Get Mystery Box with random crypto!

ከንጉሥ ካህን ይበልጣል! የንጉሥ ሥልጣን በሥጋ ላይ ነው፤ የካህን ሥልጣን ግን በነፍስ ላ | አድኅነነ እግዚኦ እስመ ሃልቀ ሔር

ከንጉሥ ካህን ይበልጣል!

የንጉሥ ሥልጣን በሥጋ ላይ ነው፤
የካህን ሥልጣን ግን በነፍስ ላይ ነው፡፡
ንጉሥ ይቅር ቢል የገንዘብን ዕዳ ነው፤
ካህን ይቅር ሲል ግን የበደል የኃጢአት ዕዳን ነው፡፡
ንጉሥ ያዝዛል፤
ካህን ግን ያስተምራል ይዘክራል፡፡
ንጉሥ ያስገድዳል፤
ካህን ግን ነጻ ፈቃድን ያያል፡፡
ንጉሥ ቁሳዊ የጦር ዕቃ መሣሪያ አለው፤
ካህን ግን ረቂቅ (መንፈሳዊ) የጦር ዕቃ መሣሪያ አለው፡፡
ንጉሥ የጦር ዕቃ መሣሪያውን ቢሰብቅ አንገዛም ብለው ባመፁት (እንዲሁም ከወራሪዎች ሥጋውያን ደማውያን) ላይ ነው፤
ካህን ግን ውጊያው ከጨለማ አበጋዞች ከአጋንንት ጋር ነው፡፡

ስለዚህ ሥልጣነ ክህነት ከሥልጣነ መንግሥት ይበልጣል፡፡ እንዲህም በመኾኑ ንጉሥ አንገቱን ለካህናት እጅ ያጎነብሳል፡፡