Get Mystery Box with random crypto!

#በድንብ_አብቅሩ_እንጂ_ማንም_ፍቅራቹ_ባይገባውም_በደንብ_አፍቅሩ | Deinstein_21

#በድንብ_አብቅሩ_እንጂ_ማንም_ፍቅራቹ_ባይገባውም_በደንብ_አፍቅሩ ከፍቅር ውጪ ፍርሃት መኖሩ ግድ ነው፡፡ ፍርሃት የፍቅር አለመኖር ነው፡፡ ፍርሃት በውስጡ አንዳችም አዎንታዊ ነገር የለውም፡፡ ፍርሃት በቃ የፍቅር እጦት ነው፡፡ ነገር ግን ማፍቀር ከቻላችሁ ፍርሃት ይጠፋል፡፡ በፍቅር ቅጽበት ውስጥ ሞት እንኳን አይኖርም፡፡

በህይወት ውስጥ ካሉ ነገሮች ሞትን በብቸኝነት ሊያሸንፈው የሚችለው ነገር ፍቅር ብቻ ነው፡፡ ሁሉም ፍርሃት የሚያጠነጥነው በሞት ላይ ነው እናም ሞትን ሊያሸንፈው የሚችለው ነገር ደግሞ
ፍቅር ብቻ ነው፡፡

ስለዚህ ማለት የምፈልገው አንድ ነገር ለፍርሃት ብዙም ትኩረት አትስጡት ነው፡፡ ምክንያቱም ፍርሃቱ ግላዊ ሰመመን ይሆናል፡፡ በፍርሃት መኖራችሁን በቀጠላችሁ ቁጥር ፣ ህይወታችሁ በፍርሃት የሚገዛ መሆኑን በቀጠለ ቁጥር በፍርሃት ተጽእኖ ይደረግባችኋል። ከዚያ በኋላም ፍርሃትን የበለጠ ትረዱታላችሁ፡፡ ይህንን ልብ በሉ - ህይወታችሁ በፍርሃት የታጠረ መሆኑን እወቁ - አለቀ! ይህ ማለት ፍርሃት ይጠፋ ዘንዳ ፍቅር በበቂ ሁኔታ ሃያል አልሆነም ማለት ነው፡፡

ፍርሃት የበሽታ ምልክት እንጂ በራሱ በሽታ አይደለም፡፡ በሽታ ስላልሆነ ሊፈወስ አይችልም፡፡ ፈውስም አያስፈልገውም፡፡ ስለዚህ ፍርሃት ምልክት ነው እናም ምልክቱም በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ ይህ ፍርሃትም ህይወታችሁን ማባከን እንደሌለባችሁ ያሣያል፡፡ ይህ የሚናገረው ብዙ ማፍቀር እንዳለባችሁ ነው።
ነገን ላየው እጓጓለሁ!!!
https://t.me/Deinstein_21
“https://t.me/Albetredeinstein”