Get Mystery Box with random crypto!

Deinstein_21

የቴሌግራም ቻናል አርማ deinstein_21 — Deinstein_21 D
የቴሌግራም ቻናል አርማ deinstein_21 — Deinstein_21
የሰርጥ አድራሻ: @deinstein_21
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.98K
የሰርጥ መግለጫ

@Deinstein_21
.
.

Contact👉0913617275 and 0964742005 or @Albetredeinstein

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-01-17 23:53:11 መጽሐፈ አክሲማሮስ

@eotcLibrary
65 views20:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-17 21:28:48

25 views18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-17 12:56:26
ዛሬ ማታ በDeinstein_21 የyoutube channel ላይ ይጠብቑኝ
119 views09:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-17 12:55:26 መንጋነትን ተፀየፍ

ሲግመን ፍሮይድ፣ አርኪመድስ፣ ኒቼ፣ ቻርለስ ዳርዊን፣ ጋሊሊዮ፣ ሶቅራጥስ፣ ቡድሃ፣ ቶማስ ኤዲሰን፣ ቫን ጎ፣ የእኛው ሀገር ፈላስፋ ዘርዓያዕቆብ ... ሌሎችም ሌሎችም በየስርቻው በየጉራንጉሩ በእኛም ሀገር ጭምር አሉልህ፡፡ አብዛኞቹ በዘመናቸው የተወገዙ ወይ አድማጭ ያጡ ነበሩ፡፡ ዛሬ እግርህን በጀብደኝነት አንፈራጠህ ቆመህ ሰልፊ (ራስ በራስ ፎቶ) የምትነሳበትን ስልጣኔ የመሰረቱት ግን እኔው ዘመንን የቀደሙ የትናንት መሰሎችህ ነበሩ፡፡ ካምቤል ኢጁጋርጁክ የተሰኘ የካናዳ ካሪቦ ኢስኪሞ ጎሳዎችን መንፈሳዊ መሪ አባባል ይጠቅሳል፡፡ ኢጁጋርጁክ እንዲህ አለ....

"እውነተኛ ጥበብ ከሰው ልጅ ተሰውራ ትገኛለች፡፡ በታላቅ ሕመምና የብቻ አርምሞ ካልሆነ የሚደረስባት አይደለችም፡፡ ፈተናን መጋፈጥና ብቻነት ግን ወደዚህ ድብቅ ዕውቀት መገኛ ስውር ቦታ አዕምሮን ይመራሉ፡፡"

የምንኖረው ግን በጅምላ በሚመለክበት፣ በጅምላ በሚወገዝበት፣ በጅምላ በሚኮነንበት፣ ሽያጩም፣ ዘረፋውም፣ ግድያውም፣ ቀብሩም ጅምላ ሆኖ ተነጥሎ መቆም ወንጀል በሆነበት ማኅበረሰብ ውስጥ ነው፡፡

እናስ በዚህ ሂደት ከመንጋው የመነጠል፣ ከዘመን የመጣላት፣ ከትውልድ የመኳረፍ አዝማሚያ የሌለው ጠቢብ የመንጋውን መፈክር በውብ ቃላት ሸላልሞ ከማተም በስተቀር ረብ ያለው ሀቲት ሊወጣው ይችላልን? ምንኖረውን የሆነውን ለመጻፍ፣ ለመዝፈን፣ ለማቅለም፣ ለማሰማመር ብዙ መጣር አርቲስት መሆን ያስፈልጋል እንዴ? በየትኛውም ዘመን ተወለድ (በእኛም ዘመን ይሁን) ብዙዎች ከሚስማሙበት ከተለየህ፣ ብዙዎች የሚያደንቁት ካልመሰጠህ፣ ብዙዎች በጅምላ የሚጠሉትን ካልጠላህ ውግዘት ውርደት፣ ግዞት ይደርስብሃል፡፡ ምክንያቱም አንተ የሚቀጥለው ትውልድ አባል ነህ፡፡

የእኛን ነገር እንኳን ተውት፣ ተውት አዲስ አተያይ ማመንጨቱን፣ የሚቀጥለውን ትውልድ ትልም የማርቀቅ ቅብጠቱን ተውት... ተውት፡፡ እኛ ከዘመንና ከትውልድ መኳረፍ ያቃተን፣ ዘልማዳዊ የነተበ ሕይወት የማይሰለቸን፣ አንሰን አንሰን የምናሳንስ፣ በአጥንት እንደሚጣሉ የተራቡ ውሾች እርስ በእርስ የምንናከስ ሕዝቦች ነን፡፡

ለብቻ መቆም መቻል ግን ውበት ነው፡፡ ፅናት ነው፡፡ ጥንካሬ ነው፡፡ ለብቻ መቆም(solitude) መሟላት እንጂ መነጠል (isolate) አይደለም፡፡ መነጠል ብሎ ነገር የለም፡፡ የምትነጠለው ጉልህ ስብዕና አጥተህ ተጀምለህ የተቆጠርክ ዕለት ነው፡፡ እንደ ጉሬዛ ከዛፍ ዛፍ እየዘለልክ ብትኖር እንኳን ከሰው እንጂ ከምልዓተ ዓለሙ መነጠል አትችልም፡፡ ማንም ሁን ከየትም ና አንተ የምልዓተ ዓለሙ የልብ ትርታ ነህ። አንተ አንተን መሆን ከቻልክ ያለ አንተ ዓለሙ ይጎድላል፡፡ ═════❥━━━❥═════
ነገን ላየው እጓጓለሁ!!! https://t.me/Deinstein_21
110 views09:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-14 21:28:35

69 views18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-14 18:50:34 #ነጻነትህን_አሳልፈህ_አትስጥ

“አንድ ሰው ለመንገደኛ ሰው ከአካልህ አንዱን (ለምሳሌ እጅህን) አንስቶ ቢሰጠው ትበሳጫለህ። ሆኖም የአንተን አእምሮ ለመጣው ለሄደው ሁሉ ትሰጣለህ፤ ብዙ ሰው አንተን ያጠቃሃል፤ በዚህም ትበጠበጣለህ፤ ትቸገራለህ… ይህስ አያሳፍርህም?”
#ኤፒክቴተስ

ሳናስበውም ቢሆን አካላችንን እንጠብቀዋለን። ሰዎች እንዲነኩንም ሆነ እጃችንን ይዘው እንዲያሽከረክሩን አንፈቅድላቸውም። ሆኖም ወደ አእምሯችን ስንመጣ ቁጥጥራችን ይላላል። በፍቃደኝነትም ለፌስቡክ፣ ለቴሌቪዥን ወይም ለሌሎች ሰዎች ለሚያስቡት፣ ለሚናገሩት፣ ለሚያደርጉት ነገር አሳልፈን ሰጥተነዋል። ስራ ልንሰራ ተቀምጠን ጥቂት እንኳ ሳንቆይ ራሳችንን ኢንተርኔት ላይ እናገኘዋለን። ከቤተሰብ ጋር እንቀመጣለን፤ በደቂቃዎችም ስልካችንን ፍለጋ እጃችንን እንሰዳለን። ሰላም በተሞላበት መናፈሻ እንቀመጣለን ሆኖም ወደ ውስጣችን ከመመልከት ይልቅ አላፊ አግዳሚውን እየገላመጥን እንዳኛለን።

በእኛ ላይ ምን ችግር እንዳለ ሁሉ አናውቅም። በድርጊታችን ውስጥ ምን ያህል ብክነት እንዳለ አናስተውልም፤ ምን ያህል ደካማ እንደሆንን፣ ምን ያህል ራሳችንን እንደምንረብሽ አናስተውልም። ከዚህ የባሰው ደግሞ ማንም እንዲህ እንድንሆን ያላስገደደን መሆኑ ነው፤ ሁሉንም ችግር የፈጠርነው በራሳችን እጅ ነው።

ለስቶይኮች ይህ አይሰራም። ዓለም የእኛን ሰውነት መቆጣጠር እንደምትችል ያውቃሉ- ወደ እስር ቤት ልንጣል እንችላለን ወይም አገር ሰላም ብለን በወጣንበት ዶፍ ዝናብ ሊወርድብን ይችላል። በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን በእኛ ቁጥጥር ስር የሚገኘው አእምሯችን ነው። ልንጠብቀውም የተገባ ነው። በአእምሮህ ላይ ቁጥጥርን ማድረግህ ከሁሉም የላቀ ሃብት ነው። share◉●••
═════❥━━━❥═════
ነገን ላየው እጓጓለሁ!!! https://t.me/Deinstein_21
125 views15:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-14 18:44:41 https://www.youtube.com/channel/UCICuPVqY5Ka5s8Fgyz0DpBg/community
115 views15:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-11 09:27:37 ከሚያስከፉህ ብዙ ነገሮች ይልቅ አሁን የሚያስደስትህን አንድ ትንሽ ነገር ፈልግ!

በአሁኑ ጊዜ የህይወትህ ጥራት የሚወሰነው በለበስከው ልብስ፣ ባለህ የትምህርት ብቃት፣ በመጣህበት ቤተሰብ ወይም ባለህ የባንክ ሂሳብ ሳይሆን በውስጥህ ባለው ሰላም እና ደስተኛ በመሆንህ ላይ ነው።

በእርግጠኝነት፣ ምግብ የሌለው እና ለመኖር መሰረታዊ ፍላጎቶችን የተነፈገ ሰው በአካል ሊሰቃይ ይችላል።

ስለዚህ ለእንደዚህ አይነት ሰው በመጀመሪያ እነዚህን ነገሮች መስጠት ይኖርብናል።

እውነታው ግን እንደዛ አይደለም፡፡

ለአብዛኞቻችን ደስታን ፍለጋ ማለቂያ የሌለው ዝርዝር ማዘጋጀት ነው ከደስታ ጋር የሚያገናኘን የሚመስለን።

ወዳጄ... ዝርዝርህ ላይ ተተክለህ አትቅር!

በመንገድ ላይ በእግሩ ከሚሄደው ሰው ይልቅ መኪና የሚያሽከረክር ሰው ይበልጥ ደስተኛ እንደሆነ ታስባለህ?

አይደለም!!!

መደሰት የሚወሰነው ባለህ ነገር ሳይሆን በዚያ ቅጽበት ባሉበት ሁኔታ ነው።

አሁን ባለህበት ሁኔታ ተደሰት፡፡ በምንም ሁኔታ ውስጥ ብትሆን ተደሰት፡፡ ደስታ ደስታን ይጠራልና ተደሰት፡፡

ከሚያስከፉህ ብዙ ነገሮች ይልቅ አሁን የሚያስደስትህን አንድ ትንሽ ነገር ፈልግ፡፡

እንደ ህጻን ሁን፡፡ አሁን ባለህ ነገር ሁሉ ተደሰት!

አቦ የደስታ ቀን እመኝልሀለሁ
55 views06:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-10 21:25:33 ሔዋን በምድር ላይ የመጀመሪያዋ ሴት አይደለችም @MrBeast


156 views18:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-10 16:11:49 አሜሪካዊው ቢሊዬነር ስቲቭ ጆብስ በህይወቱ መጨረሻ ሰዓት ላይ ያስተላለፈው አስደናቂ መልዕክት
((ስቲቭ ጆብስ በ56 አመቱ ያረፈ አሜሪካዊ ቢሊዬነር ሲሆን ህይወቱ ያለፈው በካንሰር በሽታ ነው))
በንግዱ አለም ውስጥ የመጨረሻከፍታ ጫፍ የሚባለው ቦታ ደርሻለሁ፣ ይሁን እንጂ ከዚህ ሁሉ ሀብት ደስታን ማግኘት አልቻልኩም። በልፋቴ ካከማቸሁት ሃብት ያገኘሁት ደስታ እዚህ ግባየማይባል ነው፣
አሁን፣በህይወቴ የመጨረሻው ሰዓት አካባቢ፣አልጋ ላይ ሆኜ ያሳለፍኩትን ነገር ሁሉ ወደሗላ ሳስበው ፣ እኮራበት የነበረው ሀብቴና ዝናዬ ከንቱ እና ትርጉም አልባ እንደሆነ
ስማኝ ልጄ !!!!
1. ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትውደቅ ማለት አይደለም ወድቀህ መነሳትንም ልመድ ማለት እንጂ!!!!
2. ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም ሌሎችን ለመስማት ጆሮ ስጥ ማለት እንጂ!!!!
3. ሆዳም አትሁን ማለት አትብላ ማለት አይደለም በሰው ሀቅ አትለፍ ማለት እንጂ!!!!
4. አትቆጣ ማለት ስሜት አይኑርህ ማለት አይደለም ከቁጣ ቶሎ ተመለስ ማለት እንጂ!!!!
5. ይቅርታ አድርግ ማለት አልተጎዳህም ማለት አይደለም በሆድህ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ስለሆነ እንጂ!!!!
6. ጠላትህን ውደድ ማለት ጠላት ጥሩ ነው ማለት አይደለም ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር ስለሚያሸንፍ!!!
7. ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ማለት አይደለም ባለህ ነገር ደስ ይበልህ ማለት እንጂ!!!!
8. ስራህን ውደድ ማለት የምትሰራው ስራ ጥሩ ነው ማለት አይደለም ነገ ጥሩ ስራ እንዲኖርህ ዛሬ የምትሰራውን ስራ ውደድ ማለት እንጂ!!!!
9. ወረኛ አትሁን ማለት አታውራ ማለት አይደለም ምንም ስለማታውቀው ነገር አታውራ ማለት እንጂ!!!!
10. ትሞታለህ ማለት አትስራ ማለት አይደለም ምንም ቁም ነገር ስትሰራ አትሙት ማለት እንጂ!!!!
11. ብቸኛ አትሁን ማለት ሮጠህ ትዳር ያዝ ማለት አይደለም ልብህን ግዜህን ያለህን ሁሉ አሳልፈ ለመስጠት ዝግጁ ሁን ማለት እንጂ!!!!
12. እውነተኛ ሁን ማለት ሰዎች ባሉበት ብቻ እውነትተናገር ማለት አይደለም ለራስህም የእውነት ኑሮ ኑር ማለት ማለት እንጂ!!!!
13. አትጣላ ማለት ከሰው ጋር አትኑር ማለት አይደለም ቂም ይዘህ አትቆይ ማለት እንጂ!!!!
14. ኩራተኛ አትሁን ማለት አትዘንጥ ማለት አይደለም ሌሎችን አትናቅ ማለት እንጂ!!!
15. ቆንጆ ነህ ማለት ከሌሎች የተሻልክህ ነህ ማለት አይደለም አምሮብሃል ማለት እንጂ!!! ◉ Join us share◉●••
═════❥━━━❥═════
ነገን ላየው እጓጓለሁ!!! https://t.me/Deinstein_21
223 views13:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ