Get Mystery Box with random crypto!

ቅበላ_ዓላማው_ምንድን_ነው? #አንብቡት ስለ ቅበላ ያለን አመለካከት በልማዳችን | አድኅነነ እግዚኦ እስመ ሃልቀ ሔር

ቅበላ_ዓላማው_ምንድን_ነው?
#አንብቡት

ስለ ቅበላ ያለን አመለካከት በልማዳችን ውስጥ የተንሸዋረረ ነው
ከጾም ጋር ተያይዞ በሕዝበ ክርስቲያኑ ዘንድ ከሚፈጸሙ ተግባራት መካከል በአጽማት መግቢያ የሚደረገው የአቀባበለ ሥነ ሥርዓት ነው። ይህ ሥርዓት በራሱ መጸሐፍ ቅዱሳዊ ይዘት ያለውና በጥንታዊቷ ቤተክርስቲያንም የተለመደ ትውፊታዊ ቅብብሎሽ ያለው ሥርዓት ነው። ይህ ግን አሁን ከምንፈጽመው የቅበላ ሥርዓት የተለየ ነበር። ጥቂት ማሳያዎችን እንመልከት።

https://t.me/dnhayilemikael

➪ በመጸሐፍ ቅዱስ አይሁድ ቀዳሚት ሰንበት ከመግባቷ በፊት በዋዜማው የተለየ አቀባበል ያደርጉ ነበር። ዓርብ ፀሐይ ሲገባ ካህኑ ደውል
ይደውላሉ አሊያም በቤት ያለ የቤቱ አባወራ የሰንበት
መግቢያ ሰዓት መቃረቡን ድምጽ በማሰማት ያሳውቃል፡፡ በአካባቢው ያሉ ሁሉ ይሰበሰባሉ፡፡ በአንድ ላይ ሆነው ወደ ፀሐይ መውጫ ይሰግዳሉ፡፡ ጸሎት ይደረጋል፡፡ ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ እስራኤል፣አሥርቱ ቃላት ሌሎችም ንባባት ይደገማሉ፡፡ ማብራት ተይዞ “ዕለተ ሰንበት እንኳን
ደህና መጣሽ” ብለው ያከብሯታል፡፡ ከሦስት ሰዓት በኋላእራት ይበላሉ፡፡ ሌሊቱን በሙሉ እግዚአብሔርን
ሲያመሰግኑ ያድራሉ፡፡" ከዚህም ጎን ለጎን ከግብጽ ባርነት መውጣታቸውን ምክንያት በማድረግ ለሚያከብሩት የፋሲካ ሏዓል በታዘዞት መሠረት ጠቦት አዘጋጅተው አቀባበል ያደርጉለት ነበር። ኦዘጸ 25:12

❷➪ ትክለኛው ቅበላ ግን ከሕሊና ዝግጅት ጋር ተያያዥነት ያለው ነው። ቀደምት አበው አጽዋማት ከመግባታቸው በፊት ለቤተመቅደስ አገልግሎት የሚሆኑ መገልገያዎችን ያዘጋጃሉ እነርሱም እራሳቸውን ለአገልግሎት ያዘጋጃሉ። ምእመኑም ሱባኤውን የሚያሳልፍበትን ቦታ መርጦ ይጠብቃል ንሰሐ ገብቶ እራሱን ለቅዱስ ቁርባን ያዘጋጃል። የቀማውን ይመልሳል የበደለውንም ይክሳል። ማጠናቀቅ ያለበትን ተግባረ ሥጋ ፈጽሞ ይጠብቃል። በጥቅሉ በጾም ወቅት ሊሟሉ የሚገቡ ውጫዊና ውስጣዊ ዝግጅቶችን በዋዜማው ይፈጽማሉ። ካገኙ በመጠኑ መቀበያ የፍስክ ምግብ ይመገባሉ ካላገኙ ግዴታ ስላልሆነ ጥሬ ቆሬጥመው ውሀ ተጎንጭተውም ቢሆን ይቀበሉታል።

❸➪ አሁን ያለው ደግሞ ፍጹም የተለየ አቀባበል ነው
። በጾሙ ላይ ተሳትፎ የሌለውም ያለውም በጠቅላላ የህሊና ዝግጅት የለውም አቀባበል ሲባል ቀጥታ ግንኙነት ያለው ከመብላትና ከመጠጣት ጋር ይመስለዋል። በየቦታው ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሲበላ ሲጠጣ ሲያልፍም ወዳልተገባ ሥጋዊ ስሜት ውስጥ ይገባል። ብዙ ነዳያን የሚቀምሱት ባጡበት ዘመን ከገደብ ያለፈ የአመጋገብ ሥርአት በቅበላ ወቅት የተለመደ ነው። ይህ ከክርስትናው ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለውም ሰው ለፈቃደ ስጋው ሲያደር የፈጠረው እንጂ። እግዚአብሔር ለቅበላው ስለበላነው እና ስላልበላነው ጉዳይ ሳይሆን ሚያሰበው የእኛ በኃጢአት መኖር መሆኑን ልብ እንበል። ስጋ በልቶ የተቀበል ቆሎ በልቶ ከተቀበለው ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ብልጫ የለውም። ከሁሉ ሚያሳዝነው በቅበላውም በፍቺውም የፍስከ ምግቦች ለመብላት የሚሰለፉት ማይጾሙት መሆናቸው ነው። ስለዚህ በቅበላ ጊዜ "የግድ እነዚህን ካለበላችሁ የሚል ህገ የለም ያገኘም በመጠኑ እና በማያስነውር መልኩ ቢመገብም ነውር የለውም። በአጽማት ስጋ መብሊት አለመብላት ግዴታ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ ዝግጅቶች ምናደርግበት ነው።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን ይቆየን

ተቀላቀሉ ቴሌግራም➘ https://t.me/dnhayilemikael