Get Mystery Box with random crypto!

Bule Hora University

የቴሌግራም ቻናል አርማ bulehorauniversity — Bule Hora University B
የቴሌግራም ቻናል አርማ bulehorauniversity — Bule Hora University
የሰርጥ አድራሻ: @bulehorauniversity
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 15.23K
የሰርጥ መግለጫ

Bule Hora University Official telegram

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-20 16:04:17
ሐምሌ 13/2015 ዓ.ም
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ሙያዎች ሲያሰለጥናቸዉ የቆየዉን ተማሪዎች ለ10ኛ ዙር አስመርቋል፡፡

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በሀገራችን በቅርብ ጊዜ ከተቋቋሙት ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደብ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ በ2004 ዓ.ም የመማር ማስተማር ሥራዉን በመጀመር በዛሬዉ ዕለትም ሐምሌ 13/2015 ዓ.ም ለ10ኛ ዙር በተለያዩ ሙያዎች ሲያሠለጥናቸዉ የቆየዉን በመጀመሪያ ድግሪ 907 ተማሪዎች በሁለተኛ ድግሪ 392 በድምሩ 1299 ተማሪዎችን የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፍቃዱ ወ/ማርያምን ጨምሮ የምዕራብ ጉጂ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ አባል እንዲሁም የዕለቱ ክብር እንግዳ አቶ አዱላ ህርባዬ፤አቶ አህመድ አደም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምሪያ ኃላፊ፤የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ም/ፕሬዝዳንቶችና የሴኔት አባላት፤አባገዳዎችና የኃይማኖት አባቶች እንዲሁም የተመራቂ ተማሪ ቤተሰቦች በተገኙበት በዩኒቨርሲቲዉ ዋና ግቢ ኦዳ አዳራሽ በደማ ሁኔታ አስመርቋል፡፡
**********ቡሌ ሆ ዩኒቨርሲቲ*********
4.1K viewsEyerus Ka, 13:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-20 16:02:10
Adoolessa 13/2015
Yuunivarsiitiin Bulee Horaa Barattoota Ogummaalee Adda Addaatiin Barsiisaa Ture Marsaa 10 ffaaf Eebbisiise.

Yuunivarsiitichatti barattoonni ogummaa garaa garaatiin barataa turan digirii jalqabaa 907 fi digirii lammaffaa 392 wolumatti barattoonni 1299 guyyaa har’aa bakka Obboo Ahimad Adem Itti Gaafatamaan Dhabbilee Barnoota Olaanoo akkasumas Obboo Adulaa Hirbaayyee Bulchaan Bulchiisa Godina Gujii Lixaa fi Miseensa Boordii Yuunivarsiitii Bulee Horaa fi Abbootiin Gadaa argamanitti bifa how’aan eebbifamaniiru.

Saganticharraatti ergaa baga gammaddanii kan dabarsan Pireezidaantiin Yuunivarsiitichaa Dr Fiqaaduu Woldemaariyaam milkii injifannoo qorumsa ba’umsaa si’a jalqabaaf kan ittiin milkooftan isin gootota, waan ta’eef baga ittiin isin gahe jechuun, barnoota barattan kanaan ifirra dabartanii biyyaaf akka tajaajiltan abdii cimaafi imaanaa qabdu jechuun dhaamaniiru.
Yuunivarsiitii Bulee Horaa
4.1K viewsEyerus Ka, 13:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-10 14:15:55
ለሚመለከተው ሁሉ

እንደሚታወቀው ዩኒቨርሲቲያችን የፕሬዚዳንትነት ክፍት የሥራ መደብ አምልካቾችን አወዳድሮ ለመቅጠር ከቀን 20/10/2015 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት አሥራ ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያ በተለያዩ ሚዲያና ጋዜጦች እስካሁን እያሳወጀ መቆየቱ ይታወቃል።
በመሆኑ ለቦታው ብቁ የሆናቹ አመልካቾች ማስታወቂያው የሚያበቃበት ቀን 4/11/2015 ዓ.ም ከቀኑ 11:30 መሆኑን አውቃችሁ ማስታወቂያ ላይ በተገለፁት አድራሻዎች አስፈላጊውን የትምህርት ማስረጃዎቻቹን እንድታቀረቡ እናሳስባለን::

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ቅጥር እና ምረጫ ኮሚቴ
8.8K viewsEyerus Ka, 11:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-10 14:10:48
ሐምሌ 03/2015 ዓ.ም
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ለ2015 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች የሚሰጠው የመውጫ ፈተና (Exit exam) መሰጠት ተጀምሯል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ከዩኒቨርሲቲ የሚመረቁ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና መውሰድ አለባቸዉ በሚል ያስተላለፈውን መመሪያ ተከትሎ በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲም ፈተናው የተጀመረ ሲሆን ዛሬ ማለትም ሐምሌ 03/2015 በጠዋቱ ፈረቃ 333 ተማሪዎች ለፈተና የተቀመጡ ሲሆን በከሰዓቱ ፈረቃም 416 ተማሪዎች ይፈተናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
7.3K viewsEyerus Ka, 11:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-07 19:30:08
Waxabajjii 30/2015

Yunivarsiitii Bulee Horaatti Barattoonni sagantaa Fooyya’ina Ga’umsaa (Remedial Program) xummuruu fi Barattoonni Inistitiyuutii Fayyaa Qorumsa Ba’umsaa (Exit Exam) Fudhachuu Eegaluu
=============////================
Yunivarsiitii Bulee Horaatti Barattoonni Sagantaa Fooyya’ina Ga’umsaa (Remedial Program)tiin gara Yuunivarsiitii Bulee Horaatti Ramadaman Guyyaa hardhaa karaa nagaa qabeessaan xumuraniiru. karaa biraatin Inistitiyuutii Fayyaatti barattoonni eebbifamtoota ta’an fi barattoonni ogummaa fayyaatiin baratan iddoolee garaagaraa irraa ramaddii ministeera fayyaatiin qorumsa ba’umsaa qoramuuf gara Yuunivarsiitichaa dhufan guyyaa har’aa qorumsa ba’umsaa Yuunivarsiitichaa keessatti haala gaariin fudhachuu eegalaniiru. Barattoonni ogummaa fayyaatiin qoramuuf ramadaman kunniin, muummeewwan Saayinsii Fayyaa kanneen akka Medicine, Public Health, Pharmacy, Laboratory Science, Nurse fi Midwifery kan barataa turaniidha.
Yuunivarsiitii Bulee Horaa
7.7K viewsEyerus Ka, 16:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 17:01:16
ሰኔ 02/2015
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ማህበራዊ ሣይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ በሱሮ ወረዳ ለሚገኝ ሜዲባ በርጉዳ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ለአቅመ ደካማ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡
ድጋፉ የተገኘዉ የማህበራዊ ሣይንስና ሥነ-ሰብ ኮሌጅ ዉስጥ መ/ር የሆኑት ዶ/ር Sinarayar Britto ካናዳ ሀገር ከሚገኝ OFT (Ontario Teachers Federation) ጋር በመነጋገር የተገኘ ሲሆን የኮሌጁ ዲን የሆኑት መ/ር ሾልሳ ጂሎ በት/ቤቱ በመገኘት የትምህርት ቁሳቁስ በማስረከብ ለተማሪዎቹም መልዕክት አስተላልፏል፡፡
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
2.9K viewsEyerus Ka, 14:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 19:19:52
ሰኔ 01/2015
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።
ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ሁሉም ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና መውሰድ አለባቸው በሚል ትምህርት ሚኒስተር ያወረደውን መመሪያ መሠረት በማድረግ እና ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ አስፈላጊው ሥራዎች እየተሠሩ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡ስለሆነም እስከዛሬ በነበረው ሂደት አፈፃፀሙ በምን ደረጃ ላይ እንዳለ ለመገምገም የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃኑ ለማ እና ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ከዩኒቨርሲቲው ኮሌጅ ዲኖች፣የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች እና ከየትምህርት ክፍሎች የተወከሉ የተማሪ ተጠሪዎች ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
3.6K viewsEyerus Ka, 16:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-03 14:48:56 Dear BHU Communities,

We want to let you know that the application period for the ITEC programme for the academic year 2023–2024 has started.To learn more and view the prerequisites for the applications, please click the link provided below. Please submit your application as soon as you can. 
        Internationalization       
         Directorate Office

ITEC :Indian Technical and Economic Cooperation
https://www.itecgoi.in/upcoming_courses
6.3K viewsEyerus Ka, 11:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 20:42:31 ግንቦት 25/2015 ዓ.ም
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ 3ኛ ዙር አለም አቀፍ ኮንፍረንስ ተካሄደ።

በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት በምርምርና ስርፀት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ‹‹አርብቶ አደርና የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም እንዴት ይቻላል?››በሚል ርዕስ በ25/09/2015 ዓ.ም 3ኛው ዙር አለም አቀፍ ኮንፈረንስ በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ ኦዳ አዳራሽ ተካሂዷል::
በምርምር ኮንፍረንሱ ላይ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፍቃዱ ወ/ማርያምን ጨምሮ ም/ፕሬዝዳንቶች፣የገዳ አባቶች፣የዩኒቨርሲቲው ምሁራን ፣አለም አቀፍ አጥኚዎች የትምህርት ባለሙያዎች፣ፖሊስ አርቃቂዎች፣ሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ ያሉ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት እና ሌሎችም ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
የኮንፍረንሱን አጀማመር በተመለከተ በአካባቢው ባህል መሠረት በአባገዳዎች ምርቃት የተጀመረ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው የምርምር እና ስርፀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፍፁም ደምሴ በዚህ ታላቅ ኮንፈረንስ ላይ ለተገኙት ተሣታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ የጥናትና ምርምሩ ዋና ዓላማ ሣይንሳዊና በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራር በማበጀት የሰዎችን ኑሮ የተቃና እንዲሆን ማድረግ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
አቶ ፍፁም አያይዘውም ዩኒቨርሲቲው አራት ዋና ዋና የልህቀት ማዕከላትን መሠረት አደርጎ የሚሠራ መሆኑን በመጥቀስ በዛሬው ዕለት ለኮንፈረንሱ የተዘጋጀው ርዕስ ዩኒቨርሲቲው ትኩረት ሰጥቶ ከሚሰራባቸው ከግብርና ጋር የተገናኘ እና ወቅታዊ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በሌላ መልኩ በኮንፍረንሱ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የዩኒቨርሲቲው ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ትንሣኤ ታምራት በተመሳሳይ መልኩ ዩኒቨርሲቲው በአራት ዋና ዋና የልህቀት ማዕከላት ማለትም በማዕድን፣በጤና፣በግብርና እና ሀገር በቀል ዕውቀትን መሠረት አደርጎ የሚሠራ መሆኑን በማስረዳት የአየር ንብረት ለውጡ በተለይም በጉጂና ቦረና አካባቢ እያደረሰ ያለው ተጽዕኖ ከባድ በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ዶ/ር ትንሣኤ አያይዘውም ይህ በዓይነቱና በይዘቱ ልዩ በሆነው ኮንፍረንስ ላይ አርብቶ አደሩ የአየር ንብረት ለውጥን በመቋቋም ተጠቃሚ በሚሆኑባቸው ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ መስራቱ አስፈላጊ መሆኑን በመጠቆም በዕለቱ የተጀመረው ኮንፍረንስ የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ እንዳልሆነ በመጥቀስ የተጋበዙት እንግዶችም ወደ መጡበት ሲመለሱ ይህኑንን አሠራር በማስፋት ለወደፊቱ የተጠናከረ ግንኙነት እንደሚፈጥር አስረድተዋል፡፡
በኮንፈረንሱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፍቃዱ ወ/ማርያም የተገኙት እንግዶችን እና የኮንፈረንሱ አዘጋጆችን በማመስገን በምርምሩ ዙሪያ ኮንፈረንስ መደረጉ ሁለት ዋና ዋና ጠቃሜታዎች ማለትም በአሁኑ ሰዓት የአየር ንብረት ለውጥ እያደረሰ ያለውን ጉዳት የምንገነዘብበትና አዲስ መረጃ የምናገኝበት መሆኑን በመጠቆም በጋራ በመሥራት አርብቶ አደሩን በመደገፍ ተጠቃሚ መሆን በሚችልበት የመፍትሄ ሀሳቦች ዙሪያ ውይይት የሚደረግበት መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ዶ/ር ፍቃዱ ይህን መሰል ኮንፍረንሶች ላይ በመገኘት በጋራ መወያየቱ ጠቀሜታው ያለንንና ያጣናቸውን ነገሮች ለመለየት ከማስቻሉም በላይ በአሁኑ ሰዓት የአየር ንብረት ለውጡ በተለይ በአርብቶ አደሩ አካባቢ ምን ያክል ጉዳት እያደረሰ እንዳለ ለመረዳት የሚያስችል ስለመሆኑም ጠቁመዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ አክለውም የምርምር ኮንፈረንስ መዘጋጀቱ ለማህብረሰቡ በተለያዩ ችግሮች ዙሪያ የመፍትሔ ሀሳቦችን በማጋራት ደረጃ የምሁራን ሚና ከፍተኛ መሆኑንም ተናግረዋል።
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
6.3K viewsEyerus Ka, 17:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 03:58:44 ለሁሉም የዩንቨርሲቲያችን ማህበረሰብ በሙሉ
ጉዳዩ፡- የምርምር ጉባኤ ላይ እንድትሳተፉ ስለማሳወቅ ይሆናል፡፡
በምርምርና ስርፀት ዳ/ዳይሬክተር አስተባባሪነት 3ኛው አለም ዓቀፍ የምርምር ጉባኤ “Pastoralism and Climate Change resilience” በሚል ርዕስ በቀን 25/09/2015 ዓ.ም (አርብ) ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ በኦዳ መሰብሰቢያ አዳራሽ ስለሚካሄድ እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል፡፡
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
5.6K viewsZedo FM 99.0, 00:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ