናት ምዕመናን ወንዶች ሴቶች ሽማግሌወች ፤ወጣቶች ፤በአንድ ሆነው በቤተ ክርስትያንና አመች በሆኑ ቦታወች ሁሉ ተሰብስበው የሚገብት ሱባዔ ነው፡፡
3 , የአዋጅ ሱባዔ ፦ በሀገር ላይ ድንገተኛ አደጋ ፤ አባር ቸነፈር ጦርነት ሲነሳ እንዲሁም በማህበረ ምዕመናን ላይ አስጊ የሆነ መቅሰፋት ሲከሰት እግዚአብሔር መዓቱን በምህረት ቁጣውን በትዕግስት እንዲመልስ የሚያዝ የሱባዔ አይነት ነው፡፡


☞ቅድመ ዝግጅት
ሱባኤ ከመግባታችንም ሆነ ከገባን ግዜ እንዲሁም ከጨረስን በኋላ ምእመናን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ይገባናል ፡፡

➊ ሱባኤከመግባት አስቀድሞ

፩ በመጀመርያ ሱባዔ የምንገባበትን ምክንያት ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል ፡፡
፪ ሱባኤ ለመግባት የወሰንበትን ምክንያት ከለየን በኋላ ምክንያታችንን ይዘን የንስሃ አባታችንን ማማከር ያስፈልጋል፡፡
፫ ለምን ያህል ቀናት መቆየት እንዳለብን መወሰን ያስፈልጋል ፡፡ሱባኤ ከዚህ እስከዚህ እቆያለሁ ብለን ዕቅድ የምንይዝበት ነው፡፡
፬ ወቅትና ቦታ መምረጥ ተገቢ ነው፡፡በቤተ ክርስቲያናችን በአብዛሀኛው ግዜ ሱባኤ የሚገባው በአጽዋማት ወቅት በመሆኑ ይህንን መለየት ነው ፡፡ምክንያቱም በጾም ወቅት ብዙ አባቶች ጸሎት የሚይዙበት ስለሆነ ፀሎታችን ከእነርሱ ጋር አብሮ ያርግልናልና ነው፡፡ እዚህ ላይ በማንኛውም ግዜ ሱባኤ አይያዝም ለማለት አይደለም በማንኛውም ግዜ ፈተና ያጋጠመው ሰው ሱባዔ ሊይዝ ይችላል፡፡

➋ በሱባኤ ግዜ

ሀ. በጸሎት ሰአት ዓምድና ግድግዳ ሳይደገፉ መቋሚያ ሳይዙ በሁለት እግር ቀጥ ብሎ በመቆም መጸለይ ይኖርብናል፡፡ እንዲሁም ፊትን ወደ ምስራቅ መልሶ መቆም ወደ ግራ ወደ ቀኝ አለመዟዟር በሰቂለ ህሊና ኾኖ መጸለይ ይገባል፡፡
ለ . በቅደም ተከተል መፀለይ ይገባል በመጀመርያ አአተብ ከሚለው ተጀምሮ አቡነ ዘበሰማያትን ጠቅሶ ጸሎተ ሀይማኖትን መጨረስ ፡፡ሰግዱ እና ስለ መስቀል በሚያነሳው ላይ እየሰገዱና እያማተቡ መጸለይ ፡፡ በማስቀጠል አቡነ ዘበሰማያት ፤መዝሙረ ዳዊት ውዳሴ ማርያም ሌሎችንም ማስከተል ከዚያ 41 ግዜ ኪራላይሶ ይባላል ፡፡
ሐ. በሱባዔ ግዜ ከተሐራሚው የሚጠበቀው ነገር ሐጢአቱን እያሰበ ማዘን ማልቀስ ለእያንዳንዱ በደል ማልቀስ ማዘን ይገባዋል ፡፡
መ. በመጨረሻም ሱባዔ የገባው ሰው ሱበዔውን ሳይጨርስ ወይም አቋርጦ ከማንኛውም ሰው ጋር ፈፅሞ መገናኝት የለበትም ፡፡

➌ ከሱባዔ በኋላ

ላቀረብነው ተማፅኖ እግዚአብሔር የሚያደርግልንን ነገር መጠበቅ ይኖርብናል ፡፡ "ሱባዔ" የገባ ሰው ሁሉ ራዕይ ላያይ ይችላል፡፡ምክንያቱም የእግዚአብሔር መልስ አሰጣጥ ለማንም ግልጽ አይደለም ፡፡ ከሱባዔ በኋላ መጀመሪያ የምናገኝው የህሊና ሰላም ነው ፡፡ ይህ ትልቅ የአምላክ ስጦታ ነው ፡፡ ከዚህ ባሻገር ሱባኤ ገብተን ያሰብነውን ካላገኝን ዳግመኛ ተዘጋጅተን እስከ መጨረሻው ሰዓት በመማፀን መጽናት ይኖርብናል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን ይቆየን


ተቀላቀሉ ቴሌግራም
https://t.me/dnhayilemikael
839 viewsedited  18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 18:45:46 #የወጣቶች_ሕይወት /ሕይወተ ወራዙት
(በቀሲስ ህብት የሺጥላ)

#ክፍል_3

#ግብረ_አውናን (Masterbation) #ምንድነው ?

እግዚአብሔር ለምህረትና ለመቅሰፍት ያዘጋጃቸው ልዩ ልዩ ግዳጆችን የሚፈፅሙ መላእክት እንዳሉት ሁሉ ሰይጣንም ሰውን በልዩ ልዩ መንገድ እንዲፈትኑ ድርሻ ሰጥቶ ያዘጋጃቸው አጋንንት አሉት ። ከእነርሱም ውስጥ አንዱ #ሰይጣነ_ዝሙት ነው ። ሰይጣነ ዝሙት የሰው ልጆችን የሚፈትንበት መንገድ የተለያየ ነው ። እንደውም አንዳንዶቹ ፈተናዎቹ የዝሙት አይመስሉም

#ፆር_የለመዱ (የሰይጣንን የፈተና ስልት በደንብ ለይተው ያወቁ ) አበው ቅዱሳን ግን ሽንገላ የሞላበትን የሰይጣንን ፈተና አሸንክላ ምን እንደሚመስል መጪ ትውልድ እንዲያውቀው በሕይወታቸው ያዪትንና መንፈስ ቅዱስ ያቀበላቸውን ፅፈው አስቀምጠዋል ። ለምሳሌ ሰይጣነ ዝሙት የሰውን ልጅ ወደ ዝሙት ተግባር ከሚስብባቸው መንገዶች አንዱና ዋነኛው ገሢሥ ነው ። #ገሢሥ ማለት ማሻሸት፣ መነካካት ፣ መዳበስ ማለት ነው ። ነብዩ ሕዝቅኤል "ግልሙትናቸውንም አፍስሰውባት ነበር " (ሕዝ 23:3) በማለት እንደተናገረው ለዘር የደረሱ ወንዶች ከሴቶች ጋር ሲላፋና ሲዳሩ ሩካቤ ሳይፈፅሙ ዘራቸው የሚፈስበት ጊዜ አለ ። ይህን ድርጊት እንደ ተድላ በመቁጠር ብዙ ወጣቶች ሆን ብለው ያደርጉታል

በቅዱስ መፅሐፍ "የድንግልናዋንም ጡቶች ዳብሰው ነበር " እንደተባለው ቦታ ሳይመርጡና ሰው ሳይለዩ የሴት ልጅን ገላ በመዳበስ "ግልሙትናን ማፍሰስ " ያሳፍራል ። ይህ መጥፎ ልማድ የተጠናወታቸው ሰዎች ግርግርና በሰው ብዛት የተጨናነቀ ስፍራ የሴቶችን ገላ እንደ ሐሳባቸው ለመነካካት ምቹ ሁኔታን ይፈጥርላቸዋል። ከነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ ሰው ስራቸውን አይቶ እንዳይነቅፋቸው የተለያዪ ዘዴዎችን ይፈጥራሉ። ለምሳሌ አንዳንዶቹ ምንም ሳያውቁና በእንቅልፍ ልባቸው ያደረጉት ለማስመሰል እንደ ተኛ ሰው እየተገላበጡና እያንኮራፋ በልዩ አጋጣሚ አጠገባቸው የተኛችውን ሴት ገላ ሲዳብሱ ያድራሉ

ይህ ድርጊት ያለ ሩካቤ የወንድ ዘር ከሚፈስባቸው መንገዶች መካከል አንዱ ነው ። ሌሎች ደግሞ በአድካሚ የጉዞ ወቅት ደጋፊ ፣ በሕመም ጊዜ ደግሞ አስታማሚ ... እየመሰሉ ከወሊድ ጋር ተዛምዶ ያላቸውን አካላት ለመደባበስ የሚሞክሩ ናቸው ። አንዳንዶች ደሞ እነርሱ ፈፅሞ ለመንካት እንዳላሰቡ ነገር ግን የተፈጠረው ሁኔታ እንዲጋፋ ወይም እንዲነካኩ እንዳደረጋቸው ለማስመሰል ይሞክራሉ ። በብዛት እንደዚ የሚያደርጉት ሕዝባዊ ስብሰባዎች በሚደረግባቸው እለታትና መጨናነቅ በሚኖርባቸው ስፍራዎች ነው ። ለምሳሌ እንደ ጥምቀት ፣ መስቀል ፣ ኤግዚብሽኖች ፣ የሞሉ ሚኒባሶች ሀይገሮች ባሶችና ባቡሮች መጥቀስ ይቻላል

ሌሎች ደግሞ ውጫዊ ይዘታቸው ሲታይ በዚህ ዓይነት ዘርን በማፍሰስ የመርካት ተግባር የማይጠረጠሩ አይነት ናቸው ። ለምሳሌ እድሜያቸው በጣም የገፋ ፣ በአስተሳሰብ የበሰሉ ፣ በአለባበስና በምጣኔ ሀብት የተከበሩ የሚመስሉ ወይም አስተማሪ የሆነ መንፈሳዊ አቋምና መልካም ስም የያዙ ናቸው ። እንደዚ ያሉት ሰዎች የሌሎችን ህዋሳት ለመነካካት የሚያደርጉት ጥረት "ይህን አስበው አይደለም " እየተባለ ብዙ ጊዜ በበጎ ይተረጎምላቸዋል

ሌላው ዝንባሌያቸው ደግሞ ታዳጊ ህፃናትን ማባለግ ነው ። በቅጡ ጡት ያላጎጠጎጡ ሕፃናትም እንኳን የእነዚህ ሰዎች የጥቃት ሰለባዎች ናቸው ። ህፃናቱ እነዚህ ሰዎች ምን እያደረጉ እንደሆነ አያስተውሉም ፣ አያውቁም ፣ ቢያውቁም አይቃወሟቸውም አይከሷቸውም ። ወይም በትንሽ ነገር ሊባበሉና ሊታለሉ ይችላሉ ።ሕፃናቱን ያጫወቱና ያሳሳቁ በመምሰል ሲታገሉና ሲላፋ በፍትወት እየተቃጠሉ ልብሳቸውን በዘር ጭቃ የሚለውሱትን ወንዶች ቁጥር ቤት ይቁጠረው

... ይቀጥላል

@https://t.me/dnhayilemikael
151 views15:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 22:01:23 #የወጣቶች_ሕይወት (ሕይወተ ወራዙት)

(በቀሲስ ሕብረት የሺጥላ)
#ክፍል_2

#ሕልመ_ለሊት_መፍትሄ_አለው ?

ብዙ ሰዎች ተግቶ ለመፀለይ ፣ ለማስቀደስና ለመቁረብ በወሰኑ ጊዜ ሕልመ ለሊት እንቅፋት እየሆነ ይፈተኑበታል። በእርግጥ መብላትና. መጠጣት ሳያቆሙ ሙሉ ለሙሉ ከሕልመ ለሊት መለየት አስቸጋሪ ከመሆኑም በላይ የሚቻል ነገር አይደለም ። ስለዚህ መፍትሄዎችን እናያለን

#ሀ በመፅሐፈ መነኮሳት ላይ"በሌሊት በሕልም ከሴት ጋር የተገናኘህ መስሎህ ዘር ቢወርድህ በመዓልት አታስባት " ይላል ። ሕልምህን ደስ እያለህ ብታስባት ግን በተግባር ዝሙትን ወደ መፈፀም ያደርስሃል። ስለዚህ ከሕልመ ለሊት ፈተና ለመዳን አንዱ መፍትሔ ሕልምን በውን ደስ እየተሰኙ መላልሶ አለማሰብ ነው

#ለ ሕልመ ለሊት በምታይበት ጊዜ ከነቃህ ቸል ብለህ ተመልሰህ አትተኛ ። ፈጥነህ ተነሳና ተጣጥበህ ጸሎት አድርስ ። ከተቻለህ ስገድ ባይቻልህ ግን የባሕሪህን ድካም ፈጣሪ ያውቀዋልና ይቅር በለኝ ፣ አድነኝ ፣ እያልህ ወደ እግዚአብሔር ለምን

#ሐ ሌላው ከሕልመ ለሊት ለመዳን ዋነኛው መፍትሔ ውኀ በብዛት አለመጠጣት ነው ። መፅሐፈ መነኮሳትም ይሄን ሲመሰክር " እንደ ውኀ ጥም አካልን የሚያደርቅ ፣ከሕልመ ሌሊትና ከዘር መፍሰስ ፣ በቀን ሐጢአት ማሰብን የሚያጠፋ የለም " ይላል ። አንድ ሰው ምንም በጾም አመጋገቡን ቢቀንስ አብዝቶ ውኃ የሚጠጣ ከሆነ አይጠቀምም። ለምን ቢባል ሰውነቱ ስለሚለመልምና ሰይጣን እርሱን ለማሳት መንገድ ስለሚያገኝ ነው ። ስለዚህ ከሕልመ ሌሊት እፎይ ለማለት ከፈለክ "ውኃን ከልክለህ ሰውነትህን አስጨንቀው " ተብለሀል። ወንጌልም ይህን ሲያጠነክር እንዲህ ይለናል ፦ "ርኩስ መንፈስ ግን ከሰው በወጣ ጊዜ ዕረፍት እየፈለገ ውሃ በሌለበት ቦታ ያልፋል ፤ አያገኝምም ። በዚያን ጊዜ ወደ ወጣሁበት ቤቴ እመለሳለሁ ይላል ፣ ቢመጣም ባዶ ሆኖ ተጠርጎ አጊጦ ያገኘዋል " (ማቴ 12-43) ይህ ጥቅስ ብዙ ትርጉሞች ቢኖሩትም ከያዝነው ሃሳብ ጋር የሚዛመደውን ብቻ እንይ ፡" ርኩስ መንፈስ ግን ከሰው በወጣ ጊዜ ዕረፍት እየፈለገ ውሃ በሌለበት ቦታ ያልፋል ። ማለት ሰይጣን መግቢያ ካገኘው ብሎ ሰውነቱን በረሃብና በጥም ወደሚያስጨንቅ ሰው ይሄዳል ማለት ነው ። ይልቁንም "ውሃ በሌለበት" ማለቱን መዘንጋት የለብንም ።"አያገኝምም "የሚለው ቃል ደሞ ሰይጣን ሰውነቱን በውሃ ጥም (በፆም) በሚያስጨንቅ ሰው ላይ ለማደር አለመቻሉን ያሳያል ።

#መ በሕልመ ለሊት በተደጋጋሚ እንዳትጠቃ ወደ ዝሙት ከሚያመራ ማናቸውም ነገር ሽሽ። በመሸ ጊዜ የምታያቸውን ፊልሞች ፣ ንባቦች ፣ ሌሎችንም ነገሮች በጥንቃቄ መርምረህ ለፍትወት የሚያጋልጡትን ሽሽ።ከዚያ ይልቅ ደጋግ መንፈሳዊ መፅሐፍትን ለማንበብ ትጋ ።

#ሠ ሌላው መፍትሄ ደግሞ ከመንፈሳዊ መምህራንና ከአበው ካህናት ጋር እየተመካከሩ በሚያቀርቡት የመፍትሄ ሀሳብ መጓዝ ነው ። እዚህ ላይ ልንጠነቀቅ የሚገባን የምናማክረው ሰው ምስጢራችንን ለመጠበቅ የታመነና በምንነግረውም ነገር ራሱ ወደ ፈተና ሊገባ የማይችል በሕይወቱ ብዙ ተሞክሮ ያለው መሆን አለበት ። እንዲሁም ጥሩ መፍትሄ አለን ፡ ልፋፈ ፅድቅ እንደግማለን እያሉ ከሚያጭበረብሩ ተኩላ ባህታውያንም መጠንቀቅ
አለብን

@dnhayilemikael
@dnhayilemikael
@dnhayilemikael
293 views19:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ