Get Mystery Box with random crypto!

ዘፈን በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ክፍል 1 ዘፈን ጥበብ ነውን ? ዘፈን ጥበብ ነው የሚሉ አ | አድኅነነ እግዚኦ እስመ ሃልቀ ሔር

ዘፈን በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ

ክፍል 1

ዘፈን ጥበብ ነውን
?

ዘፈን ጥበብ ነው የሚሉ አሉ። አዎን ጥበብ ነው ከእግዚአብሔር ሳይሆን ከሰይጣን የተገኘ ጥበብ ነው፤ ቅዱስ ሳይሆን ርኩስ ጥበብ ነው፤ መዳኛ ሳይሆን መጥፊያ ጥበብ ነው፤ የህይወት ሳይሆን የሞት ጥበብ ነው፡፡ ይህን ሳስብ ቅዱስ ጳውሎስ የዚች ዓለም ጥበብ በእግዚአብሔር ዘንድ ሞኝነት ነው ያለው ትዝ አለኝ

እግዚአብሔር ድምፅ የሰጠን እሱን እንድናመሰግንበት እሱን እንድናወድሰው፣ እሱ የፈቀደላቸውን እሱ ያከበራቸውን ቅዱሳኑን እንድናመሰግንበት ነው እንጂ ለሰው እንድንዘፍን አይደለም። ወይ የእግዚአብሔር ወይም የዓለም ልንሆን ግድ ይለናል፤ ሁለት ጌታ የለም።  ዘፈን መዝፈን ኃጢያት ነው

አሁን ባለንበት ዘመን ዘፈን ኃጢያት እንደሆነ፤ የዲያቢሎስ ታላቅ መሳሪያ እንደሆነ፤ ዘፋኝነት ከክርስቶስ ማህበር እንደሚለይ በግልጽ እየተመለከትን ነው። ዘፈን ስራ ነው የሚሉ አሉ አዎን ለዘፋኝ መዝፈን ስራው ነው፤ ለሌባም መስረቅ ስራው ነው፤ ለዝሙት አዳሪዋም ዝሙት ስራዋ ነው፤ ለቅጥረኛ ነፍሰ ገዳይም መግደል ስራው ነው ግን ደግሞ ኃጢያት ናቸው ስራዬ ነው ብሎ ኃጢያትነቱን ማስቀረት አይቻልም፡፡ እንግዲህ ምን እንላለን ኃጢያትን ስራ ነው ብለን ሙግት እንገጥማለንን ?

እየመረጥን ብንዘፍንስ ለመልካም የተዘፈኑ ዘፈኖች አሉ የሚሉም ብዙ ናቸው። ዘፈን ሀጥያት ነው በቃ ምንም ጥያቄና መልስ የለውም ቴዲ ስለዘፈነው መዝሙር መሆን አይችልም ስለ ሀገር ሆነ ስለምን.. ስለ ሀገር ጸልዩ እንጁ ዝፈኑ አልተባለም፣ እናት ቢዘፈንላትስ ይላል ደሞ አንዱ፣ እድሜህ እንዲረዝም እናትና አባትህን አክብር ይላል እንጂ ዝፈንላቸው አይልም!! ብዙ ሰው ጥብቅና ለቆመለት ሰው ቃሉ ይህን ይላል

<< ዘፋኝነት፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜም እንዳልሁ፥ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም!!።">>(ወደ ገላትያ ሰዎች 5:21)

አንድ ሌባ ሰርቆ የተራበ ቢያበላ ጽድቅ ነውን??? የተቸገሩ ሰዎችን ከችግራቸው ያላቅቅ ዘንድ አጥብቆ የሚተጋ አንድ ሰው ሌሎችን ለመርዳት የሚያስፈልገውን ገንዘብ ለማግኘት ዝሙትን መፈጸም ግድ ቢሆንበት እርሱም ሰውነቱን አርክሶ ዝሙትን ፈጽሞ ገንዘቡን ቢቀበል ችግረኞቹንም ከችግራቸው ቢያላቅቅ መልካም አደረገ እንለዋለንን??? ዘፈን ያስደስታል፣ ዘና ያደርጋል፣ ደስታ ይፈጥራል ... ወዘተ ምክንያቶች እየደረደርን ጥብቅና አንቁም! መልካምን ነገር ለማድረግ በኃጢያት ውስጥ ማለፍ አይጠበቅብንም፤  ኃጢያትን ያደረገ ኃጢያተኛ እንጂ ጻድቅ ሊባል አይችልም፡፡ ነገሩ ከዝንጀሮ ቆንጆ ምን ይመራርጡ ነው እንዲያ ካልሆነማ፤ ከኃጢያት ከተመረጠማ ለዘፈን ብቻ ለምን ?

የዘፈነው ለመልካም ነው፤ ፍቅርን ለመስበክ ነው፤ አንድነትን ለማምጣት ነው ካልን ሌባውም የሰረቀው የተቸገሩትን ሊያበላ ነው፤ ሰውየውም ዝሙት የፈጸመው ችግረኞችን ለመርዳት ነው፣ ነፈሰ ገዳዩም እንጀራ ሆኖበት ነው። ስለዚህ እነዚህም አብረው ይጽደቁ? እንዲህ ከሆነ ደግሞ ኃጢያተኛ ሁሉ ጻድቅ ሆነ ማለት ነው። ራሳችንን ከማታለል እንውጣ፤ ከአዚም እንላቀቅ አትግደል ከተባለ አትግደል ነው፤ አትስረቅም አትስረቅ ነው፤ አትዝፈን ሲልም አትዝፈን ነው፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ተመራጭ አገዳደል፤ ተቀባይነት ያለው ስርቆት፤ የሚወደድ ዘፈንም የለም ... ይቀጥላል

https://t.me/dnhayilemikael