2022-11-24 12:14:54
ከፀሐይ በታች በሚደክምበት ድካም ሁሉ የሰው ትርፉ ምንድር ነው?
እንዴት ናችሁ
ሰሞኑን ጳዉሎስ ሆስፒታል ከአንድ አባት ጋር እያወራን በጨዋታ መሀል አንድ ጥያቄ ጠየቋቸው፡፡
እንዴት ነው ወደ ወጣትነት ዘመኖ ቢመለሱ ምን ያስተካክሉ ነበር?
#_አይ_ልጄ_የእግዚአብሔርን_ቃል_አነብብ_ነበር_እንደቃሉም_እኖር_ነበረ ፡፡
ይገረምሀል ያልሞከርኩት ነገር የለም እጠጣለው አጨሳለው ይኸው ሲጋራ ካቆምኩኝ አምስት አመት አለፈኝ እስከ አሁን ድረስ ያስቸግረኛል፡፡
ሁሉም ነገር ከንቱ ነው፡፡
አባቶች እንደዚህ ይሉ ነበር ስለ #መጠጥ
ወደ መጠጥ ቤት ( #እንደ_እርግብ_ትገባለህ ) ጨዋታው ይጀመራል ( #እንደ_ዝንጀሮ_ታስካካለህ) ቀጣይ መናደድ ትጀምራለህ ( #እንደ_ነብር_ትቆጣለህ ) መሳደብ መጣላት መደባደብ ትቀጥላለህ ( _ #እንደ_አሳማ_ተጨመላልቀህ_ትወጣለህ)
ጠቢቡ ሰለሞን ሊያስተምረን ሲጀምር እንዲህ አለ፡ (መጽሐፈ መክብብ 1 )
------------
2 ሰባኪው፦ ከንቱ፥ ከንቱ፥ የከንቱ ከንቱ፤ ሁሉ ከንቱ ነው ይላል።
3 ከፀሐይ በታች በሚደክምበት ድካም ሁሉ የሰው ትርፉ ምንድር ነው?
ደግሞ ሲጨርስ እንዲህ አለ " #የነገሩን_ሁሉ_ፍጻሜ_እንስማ ፤ #ይህ_የሰው_ሁለንተናው_ነውና ፤ #እግዚአብሔርን_ፍራ፥ #ትእዛዙንም_ጠብቅ ።"
(መጽሐፈ መክብብ 12: 13)
126 views09:14