2023-01-28 13:20:46
በሴቶች ላይ የሚደርስ የአዕምሮ ጭንቀት ክፍል 5
የብቸኝነት ሕይወት
ከላይ ታሪኳን ያነበብነው አሰለፈች ትልቁ ችግሯ ብቸኝነት ነው። ይሁን እንጂ ይህን ዓይነት ችግር ያለባት እርሷ ብቻ አይደለችም።
አሜሪካ ውስጥ ዕድሜያቸው ከ14 ዓመት በላይ የሆኑ በ1980 (እ.ኤ.አ) የተደረገው ጥናት እንደሚያመለክተው አሥራ አንድ ሚሊዮን ሴቶች ብቻቸውን ይኖራሉ።
ከነዚህ ውስጥ ስምንት ሚሊዮን ሴቶች የልጆች እናት ሲሆኑ፣ ልጆቻቸውን የሚያሳድጉት ለብቻቸው ሆነው ነው።
ብዙ ሴቶች ብዙ ጊዜ ያገቡና ቤተሰብ የመሠረቱ እንኳን ቢሆኑም ብቸኝነት ይሰማቸዋል።
እርግጥ ነው ካገቡት ይልቅ ያላገቡት ይበልጥ በብቸኝነት ስሜት ይሰቃያሉ።
አልፎ አልፎ ማንኛውም ሰው ቢሆን ብቻ መሆን የሚያስፈልገው ጊዜ አለ።
ኢየሱስም ቢሆን ብቻውን የሚሆንበት ጊዜ ነበረው (ማቲ. 26፥36)። ይሁን እንጂ የሚደግፉንና የሚረዱን ሰዎች ያስፈልጉናል።
የልባችንን ሳንደብቅ የምንገልጽላቸው ለእኛ ቅርብ የሆኑ ወዳጆች ካሉን ተስፋ እንዳንቆርጥና በአዕምሮ ጭንቀት እንዳንያዝ ይጠብቁናል።
ብዙ ጊዜ ዓይን አፈር የሆኑና ብቸኛ ሴቶች ለአዕምሮ ጭንቀት በጣም የተጋለጡ ናቸው።
"ተፈላጊ አይደለሁም" የሚል ስሜት
ሴትን ወደ አዕምሮ ጭንቀት ሕይወት ከሚመሯት ምክንያቶች መካከል አንደኛው "ቆንጆ አይደለሁም፤ የሚፈልገኝ ወንድ የለም" የሚል ስሜት ነው።
በተለይ ለጋብቻ የሚጠይቃቸው ወንድ ያላጋጠማቸው እንደሆነ ፣ አንዳንድ ሴቶች ትልቅ የስሜት መጎዳት ይደርስባቸዋል።
ዕድሜያቸው በጨመረ ቁጥር የማግባት ተስፋቸው እየቀነሰ የሚመጣ መስሎ ስለሚሰማቸው ስጋታቸውና ፍርሃታቸውም በዚያው መጠን እየጨመረ ይሄዳል።
ጓደኞቻቸው በአገቡ ቁጥር ፤ ስሜታቸው እየተጎዳ የሚታመሙ ወጣት ሴቶች ቁጥር ትንሽ አይደለም።
ሌላው ቀርቶ ያገቡት እንኳን በተለያየ ምክንያት ባሎቻቸው የሩካቤ ሥጋ ግንኙነት ባይፈጽሙ ፣ "በአቋሜ ደስ ባልለው ነው፤ ጠልቶኝ ነው" በማለት ስለራሳቸው ቅሬታ የሚሰማቸውና የሚያዝኑ አሉ።
በዚህ ዓይነት ስሜታቸው የሚጎዳ ሴቶች ቀስ በቀስ በአዕምሮ ጭንቀት ይያዛሉ።
"አልተፈለግሁም፤ አልተወደድኩም" በሚል ስጋት ብቻ ሳይሆን የሩካቤ ሥጋ ፍላጎታቸውን የሚወጡበት ሁኔታና መንገድ ሲጠፋም ይበሳጫሉ፤ ሲቆይም ወደ አዕምሮ ጭንቀት ውስጥ ይከታቸዋል።
ባሎች ከሚስቶቻቸው የሚገባቸውን የሥጋ ፍላጎት መፈጸም ሀላፊነት እንዳለባቸው መርሳት የለባቸውም።
ይሁን እንጂ ፣ የሩካቤ ሥጋ ግንኙነት እውነተኛውን ፍቅር መግለጫ እንጂ እንደ ሥራ ወይንም እንደ ሀላፊነት መታየት የለበትም።
ባሎች በዚህ ዓይነት መልክ ከወሰዱትና እንዲሁም ሚስቶች በዚህ ዓይነት መልክ ከተረዱት ፣ ለሩካቤ ሥጋ ግንኙነት ያላቸው ፍላጎት ይጠፋል።
በተለይ በኢትዮጵያውያን ላይ የባህል ተጽዕኖ ስላለ ሴቶች በዚህ አቅጣጫ ስሜታቸውን ለመግለጽ ያቅታቸዋል።
ይሁን እንጂ ደስተኞች አለመሆናቸውን የሚገልጹበት የራሳቸው መንገድ አላቸው።
በቀላሉ ይበሳጫሉ ፣ ይነጫነጫሉ ፣ ውሃ ቀጠነ ይላሉ ፣ ያለ ምክንያት ያኮርፋሉ።
በሩካቤ ሥጋ ግንኙነት አለመፈለግ መናቅ፣ አለመወደድ የደረሰባቸው ስለሚመስላቸው ስሜታቸው ይጎዳል።
የስሜታቸው መጎዳትም የአዕምሮ ጭንቀት ያስከትልባቸው። ስለዚህ ባሎች በዚህ አቅጣጫ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል።
የብዙዎች ባሎች ችግር ፣ ሚስታቸው አንዴ ወይንም ሁለቴ በተለያየ ምክንያት የሩካቤ ሥጋ ግንኙነት በዚያን ቀን "እንቢ" ካለች፣ "ሁልጊዜ እምቢ ትላለች፤" ወይንም "ዛሬ ጠይቄ እንቢ ብትለኝ ስሜቴ ይጎዳል" በማለት ከሚስታቸው ገፍቶ ካልመጣ በስተቀር ሚስቶቻቸውን የማይቀርቡ ወንዶች አሉ።
በባልና ሚስት መካከል እውነተኛነትና መተማመን ያስፈልጋል። "አሞኛል" ስትል ለማምለጥ ሳይሆን እውነቷን መሆኑን ማመን አለበት ፤ ሴትም ሳያማት "አሞኛል" የሚል ምክንያት መስጠት የለባትም። እዚህ ላይ በሁለቱም በኩል በግልጽነት ሊወያዩበት ያስፈልጋል።
የልጆች መወለድ
አብዛኛውን ጊዜ ልጆች ከአባታቸው ይልቅ ወደ እናታቸው መቅረብ ይቀላቸዋል። በዚህ ምክንያት እናቶች ቤታቸውን ለመያዝ ፣ ከልጆቻቸው ጋር ትክክለኛ ግንኙነት ለመፍጠር ፣ በሚያደርጉት ጥረት አንዳንድ ሁኔታዎች ስለሚፈጠሩ ብስጭትና የአዕምሮ ጭንቀት ይደርስባቸዋል። ሕፃናት ለእናታቸው የአዕምሮ ጭንቀት ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ።
ይህም የሚሆነው ፣ ፍላጎታቸውን ለማሟላት ፣ የሚጠይቁትን ሁሉ ለማድረግና ለመስጠት እናት የሆነችዋን ሴት ከፍተኛ ጊዜና ጉልበት ስለሚጠይቃት ነው።
ልጆች ከፍ ሲሉ ደግሞ የቤት ዕቃን ለመበጥበጥና ለማተረማመስ ሀይልና ጉልበት ሲኖራቸው ፣ መስመርና ስርዓት ለማስያዝ አሁንም እናትየው ብዙ ትደክማለች።
ልጆቿን እንደምትፈልጋቸው ሆነው ካልተገኙ "ጥሩ እናት ባልሆን ይሆናል ....በደንብ ባልይዛቸው ነው" በማለት እራሷን መውቀስ ትጀምራለች።
ልጆችን በደንብና በሥርዓት ማሳደግ ቀላል አይደለም። አንዳንድ ወልደው ያላዩ ሰዎች በእንግድነት ሰው ቤት ሲሄዱ፣ ልጆቻቸውን በማየት ወላጆችን ሲነቅፉና ሲታዘቡ ይታያሉ። አንዳንድ ወላጆችም ስለ ነርሱና
ስለልጆቻቸው ልዩ የሆነ አስተያየት እንዳይሰጥባቸው ከሚገባ በላይ ይጠነቀቃሉ። እናቶች ልጆቻቸው ተጫውተው ማደግ እንዳለባቸው በመዘንጋት ከሚገባ በላይ ሲጫኑአቸውና ነጻነት ሲከለክሉአቸው ይታያሉ።
ይህን ዓይነት ቁጥጥር ለማድረግ ደግሞ የእናትየዋን ጊዜና ጉልበት በሀይል ይጠይቃል። ይሄም በሥጋዋና በሥነ አዕምሮዋ ላይ ከፍተኛ ድካም ስለሚያስከትል ፣ ሲቆይ የአዕምሮ ጭንቀትን ይፈጥርባታል።
በሰውነት ውስጥ ስለሚፈጠሩ ለውጦች
#ይቀጥላል
@BiniGirmachew @BiniGirmachew
ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን የቴሌግራም ቻናልሼር በማድረግ ሌሎችም እናድረስ
6.6K viewsedited 10:20