2023-03-18 10:12:49
መጋቢት 09/2015 ዓ.ም
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በግብርና ሣይንስ ኮሌጅ የ2015 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች የሞዴል ፈተና በኦንላይን ተሰጠ፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት ጥራቱ ላይ ትርጉም ያለዉን ለዉጥ ለማምጣት የጀመረዉን አቅጣጫ በመከተል የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ሣይንስ ኮሌጅ ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ አይሲቲ ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር እና የኢ-ሌርንግ ሲስቴም በመጠቀም ለአራተኛ አመት ተማሪዎች የ1ኛ ዙር የሞዴል ፈተና በኦንላይን መስጠቱን አሳዉቋል፡፡
የግብርና ሣይንስ ኮሌጅ ዲን የሆኑት መ/ር ንጉሴ ጎዳና እንደገለጹት የሞዴል ፈተና በኦንላይን ለተማሪዎቹ መሰጠቱ ጥቅሙ ከኩረጃ ነፃ በሆነ መንገድ ማለፍ እንዲችሉ ከማድረጉም በላይ በቀጣይ ለሚፈተኑት የመዉጫ ፈተና በራስ የመተማመን ሁኔታን እንደሚፈጥር አስረድቷል፡፡
በተያያዘ መልኩ መ/ር ንጉሴ እንደገለጹት ቀደም ሲል ተማሪዎች ፈተናዉን ተፈትነዉ ዉጤት ለማየት የሚቆዩበትን ጊዜ በማስቀረት ዉጤታቸዉን ወዲያዉኑ እንድያዉቁት ከመርዳቱም በላይ አንዳንድ ጊዜ የሚፈጠረዉን የእርማት እና የዉጤት አጠነቃቀር ስህተትን እንደሚያስቀር የተናገሩት የኮሌጁ ዲን ከወጪ አንፃርም ለፈተናዉ ዝግጅት ልወጣ የነበረዉን የጽፌት መሣሪያ እና ተያያዥ ጉዳዮችን ወጪ ማዳን የተቻለ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡
ተማሪዎች ለፈተና እንድዘጋጁ ከማድረግ አንፃርም በፈተናዉ ዙሪያ አስፈላጊዉ ገለፃ፤ቲቶሪያል ትምህርት እና የተለያዩ ሞጁሎች ተዘጋጅቶ መሰጠታቸዉንም ጠቁመዋል፡፡
በመጨረሻም እንደ ኮሌጁ ዲን ገለፃ ይህንኑ በትምህርት ጥራት ላይ የተጀመረዉን መልካም ሥራ በተጠናከረ ሁኔታ ለማስቀጠል እንዲቻል የተወሰኑ ተግዳሮቶች ማለትም የኮምፒዩተር እጥረት ፤የኢንተርኔት መስመር ዝርጋታ በቂ አለመሆን እና የመብራት መቆራረጥ ችግሮች እያጋጠሙ ስለሆነ የሚመለከታቸዉ አካላት አስፈላጊዉን ትኩረት በመስጠት ችግሩ የሚፈታበትን መንገድ እንድያመቻቹ ጠይቀዉ የሁለተኛ ዙር የኦንላይን ፈተና በቀጣይ ሚያዚያ ወር ዉስጥ እንደሚሰጥ መግለፃቸዉን ለመዘገብ ተችሏል፡፡
ለላቀ ለዉጥ እንተጋለን!
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
2.4K viewsTesso Dido, 07:12