2022-12-26 14:41:41
#ለወረት_የዘንድሮ_ፍቅር_ባፍንጫዬ_ይውጣ
የመሬት ስበትና ኤሌክትሮማግኔቲዝም የመሳሰሉ የተፈጥሮ ታላላቅ ሃይሎች ከስሜታችን የተሰወሩ ቢሆንም ጉልበታቸው ግን የማያከራክር ነው። በተመሳሳይ የፍቅር ሃይል ከእይታችን የተሰወረ ቢሆንም ከሌሎች ተፈጥሯዊ ሃይሎች ሁሉ በእጅጉ ይልቃል። የሃያልነቱ አሻራም በመላው ዓለም ተሰራጭቶ ይገኛል።ያለፍቅር ህይወት አይኖርም።
እንደመላዕክት ክንፍ ቢኖረኝ እንኳን ፍቅር ከሌለኝ ከንቱ ነኝ የሚለውን የሐዋሪያውን ቃል ሰምቼ ካልገባሁበት ያልኩት ፍቅር ለካስ እራሱን የቻለው መስፈረት አለው።
ፍርሃትን ለማሸነፍ ፍቅር ሃያል ነው ለዚህም ጌታችን እና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው። ሞትን ድል የነሳው በፍቅሩ ነው። እያንዳንዱን የፍራት ካብ ለመናድ ፍቅር ትልቅ ሃይል ነው። ሴት የላከው ጅብ አይፈራም ይባል አይደል። ብቻ ምን ልበላቹ ፍቅር እራሱን የቻለ የማይታይ ሃይል ነው። ይሄን ያህል ስለ ፍቅር ካልን ፍቅር መስፈርት እንዳለው ስንቶቻቹ ታውቃላችሁ?
ፍቅር ትልቅ የሆነ መስፈርት አለው እሱም “መብሰል” ይባላል። በፍቅር ውስጥ መብሰል ከሌለ መርዛማ ይሆን እና ወደ ፍጹም ጥላቻ ይቀየራል። ይሄን ሃሳብ ትንሽ ልበትናት መስሰል። ለምሳሌ ፦ ሰይጣን በመጀመሪያ የአምላክን ዙፋን ከመመኘቱ በፊት ፍቅር ነበረው ያምፍቅር ጌታው ያስቀመጠለት ሲሆን ሳጥናኤል ሁኖ እንዲገኝ አደረገው ነገር ግን ያልበሰል ፍቅር ስለነበረው እኔ ነኝ አምላክ ብሎ ሳታ ለምን አምላክ የመሆን ፍቅሩ ሃይሎ ስለነበረ ባልበሰረ አምዕሮው እንዲዋሽ እና እንዲኪድ አደረገው። ከዚያም ያፍቅር ወደ መርዝነት በውሸት ምክንያት ተቀይሮ በስተመጨረሻም በእሱና በአምላኩ መካከል ጠላችነትን ፈጥሮ በፍቅር የተጀመረው ጥንስስ በጥላቻ ተጠናቀቀ እላችኋለሁ ይህም ጥላቻ እስካሁን እንደ ቀጠለ ነው። ሌላ ያልበሰለ ፍቅር ታሪክ እምንዘዝ እስኪ ከሐዋሪያው ዮሃንስ በስተቀር ሌሎች በጌታቸው ስቅለት (መያዝ) በሰሙ ጊዜ ሸሹ ነገር ግን ከሰዓታት በፊት እነ ቅዱስ ጴጥሮስ በአምላካቸው ፍቅር ተነድፈው እኔ እሆን እንዴ እያሉ አምላካቸውን እየጠየቁ ነበር። ቢሆንም ግን ያልበሰለ ፍቅር ስለነበረ አምላኩን አላውቅውም ብሎ በመካድ ፍቅሩን ወደመርዛማነት አሳደገው ነገር ግን የአምላኩ ፍቅር የበሰለ ስለነበረ። እራርቶለት ጴጥሮስን እና ሌሎች ሃዋሪያት ጥላቻ ውስጥ አምላካቸው ጋር ሳይገቡ እናም ተለያዩ ።
እስኪ የበሰለውን ፍቅር እንይ …..ይበሰለው ፍቅር ለእኔ የኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን መብሰሉን ስለፍቅር ሲል ዝምታን መረጠ ፍቅር የህግ መጨረሻ መሆኑን ለማሳይወቅ እስከ መጨረሻው ደቂቃ ድረስ ምንም ሳይናገር የሚረጉትን እየመረቀ ሲመቱት ምንም ሳይመልስ አለፈ። የመብሰልን አስፈላጊነት ሲነግረን በዝምታው ውስጥ የሌሎችን ጥላቻ እሱ ግን በፍጹም ፍቅር መለሰ የነሱንም የፍቅር ምላሽ አልፈለገም ከመትረፍረፍ የወጣ ፍቅር ስለነበረ ሁሉን እንደ ታረ ቆጠረው።
እና ወደተነሳሁበት የዘንድሮ ፍቅር ስመጣ ፍቅር እንደ ሳጥናኤል የሆነ ነገርን በመፈልግ ላይ የተመሰረት እና ከስሜት ብቻ የሚነዳ በመሆኑ እንዲሁም እንደ ሐዋሪያት በችግር ጊዜ የሚሸሽ፣ ልታይ ላታይ የሚወድ እና አንዱ አንዱን መማማለን በሱ ቁጥጥር ስር በማድረግ ለመጫወት የሚሞክርበት ነው። ……እና እኔም ለምን ይቀርብኝ ብየ የገባሁበት የዘንድሮ ፍቅር ተመርዞ ወደ ዘላለማዊ ጥላቻ ሳይቀየር ባቆመዉስ አይሻልም ትላልቹ።
ነገር ግን ወደዱ አፍቅሩ የጥንቱን ፍቅር ካገኛችሁት እንደዛ ስትባሉ ደግሞ ተጃጃሉ አሏቹ።
ያለፍቅር ህይወት አይኖርም። አፍቅሩ አፍቅሩ ነገር ግን ከእናተ እና ካላማቹ በኋላ አምላካችሁን እያስቀደማችሁህ።
8:40 ቀን
አዲስ አበባ - ቦሌ
17/04/2015
◉ Join us share◉●••
═════❥━━━❥═════
ነገን ላየው እጓጓለሁ!!! https://t.me/Deinstein_21
63 viewsedited 11:41