2022-12-02 12:09:31
#ስለዚህ ስለ ፍርሃት አላወራም፡፡ የበለጠ አፍቃሪዎች ትሆኑ ዘንዳ እረዳችኋለሁ ፍርሃትም እንደ ውጤት ይጠፋል፡፡ በፍርሃት ላይ ቀጥታ መስራት ብትጀምሩ ፍርሃትን በይበልጥ ታጠናክሩታላችሁ የዚህ ምክንያቱም መላው ጥሞናችሁ በፍርሀት ላይ ስለሚያተኩር ነው፡፡ ይህም አንድ ሰው ጨለማን ለማጥፋት
እንደሚሞክረው አይነት ነገር ነው፡፡ ጨለማን በቀጥታ ማጥፋት አትችሉም፡፡ ምክንያቱም በመጀመሪያ ደረጃ ጨለማ የሚባል ነገር የለም፡፡ጨለማ እንዳለ ያለውን እውነታ እወቁት እና እንዴት ብርሃንን በማምጣት ጨለማን ማጥፋት እንደሚኖርባችሁ እወቁ፡፡
ፍርሃትን ለመዋጋት የምትጠቀሙት ተመሣሣዮ ሃይል ፍቅርን ለማሣደግ መጠቀም ይቻላል። ብዙ ጥሞናን ለፍቅር ስጡ፡፡ ስትነኩ ልክ መላው ሰብዓችሁ በእጃችሁ ውስጥ እየፈሰሰ እንደሆነ በሚሰማ ሁኔታ በሚቻለው መጠን በፍቅር ንኩ፡፡ ሃይል በእጃችሁ ውስጥ በመፍሰስ ሲያልፍ የሚሰማችሁ ይሆናል፡፡ ፍቅር የምትሰሩ ከሆነ ሁሉንም ስልጣኔ እርሱት እና የዱር ሁኑ። ስለፍቅር የተማራችሁትን ሁሉም ነገር እርሱት:: አንድ ጊዜ የፍቅር መኖር የፍርሃት መጥፋት መሆኑን ካወቃችሁ ነገሩ ገብቷችኋል ማለት ነው፡፡ እናም ምንም ችግር አይኖርም፡፡
የሰው ልጅ በፍርሃት ውስጥ በሚኖር ጊዜ ጠጣር ይሆናል፡፡ ይህን ጠጣርነት የሚፈጥረው ፍርሃት ነው፡፡ በፍርሃት ውስጥ ስንሆን ሁሉንም በሮች እና መስኮቶች እንዘጋለን፡፡ በጣም ትንሽ ፣ ጨለማ ጉድጓድ ውስጥ መኖር ጀምረናል፡፡ ህይወታችን ቀድሞውኑ ሞት ይሆናል፡፡ የተጠበቅን እንሆን ዘንዳ በዙሪያ ገባችን ጠንካራ ብረት የተሰራ ጥሩር / ጋሻ እንፈጥራለን፡፡
ይህ የህይወት መንገድ አይደለም፡፡ ይህ ራስ የማጥፊያ መንገድ ነው፡፡ ይህ እውነተኛው ራስ ማጥፋት ነው፡፡ ይህ ወደ መቃብራችሁ ውስጥ ገብታችኋል ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ይህ አይነቱ የተዘጋ ህልውና አንዳችም እውነትን፣ ውበትን፣ ፍቅርን፣ ቡራኬን፣ እግዚአብሔራዊነትን ማወቅ አይችልም፡፡ ምንም ነገር ለማስገባት ካልተፈቀደ ምን እንደከበባችሁ ልታውቁ ትችላላችሁ? እናም የከበባችሁ ምን እንደሆነ ካላወቃችሁ ራሳችሁን ፈጽሞ ማወቅ አትችሉም፡፡ አንድ ሰው ራሱን ማወቅ የሚችለው ከሌላው ሰው አንጻር ነው፡፡
የስነ-ልቦና ተመራማሪዎች እንደሚሉት -ህጻኑ በመጀመሪያ የሚያውቀው ሌሎችን ማለትም ፡- እናቱን፣ አባቱን፣ ወንድሞቹን፣ እህቶቹን፣ ቤተሰቡን፣ የከበቡትን ነገሮች፣ ክፍሉን፣ ግድግዳዎቹን፣ አሻንጉሊቶቹን ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ቀስበቀስም በጣም እና በጣም እየቀረበ ይመጣል፡፡ ከዚያም አካሉን ማወቅ ይጀምራል፡፡ ከዚያም አንድ ቀን ራሱን እንደ ተነጠለ ግለሰብ ይሰማው ይጀምራል፡፡ በመጀመሪያ ሌላውን ያውቃል እናም ከዚያ በኋላ ራሱን ከሌላው በማነጻጸር ለራሱ ፍቺ ይሰጣል፡፡ ሌላውም ፍቺውን ይሰጣል፡፡
ነገሮችን የግሉ በማድረግ የሚኖር ሰው እውነተኛ ማንነቱን እያዉቅም፡፡ ምክንያቱም ይህ ሰው የሚኖረው በነገሮች ተከብቦ ነው እናም ሰዎች እናንተን ፍቺ የሚሰጧችሁ እንደ ነገር ነው፡፡ ሰዎች እናንተን እንደ ነፋስ ፍቺ ሊሰጧችሁ አይችሉም፡፡
አንድ ሰው በጥልቅ ፍቅር ውስጥ ብቻ ነው ነፍሱን ማወቅ የሚችለው ምክንያቱም በጥልቅ ፍቅር ውስጥ ሲሆን የሌላውንም ነፍስ የሚያውቅ ይሆናል፡፡ የሌላው ነፍስም በውስጣችሁ ምላሽን፣ ብቃትን ይፈጥራል፡፡ በድንገትም ከጊዜ እና ቦታ ባሻገር የሆነን አዲስ ልኬትን የምታውቁ ይሆናል፡፡
ምንጭ ፦ ነፃ ስሜቶች( ኦሾ)
ተርጓሚ ፦ ዩሀንስ አዳም ነገን ላየው እጓጓለሁ!!!
https://t.me/Deinstein_21
“https://t.me/Albetredeinstein”
194 views09:09