Get Mystery Box with random crypto!

ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን

የቴሌግራም ቻናል አርማ binigirmachew — ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን
የቴሌግራም ቻናል አርማ binigirmachew — ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን
የሰርጥ አድራሻ: @binigirmachew
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.78K
የሰርጥ መግለጫ

👉*የስነ-ልቦና የምክር አገልግሎት በአካል፣ በስልክ ወይም በቴሌግራም(Online,,Video Call) አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ።
እዚህ ላይ ሙሉ መረጃ ማግኘት ይችላሉ
👇👇👇👇👇👇
@sewhunkesewumsewhunbot
ወይም ይደውሉ በሥራ ሰዓት
251927707000

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-01-27 08:38:35 በሴቶች ላይ የሚደርስ የአዕምሮ ጭንቀት

ሰው በሕይወቱ የሚያጋጥመውን ሁሉ አስቀድሞ የማወቅ ሀይል ስለ ሌለው ፣
የማይመርጣቸውና የማይፈልጋቸው ልዩ ልዩ "ደስታ ገፋፊዎች" የሆኑ ነገሮች ሊያጋጥሙት ይችላሉ።

የሰው የማያቋርጥ ጥረቱ ዘላቂ የሆነውን ደስታ ለማግኘት ቢሆንም ፣ የጠበቀውን ደስታ ሁልጊዜ የማግኘት ችሎታና አቅም የለውም።

ለአንዳንድ ሰዎች "ደስታ" የሚወሰነው ወይንም "ነው"፣ "አይደለም" የሚል ወሳኙ የሰውየው አስተያየትና አመለካከት ነው።

ያም ሆነ ይህ ፣ ሰው የጠበቀውን "ደስታ" ማግኘት ሲያቅተው የመንፈስ ሀዘን ወይንም ጭንቀት ውስጥ ይገባል።

እርግጥ ነው ማንም በኑሮ ውስጥ "ደስታ ገፋፊ" ከሆኑ ነገሮች የማምለጥ ሀይል የለውም።

ስለዚህ በኑሮ ውስጥ የሚያጋጥሙትን ማንኛቸውንም ዓይነት "ደስታ ገፋፊ" የሆኑትን ነገሮች ታግሶ ማለፍ ካልቻለ፣ ደስታ የሸሸው ሰው ይሆናል።

ደስታ ማጣት ደግሞ የአዕምሮ ጭንቀት መግቢያ ቀዳዳ በመሆኑ ፣ በወቅቱ እርዳታ ካላገኘ ፣ በአዕምሮ ጭንቀት ውስጥ ለረጅም ጊዜ ይኖራል።

ይቀጥላል


@BiniGirmachew    @BiniGirmachew

   መልካም ቀን

ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን  የቴሌግራም ቻናል
8.3K views05:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-26 20:13:43 ሌሊት ላይ የ12ተኛ ተማሪዎች ክፍል ውጤት  እንደሚገለጽ መነገሩ ይታወሳል ። በመሰረቱ  ሌሊት ላይ ወጤት  መለቀቅ አልነበረበትም! 

ምክንያቱም  አብዛኛው  ተማሪ  ለእንቅልፍ ማጣትና እንዲሁም   ራሱን ለማጥፋት(ለመጉዳት)  ሊነሳሳ  ይችላል። 


እናም ቤተሰቦች   ከልጆቻችሁ  ጋር በመሆን  ይሄን ምሽት እንድታሳልፉ እመክራለሁ። 



በዚህ አጋጣሚ መልካም እድል እየተመኘን የመረበሽና የመደናገጥ ስሜት ውስጥ ከገባችሁ ላዛሬ በነፃ የምክር አገልግሎት እንሰጣለን!https:

@Sew_Hun_Bini ላይ ያናግሩን!

የፈጣሪ ሰላም ከሁላችንም ጋር ይሁን

@BiniGirmachew    @BiniGirmachew

   ሼር በማድረግ ለወላጆች ያድረሱ

ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን  የቴሌግራም ቻናል
9.7K viewsedited  17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-26 14:26:53 የቴሌግራም ቻናል 44ሺ  መግባታችን  አስመልከቶ  አንድ ትምህርት  እለቅላቹዋለው። 

በሴቶች ላይ የሚደርስ የአዕምሮ ጭንቀት በደምብ ተከታተሉ።

ሌሎችም ሼር


@BiniGirmachew    @BiniGirmachew

   መልካም ቀን

ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን  የቴሌግራም ቻናል
9.5K viewsedited  11:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-20 08:37:33 ለራስ የሚመልሱት ጥያቄ

በድጋሚ የተለቀቀህ   አዲስ ወደዚህ ቻናል  የገባቸው እባካችሁ እዚህ ቻናል  ላይ የተለቀቀውን ከዚህ በፊት አንብቡ ሼርም አድርጉ ለሌሎች

ወደ ትዳር የሚሄዱ ለራሳቸው የሚመልሱት ጥያቄ

    Bini Girmachew

የወደፊት ባል የምትሆነው ወንድም

   1)ሚስትህን በእውነት ትወዳታለህ?በሚገጥማት  ችግር የራስህን ሕይወት አደጋ ላይ ጥለህም ቢሆን ለመርዳት ፈቃደኛ ነህ?

2)ምርጫዋንና መልካም ስብእናዋን ለማድነቅ ፍቃደኛ ነህ?

3) ከተወሰነ ዓመት  በኋላ ቢያንስ ከ40ዓመት በኋላ ሚስትህ ይህን ዓለም ስለምትንቅ መንፋሳዊ ፍላጎቷን ተከብርላታለህ?

4)ስሜቷ ስስ ስለሆን ብሶቷን ስትነርግህ ያለ ነቀፋ ታዳምጣታለህ?

5) ፈጣሪ የሚያስተምርህን እውነት አስበህ ታስተምራታለህ?

6)ነገ ከፍተኛ ሹመት ላይ ብትደርስ በከፍተኛ ትምህርት ብትመረቅ የእኔ ብለህ ትቀበለዋለህ?

7)በልጆቿ እና በሠራተኞቿ ፊት ላትነቅፋት ቃል ትገባለህ?

8)ምንም ብስጭት ቢገጥምህ ዱላን ላለመሰንዘር ቃል ትገባለህ?

9)ትዳርህ አንድ መንፈሳዊ አማካሪ በጋራ የምታከብሩት አንድ አዋቂ ወዳጅ አንዲኖረው አስበኀል?

10)አካላዊ ንፅሕናን የአፍ ንፅሕናን ያለማቋረጥ መጠበቅ ተዘጋጅተሀል?ይህ ለራስህ ያለህን ክብር ማያሳያ ነው።

11)ሱስንና ደጅ ማምሸትን ለመተው ዛሬ ወስነሀል?ልጅህ ምን አይነት ሰው እንዲሆን ትፈልጋለህ?ጻፈውና አንተ በሙሉነት ኑረው።ያን ጊዜ ልጅህ አንተ ይሆናል።

12)ያለህን ሀብትና ደሞዝህን ለማሳወቅ ፍቃደኛ ነህ?

13)ልጅ ባትወልዱ ከአሥር ልጅ ሚስትህ እንደምትበልጥ ታምናለህ?

14)በልጆቻችሁ ላይ  የጋራ አቋም እንዲኖራችሁ ትመካከራላችሁ?

15)ቤተሰቦቿ ባይወዱህም ለመውደድ ፍቃደኛ ነህ?

16)ወደ ትዳር ስትገቡ ከመንፈሳዊ አገልግሎቷና ወዳጆቿ  ጋር ያላትን ኅብረት ታከብርላታለህ?

17)ሚስትህ እኩያህ እንጂ ተማሪህ አይደለችምና በእያንዳንዱ ነገር ልታርማት ትፈልጋለህ?አንዳንዱን ለማለፍ ዝግጁ ነህ?

18)የጋራ ጸሎታና ማዕድ እንዲኖራችሁ አስበህበታል?

19)ስጦታን መስጠት የሕይውትህ ሥርዓት ልተደርገው ትፈቅዳለህ?


   ፈጣሪ የሌለበት ኅብረት በድን ነውና እባክህ ፈጣሪህን ያዝ።

የወደፊት ሚስት የምትሆኚ እህት

1)ባልሽን በልብሽ ታከብሪዋለሽ?የቤቱ ራስ እንደሆነ ትቀበያለሽ?

2)ለልጆችሽ ባልሽ ክቡር መሆኑን ለመንገር ፍቃደኛ ነሽ?

3)ውበትሽ ፀጥታና ዝግታ መሆኑን አውቀሽ ራስሽን በእውቀትና በማስተዋል እየገነባሽ ነው ወይ?

4)የቤቱ ኃላፊነት በይበልጥ ያንቺ መሆኑን ተረድተሽ የራስሽንና  የቤትሽን ንጽሕና ለመጠበቅ ንቁ ነሽ?

5)የትኛውም ውጥረት ቢኖርብሽ ቤትሽ ቀድመሽ በመግባት ባልሽን መቀበል እንዳለብሽ ታውቂያለሽ?

6)ጣፋጭ ምግብ ሰርተሽ ለባልሽ ለማቅረብ ሙያ አለሽ ወይ? ምግቡን ሠራተኛ ቢሠራው ማቅረቡ ግን ያንቺ መሆን እንዳለበት ትገነዘቢያለች? አብዛኛው ወንድ ልጅ በሠራተኛው እጅ ምግብ ሲቀርብለት የራሱ ቤት አይመስለውም።

7)ከወደፊት ባልሽ ጋር ምንም የስጋ ዝምድና እንደሌላቸው አረጋግጠሻል?ከእህትሽ ወይም ከጓደኛሽ ጋር ጓደኝነት ያልጀመረ መሆኑን አረጋግጠሻል?

8)በትምህርትም በገንዘብም ራስሽን መቻል እንዳለብሽ ትገነዘቢያለሽ?ሁለታችሁ ከተስማማችሁ ችግር የለውም።ግን እንዳትቀሪ አስቢ። ደጁን ከረሳሽ ለባልሽም ማዘን አትችይም።

9)የባልሽ ቤተሰቦች አንዳንዴ ሊጠሉሽ ይችላሉ።አንድ ወንድን  ብዙ ሰው ሲወደው ይህ ይከሰታልና በደስታና በማስተውል ተቀበይው።

10) የልጆችሽ ኃላፊነት ይበልጥ ባንቺ ላይ እንዳለ ተረድተሽ ልጆችሽን በፈሪሃ እግዚአብሔር ለማሳደግ ቁርጥ ውሳኔ አድርጊ።

11)ልጅ መውለድ ያንቺ ችሎታ ሳይሆን የፈጣሪ ስጦታ መሆኑን ተረድተሽ ቢከለክልሽ እንኳ ደስተኛ ነሽ ውይ?ምናልባትም በሽታ ልጅ እንደ ይሁዳም ጌታውን የሚሸጥ እንዲወለድ አስበሻል ወይ?እንኪ ብሎ ቢሰጥሽ እንጂ ያውልሽ ብሎ ሲሰጥሽ ከባድ ነው።

12)የባልሽን ቤተሰቦች እንደ ራስሽ ቤተሰቦች ይቅርታ ታደርጊላቸዋለሽ?ካለሽ ላይስ ታካፊያቸዋለሽ?

13)ባልሽ ከደጅ ሲገባ ምንም ቢከፋሽ በብሩህ ፊት ትቀበይዋለሽ ወይ?ያንቺ ብሩህ ፊት ከሌለ ቤቱን ይጠላል።

14)የባልሽን እንግዶች በደስታ ታስተናግጃለሽ? ወንድ ልጅ በቤቱ እንግዶችን መጋበዝ ይፈልጋል።አንቺ ደስተኛ ካልሆንሽ ግን ሆቴል ይጋብዛል።

15)ወደ ትዳር ብትገቢ ብትወልጂም አንደ ድሮ ራስሽን ለመጠበቅ ጎበዝ ሴት ነሽ?

16)እስከ ጋብቻ ድረስ ክብርሽን ጠብቀሽ ለመቆየት ወስነሻል።ቆራጥ ሴትን አንበሳም እንደማይደፍራት ተገንዝበሻል?

17 )ዘመናዊነት ሴት ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱሳዊት ሚስጥ ለመሆን ፈቃደኛ ነሽ?

18)በቅንዓት እየፈጠርሽ ባልሽን መጠራጠር ባልሽን ስርቆት ማስተማር መሆኑን ተገንዝበሻል? ቤትን የሚሠራ ፈጣሪ ነውና በጸሎት ትጊ! ፈጣሪ ያማረውን ቤት ይስራልሽ!!!














@Bini_Girmachewbot @BiniGirmachew
604 views05:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-19 07:15:42
•••ያን ጊዜም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከገሊላ ናዝሬት መጣ፤ ዮሐንስም በዮርዳኖስ ወንዝ አጠመቀ።ማር 1÷9-10

#እንኳን_ለብርሃነ_ጥምቀቱ_በሠላም_አደረሳችሁ !
1.6K views04:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-19 00:52:46
የዛሬ 5 ዓመት የተፃፈው ነበር ወይ ጊዜ

2 በእድሜ ገፋ ያሉ ባለትዳሮች ናቸው

በጣም ድብር ሲላቸው ባልየው እንዲህ አላት

"የወጣትነታችንን ጊዜ የጋብቻችንን ጊዜ ወደ ኃላ ብንመልሰው ምን ይመስልሻል"
.

ሚስት:- በጣም ደስ ብሏት እሺ አለቺው!

ባል ፦ እኔ ታች ሱቁ ጋር ልውረድና ቁጭ ባልኩበት አንቺ ትመጪና በድንገት እንገናኛለን አላት

እሺ ተባባሉና ሄደ ወረደ ታች ሊጠብቃት ቢጠብቃት ቢጠብቃት አትመጣም 4 ሰአት ሙሉ ጠበቃት

አሁንም ወፍ የለም የሆነ ነገር አጋጠማት እንዴ ብሎ በፍርሃት ቶሎ ወደ ቤት ተመለሰ ሊያያት
እሷ ቁጭ ብላ ስቅስቅ እያለች ታለቅሳለች
ባል ደንግጦ ምን ሆንሽ ውዴ??

አላት
.
ሚስት:- እናቴ ከቤት መውጣት ከልክላኝ ነው ብላ እርፍ


@BiniGirmachew    @BiniGirmachew
315 viewsedited  21:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-18 07:46:52
በህይወቴ ከተማርኩት ነገር ውስጥ አንደኛው ለሰዎች መልካም ነገር ብታደርግ ለመልካምነትህ ከሰዎች ዘንድ ምላሽ መጠበቅ ሊጎዳ እንደሚችል ነው። አንዳንዱ መልካም ስታደርግ ሞኝ እንደሆንክ ሊቆጥርህ ይችላል። አንዳንዱ ደግሞ ከእሱ የሆነ ነገር ፈልገህ የምታደርግለት ይመስለዋል። ሌላኛው ደግሞ ከምስጋና ይልቅ ጠላትህ ሆኖ ያርፍዋል።

እናም እልሀለሁ ለመልካምነትህ ከሰዎች ምላሽን አትጠብቅ! ባገኘኸው አጋጣሚ ሁሉ ምላሹ ምንም ይሁን ምን መልካምነት አብሮህ ይሁን!
ፈጣሪ ይከፍልሀልና!!!
"መልካምነት ለራስ ነው"

መልካም ቀን

@BiniGirmachew    @BiniGirmachew

የዛሬ 6 ዓመት የተፃፈ ነበር
2.3K viewsedited  04:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-17 07:53:06
2.7K views04:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-16 19:38:51 #እያሰብን #እያስተዋልን

    ክፉ ባሎች ደግ ሚስት ያገኛሉ በሚል ስሌት ትዳርህን የጭካኔ ቦታ አታድርገው ።




------

አሳብ ይዘህ እንጂ ውሳኔን ይዘህ  አታማክር ። ያለ መስፈርት ውደድ እንጂ ወደ ኑሮ ከገባህ በኋላ አትኩረህ አትመልከት ።

የሚያጣራ ዓይን ፣ የሚያበጥር ጆሮ ለትዳር ተገቢ አይደለም ።

ቤትን የሚጠብቅ እምነት ነው ።

ደግሞ አንተ አትክዳ እንጂ በሌሎች መከዳት ካሣው ከፈጣሪ ነው ።  

#እናስታውስ ከልብ

ሰዎች አንተ ፈጣሪን  የበደልከውን ያህል አልበደሉህምና ይቅር በላቸው ።

#በመታገሥ ቤትህን ታተርፋለህ።


@BiniGirmachew    @BiniGirmachew
2.1K views16:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-16 14:16:01 ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን pinned «ስለ ዝምተኛ ሰዎች እውነታውን ልንገራችሁ Bini Girmachew 1. ዝምተኛ ሰዎች በልባቸው ውስጥ ብዙ ያወራሉ  ፤ አንዳንድ ጊዜም ብቻቸውን ያወራሉ። 2. አንድ ጊዜ ከአናንተ ጋር ምቾት ከተሰማቸው። እብድ እና ልዩ ነው የሚሆኑት። 3. የሚናገሩት በሀሳባቸው እና በልባቸው ነው። 4. አይናፋሮች ናቸው ፤ የአይን ለአይን ግንኙነት ብዙ ጊዜ መጠበቅ አይችሉም። 5. በጣም ብዙ ንዴት አለባቸው…»
11:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ