Get Mystery Box with random crypto!

Deinstein_21

የቴሌግራም ቻናል አርማ deinstein_21 — Deinstein_21 D
የቴሌግራም ቻናል አርማ deinstein_21 — Deinstein_21
የሰርጥ አድራሻ: @deinstein_21
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.98K
የሰርጥ መግለጫ

@Deinstein_21
.
.

Contact👉0913617275 and 0964742005 or @Albetredeinstein

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-01-10 16:09:21

190 views13:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-09 09:12:36 ታላቅ ግዛት እንዲኖርህ ትፈልጋለህ እንግዲያውስ እራስህን በቅጡ ግዛ

ሰናይ ቀን
15 views06:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-08 15:03:13 "መምህር ሆይ! ፍቅርን ፈልጎ ለማግኜት መንገዱን ይምሩኝ ይላቸዋል። ሩሚም "የአንተ
ድርሻ ፍቅርን መፈለግ አይደለም ነገር ግን ከእሱ ጋር እንዳትገናኝ ያገደህንና በልብህ
የገነባኸውን የጥላቻ ግንብ ማፍረስ ነው " ። ለሩሚ ፍቅር ከፈጣሪ የተሰጠ ስጦታ
በመሆኑም ይህንን ስጦታ የምናገኝበት ቀላሉ መንገድ ሰጭውን አጥብቆ መፈለግ ነው።

ለዚህም ሩሚ ሲናገሩ፦ በፈጣሪ ብርሀን ፍቅር አገኜሁ፤ ከእሱም ውበት ቅኔን ተቀኜሁ፤
የሰው ልጅ ዓይኖች ሊያዩህ በማይቸሉት ልቤ ውስጥ ሆነህም ዘወትር አሸበሽባለሁ፤ እናም
አንዳንዴ በአንተ ታጅቤ ስወዛወዝ ሰዎች ይመለከታሉ ይህንን ደግሞ ጥበብ በማለት
ይጠሩታል

ሱፊው ሩሚ አንድ ወዳጃቸው ቤት ተጋብዘው እጅግ ደስ የሚል የፍቅር ታሪክ ሰምተው
ሲጨርሱ ጋባዣቸው፦ "ፍቅር በእርግጥም እውር ነው፤ ሰዎችን ባልጠበቁት ስፍራ ወስዶ
ያገናኛቸዋል" አለ።

ሩሚ ግን እንዲህ በማለት አስተካከሉት፦ "ፍቅረኞች በመጨረሻ የሚገናኙበት ስፍራ
◉ Join us share◉●••
═════❥━━━❥═════
ነገን ላየው እጓጓለሁ!!! https://t.me/Deinstein_21
119 views12:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-07 22:13:36 ጌታችን እኛን ለማዳን ሲል ስለሀጢያታችን ብዛት ሳይሆን ስለፍቅሩ ኋያልነት ሰው ሆኖ ተወልዶ ስቃያችንን ሊሰቃይልን ሞታችንን ሊሞትልን መጥቶ የፍቅርን ጥግ አስተምሮናልና !

ለሰዎች ያለንን ፍቅር ምን ያህል መሆን ይገባዋል ስንል ጌታችን ምን ድረስ ሰጠን ብለን እንመልከት ያኔ የፍቅር ጥግ ምን ያህል እንደሆነ ገብቶን እርስ በእራስ ስንፋቀር እንኖራለን ! ፍቅር በምድራችን ይብዛልን !

እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም በጤና በፍቅር አደረሳችው በዓሉ የሰላም የደስታ የፍቅር የአብሮነት ይሁንልን ይሁንላችው !

የፍቅር በዓል ተመኘን
ሰውና_ፍልስፍናው
      
@cekuaa
ነገ መልካም ይሆናል !
https://t.me/philoso_phy
             
@cekuaa
54 views19:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-06 21:43:12 #አከብራለሁ!
(በእውቀቱ ስዩም)

ነገ የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ይከበራል፤ ጥምቀት ይከተላል፤ እኒህን ትልልቅ በዓላት የሚከሩበትን ቀናት የደነገገችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ናት፤ ስለእርሱዋ የሚሰማኝን ለመናገር ከዚህ የተሻለ አጋጣሚ የማገኝ አይመስለኝም፤

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን የኢትዮጵያ ቀዳሚ አንደበት ናት ፤ የግእዝ ፊደል የተወለደው ከክርስቶስ ልደት በፊት በአክሱም ነው፤ ይሁን እንጂ ፊደሉን ከርክመው፥ አሰማምረው ፥ ልገው ፥ ስርአት አስይዘው የዛሬውን መልክ ያስያዙት የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ሊቃውንት ናቸው፤ በአማርኛ በተራቀቅሁ ቁጥር የኒህን ሊቃውንት ውለታ አልዘነጋም::

የሰውን ልጅ ከበሬ ወይም ከጉማሬ የሚለየው ባህል ነው፤ በአእምሮ የማይራቀቅ ባህል መፍጠር አይቸልም፤ ኢትዮጵያ ለእንግዳ በኩራት ከምታሳያቸው ደማቅ እና አይነተኛ (ኦሪጂናል) የባህል መለዮዎች መካከል አብዛኞቹ የመነጩት ከአድባራት ነው፤ እድሜ ይስጠኝ እንጂ ዝርዝሩን እያረፍሁ አወጋዋለሁ::

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ባንድ ጊዜ የባህል ሚዝየም እና የባህል መድረክ መሆን ትችላለች፤ በፈርኦኖች ዘመን የኖረ ጽናጽል ብሪቲሽ ሚይዘይም ውስጥ ማግኘት ትችላለህ፤ ጽናጽሉ ወደ ዜማ ሲተረጎም ለመታዘብ ግን አብማ ማርያም ቤተክርስትያን መገኘት ያስፈልጋል::

የቤተክርስትያን ቅዳሴ መታደም ዝም ብሎ የአማኞችን ጉባኤ እንደመታደም አይደለም፤ የጊዜ መኪና እንደመሳፈር ነው፤ በሀያ አንደኛው ክፍለዘመንን ለቅቀህ ራስህን በመካከለኛው ዘመን ውስጥ ታገኘዋለህ፤ አጼ ናኦድ ያደመጡትን ዜማ መስማት መቻልህ ካላስደነቀህ ምን ሊያስደንቅህ ይችላል? ምንጅላቶችህ ያሸተቱትን እጣን ወይም ከሴ ማሽተት መቻልህ ካላስገረመህ ምን ሊያስገርምህ ይችላል? እኔ እንዲህ አይነቱን እድል ጊዜን እንደማስገበር እቆጥረዋለሁ::

የብሉይን መጽሀፍት ብታነቢ የጥንታዊ እብራውያን ታሪክ፤ ባህል እና ህልም ታውቂያለሽ፤ ሀዲስ ኪዳንን ስታጠኚ የጥንት እብራውያን ግሪካውያን እና ሮማውያን እምነት፤ ህልም እና ስነልቦና ትገነዘቢያለሽ፤ የቀደምት አባቶችሽ እና እናቶችሽ ምን ያስቡ እንደነበር ለመረዳት ከፈለግሽ ግን የጻድቃን ገድላትን ማንበብ ይጠበቅብሻል፤ የኢትዮጵያውያንን ስነጽሁፍ፥ ስነልቦና ፥ መልክአምድር ለማወቅ የሚገደው ሰው የጻድቃን ገድላትን እና ድርሳናትን መመርመር ይጠበቅበታል::

በአርባ ቀኔ ማንኩሳ ሚካኤል ተጠምቂያለሁ፤ የልደት ስሜም ወልደሚካኤል መሆኑ ይታወቅልኝ! በባህል ረገድ ራሴን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን እመድባለሁ፤ ያም ሆኖ ዓለማዊነቴን ለመሸመጥጥ አልሞክርም፤ ሊቁ አድማሱ ጀምበሬ “ የምናውቀውን ዓለም በማናውቀው ዓለም እንለውጣለን” ይላሉ፤ ይመቻቸው! እኔ የሚታወቀውን ዓለም በማይታወቀው ዓለም የሚያስለውጥ ምክንያት እስካሁን አልገጠመኝም፤ የሚታወቀውን ዓለም ከነ ትርኪምርኪው በጸጋ እጄን ዘርግቼ፥ ልቦናየን ከፍቼ እቀበላለሁ:: በምድር ስኖር የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ የስልጣኔ ፍሬዎችን ያበረከቱልን ሁሉ ማክበር እና ማመስገን እንደሚገባን ተረድቻለሁ::
ሰናይ በዓል!
Deinstein ይላይ መልካም በዓል ለመላው የሰው ልጅ በሙሉ ◉ Join us share◉●••
═════❥━━━❥═════
ነገን ላየው እጓጓለሁ!!! https://t.me/Deinstein_21
125 viewsedited  18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-30 11:32:15 ስለዚህ ፍቅር መልካም ነገር ነው፡፡ እንደውም ፍቅር የሌለበት ነገር ሁሉ ስህተት ነው፡፡ ግን ፍቅር ከፍተኛ ዋጋ በመሆኑ ከማንኛቸውም ዓይነት በካይ መርዘኛ ነገሮች መጠበቅ አለበት፡፡ ትስስር ይበክለዋል። ዓለም በግለሰቦች የተሞላች እንድትሆን እፈልጋለሁ፡፡ «ጥንድ» የሚለው ቃል እንኳን ይዳዳኛል፡፡ የሁለት ግለሰቦችን ህልውና አጠፋችሁ ማለት ነው:: ጥንድ በራሱ ውበት የለውም፡፡

ዓለም በግለሰቦች ብቻ የተሞላች ትሁን፡፡ ፍቅር በራሱ ጊዜ ጎምርቶ ሲፈነዳ ፍቅርን ዘምሩት ፣ ጨፍሩት፣ ኑሩት፣ ግን ፍቅርን ወደ ሰንሰለት አትለውጡት፡፡ ሰውን በባርነት ለመያዝ አትሞክሩ፣ ሌላም ሰው በባርነት እንዲይዛችሁ አትፍቀዱ። ነፃ ግለሰቦችን የያዘች ዓለም በትክክል ነፃ አለም ትሆናለች።

መፈለግ (መውደድ/ ከሰዎች ታላላቅ ፍላጎቶች አንዱ ነው። ስለዚህ ፍቅር ህልውናን ይዞ ይኖራል። የሰው ልጆች እስካሉ ድረስ የፍቅርን ያህል ትልቅ ነገር አያገኙም። በምድር ላይ የሚገኝ ግን የምድር ያልሆነ ነገር ነው:: በፀሐይ ፊት እንደንስር የምትበሩበት ክንፍ ይሰጣችኋል።

ያለ ፍቅር አክናፋት አይኖሯችሁም። እጅጉን አስፈላጊ የመንፈስ ምግብና ተፈላጊ ነገር ከመሆኑ የተነሳ በዙሪያው ችግሮች ይከቡታል። ፍቅረኛህ ወይንም ፍቅረኛሽን ነገ የራስህ /ሸ/ ማድረግ ትፈልጋላችሁ ውብ ነገር አሳልፋችኋል፣ ለነገ ደግሞ ትጨነቃላችሁ::
ክፍል 4 ◉ Join us share◉●••
═════❥━━━❥═════
ነገን ላየው እጓጓለሁ!!! https://t.me/Deinstein_21
59 views08:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-29 17:30:13 ፍቅርህን ህልውናህ አድርገው፡፡ ፍቅር እንዲይዝህ ሳይሆን አፍቃሪ እንድትሆን ጣር፤ ፍቅር ባሪያህ ነው፡፡ ለአንተ ፍቅር የህልውናህ ጥፁም መዓዛ ነው፡፡ ብቻህን ብትሆን እንኳን በአፍቃሪ ኃይል ትከበባለህ፡፡ የሞተ ነገርን ለምሳሌ ግዑዝ ወንበርን ብትዳስስ እንኳን ከእጅህ ፍቅር ይፈልቃል፡፡ ፍቅርህን የምትሰጠው ለምንም ወይንም ለማንም ሊሆን ይችላል::

በፍቅር ስሜት ውስጥ መሆን የለም እያልኩ አይደለም፡፡ ዳሩ ግን በፍቅር ስሜት ውስጥ መኖር የምትችለው የቀድሞውን ኢጎአዊ የፍቅር ግንኙነት አስተሳሰብህን በምትተውበት ጊዜ ነው:: ፍቅር ኢጎን መሰረት ያደረገ በሰዎች መሀል የሚመሰረት ግንኙነት ዓይደለም።

ሁለት ሰዎች አንድ ላይ እጅግ አፍቃሪ ሊሆኑ ይችላሉ:: አፍቃሪነታቸው በጨመረ ቁጥር በመካከላቸው የሚፈጠረው የፍቅር ግንኙነት ይጠፋል። አፍቃሪነታቸው በጨመረ መጠን፣ አንዳቸው ከሌላቸው የሚፈልጉትንና አንዳቸው በሌላቸው የሚጥሉት ተስፋ ይቀንሳል፡፡ ፍቅር ውስጥም ይገባሉ፡፡

በውል ሳይተዋወቁ ፍቅርን ብቻ እያሰቡ ሲወዳደሱ በመጨረሻ መወቃቀስ ይጀምራሉ፡፡ ለዚህም ነው ምንም ዓይነት ተስፋ ማድረግ እንደማያስፈልግ ልታስታውስ የምፈልገው:: ፍቅር የራስህ ውስጣዊ እድገት መሆኑን አውቀህ አፍቅር። ፍቅርህ ወደላቀ ብርሀን፣ ወደላቀ እውነትና ነፃነት ከፍ ያደርግሀል፡፡ ግን በኢጎ ላይ የተመሰረተ የፍቅር ግንኙነት አትፍጠር::

አንድ ነገር ብቻ አስታውስ፣ ፍቅር ማንኛውንም ዓይነት መጥፎ ነገር የማጥፋት አቅም አለው፣ ፍቅርን ወደ ኢጎአዊ ፍቅር ግንኙነት እንዲለወጥ ከፈቀድክለት ግን፣ ፍቅር ይጠፋና የጓደኝነት ስሜት በውስጥህ ያለው ውብ ባህሪ ሲሆን ጓደኝነት ግን ወደ ትስስር ያመራል።
ክፍል 3 ◉ Join us share◉●••
═════❥━━━❥═════
ነገን ላየው እጓጓለሁ!!! https://t.me/Deinstein_21
99 views14:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-29 15:50:10 ሌላው መታወስ ያለበት ነጥብ ደግም ራስህን ባርያ ሳታደርግ ሌላውን ሰው ባርያ ማድረግ አትችልም። ባርነት ባለሁለት ስለት ሰይፍ ነው:: አንደኛው የበለጠ ጠንካራ፣ ሌላው የበለጠ ደካማ ሊሆን ይችላል፣ ግን በሁሉም የፍቅር ግንኙነቶች ውስጥ አንደኛው አሳሪ ሌላው ታሳሪ ይሆናል። ከእሱ አንፃር ሲመለከተው እሱ አሳሪው አንተ ደግሞ ታሳሪ ትሆናለህ:: የሰው ልጅ ይህን በመሰለ ሀዘንና ሰቆቃ የመኖሩ ዋነኛ ሀቅና ምክንያት መካከል አንዱ ይኸው ነው፡፡

ጥላቻ ደግሞ ከፍቅርህ የጠነከረ ግንኙነት ይፈጥራል ምክንያቱም ፍቅርህ ከአንገት በላይ ነው፡፡ ጥላቻህ እጅግ ጥልቅ ነው:: ጥላቻህን የወረስከው ከእነስሳዊነት ባህሪህ ነው:: ፍቅርህ ለመጪው ሕይወትህ ያለህ ብቸኛ እምቅ ኃይልህ ነው፡፡ እውን የሆነ ክስተት ሳይሆን ወደፊት ፍሬ የሚያፈራ ዘር ነው:: ጥላቻህ ግን ሙሉ በሙሉ በተግባር ላይ የሚገኝ፣ እጅግ የጎለመሰ ያለፈው የብዙ ሺህ ዓመት ታሪክህ ህያው ቅርፅ ነው:: የሚያድግበት ጊዜና ቦታ የነበረው። ለውጡ መከሰት የሚጀምረው ግን በሰው ልጆች ላይ ነው፡፡

ግን ማንንም እኔን ከመጥላት ማገድ አልችልም ስለዚህ ማንም ሰው እንዲያፈቅረኝ ማድረግ አልችልም፡፡ ልገልፀው የምችለው ነገር ቢኖር ጥላቻም ሆነ ፍቅር የግንኙነት መልክ በሚይዝበት ጊዜ ንፅሕናውን እንደሚያጣ ብቻ
ነው፡፡ ክፍል 2 ◉ Join us share◉●••
═════❥━━━❥═════
ነገን ላየው እጓጓለሁ!!! https://t.me/Deinstein_21
3 views12:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-29 10:01:40 ከፍቅር ወደ አፍቃሪነት

ፍቅር ሁለት ፍፁም የተለያዩ እንደውም ሙሉ ለሙሉ ተቃራኒ ትርጉሞች ሊኖሩት ይችላሉ፡፡ አንዱ ትርጉም ፍቅር በኢጎ በተሞላ ፍቅር ግንኙነት መልኩ ሲገለጽ እና ሌላው ደግም ፍቅር በራሱ ህልውና ይዞ ሲገኝ ነው:: ፍቅር ወደ ኢጎአዊ ፍቅር ግንኙነት በሚለወጥበት ወቅት ባርነት ይሆናል፡፡ ምክንያቱም የምንጠብቃቸውና የሚጠበቁብን ነገሮች እንዲሁም መረበሽ እና ፍርሀትን ይፈጥሩብናል:: ከሁለቱም ወገንም እኔ እበልጥ ስሜት ይመጣል፡፡ የኃይል እሽቅድምድም ይሆናል:: ኢጎአዊ የፍቅር ግንኙነት ትክክል አይደለም፡፡ ፍቅር ህልውና ይዞ ሲገኝ ግን ሙሉ በሙሉ የተለየ ነገር ይሆናል፣ ስታፈቅር ከፍቅር ሌላ የፍቅር ግንኙነት እየፈጠርክ አይደለም ማለት ነው:: ፍቅርህ እንደ አበቦች ጥዑም መዓዛ ይሆናል። ኢጎአዊ የፍቅር ግንኙነት አይፈጠርም፣ ይህን አድርግ፣ ባህሪህ እንዲህ ይሁን አይልህም፡፡ ከአንተ ምንም አይፈልግም። ያካፍላል። በማካፈሉም ምንም ሽልማት አይፈልግም፡፡ ማካፈሉ በራሱ ሽልማት ነው፡፡

ፍቅር ለአንተ እንደ አበቦች መዓዛ በሚሆንበት ጊዜ ታላቅ ውበት ይኖረዋል ከሰብዓዊነት በላይ የመጠቀ መለኮታዊ ነገር ይኖረዋል።

ፍቅር ብቻውን ከመጣብህ ምንም ልታደርገው አትችልም፡፡ በማንኛውም ሰው ላይ አሳርን አያመጣም አንተም በማንኛውም ሰው እንድትታሰር አይፈቅድም።

ግን ከልጅነት አንስቶ ኢጎአዊ የፍቅር ግንኙነቶችን የመፍጠር ልምድ አለህ፡፡ ከማታውቀው ወንድ ጋር የአባትና የልጅ ግንኙነት ትፈጥራለህ። አባትህ መሆኑን በፍፁም ርግጠኛ ልትሆን አትችልም፡፡

አንድ የሰዎችን መዳፎች በመመልከት ዕጣ ፈንታቸውን ስለሚተነብይ ሰው የሰማሁት ታሪክ አለ፡፡ በእጅ መዳፍ ንባብና በአስትሮሎጂ በመሳሰሉት እንዲሁም በእግዚአብሔርም የማያምን አንድ ወጣት ወደዚሁ ሰው ይሄድና፣ «ሳይንስህ ትክክል ከሆነ እጄን አንብብና አባቴ የት እንደሚገኝ ንገረኝ አለው፡፡»

አዋቂውም መዳፉን ተመልክቶ እንዲህ አለው «አባትህ አሳ እያጠመደ ነው::» ወጣቱ ኢአማኒ ሳቀ፡፡ «እኔ የምለው ይህንኑ ነው፤ የማይረባ ሥራ ነው:: አባቴ ከሞተ ሶስት ዓመት ሆኖታል፤ ዛሬ እንዴት አሣ ለማጥመድ ይሔዳል?

አዋቂውም ሲመልስ፣ «ይህ እኔን አያገባኝም፣ እውነቱ ግን ያ የሞተው ሰው አባትህ ያለመሆኑ ነው፡፡ ትክክለኛ አባትህ አሳ እያጠመደ ነው:: ወደ እናትህ ሂድና ጠይቃት፡፡ ታማኝና እውነተኛ ከሆነች የሞተው ሰው አባትህ እንዳልሆነ ትነግርሀለች:: አንተ ግን አባትህ ነው ስለተባልክ ከእሱ ጋር የአባትና የልጅ ፍቅር ግንኙነት ፈጥረሀል።

ሕይወታችሁ በሙሉ በብዙ ዓይነት ኢጎአዊ ግንኙነቶች የተሞላ ነው:: ይህ መሰል ግንኙነቶች ደግሞ እውነትም ይሁን ሀሰተኛ፣ እጅግ ውስብስብ የሆነ ስነ-ልቦናዊ ባርነትን ይፈጥራል። ወይ ሌላውን ባርያ ታደርጋለህ፡፡ ወይንም ራስህ ባርያ ትሆናለህ፡፡ ምንጭ ፦ ነፃነት (ኦሾ)
ትርጉም ፦ ዘላለም ንጉሴ ◉ Join us share◉●••
═════❥━━━❥═════
ነገን ላየው እጓጓለሁ!!! https://t.me/Deinstein_21
99 views07:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-28 17:17:08

172 views14:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ