2022-12-31 08:08:31
«Recycle Bin»
በማስተዋል አንብብ
ተጻፈ፣ በስነ-ልቦና ባለሙያ
. . . Bini Girmachewበኮምፒዩተር ትምህርት ቋንቋ መሠረት «Recycle Bin» ትርጉሙ ከፍተኛ ነው።
___
አንድን ነገር እንሠራለን ከሠራንም በኋላ ቦታ እንዳይዝብን በማሰብ እናጠፋዋለን «Delete» እናደርገዋለን።
___
«Delete» ማድረግ በራሱ ችግር አይደለም ምክንያቱም አንደኛ ቦታ ስለሚይዝብን ኹለተኛም ካጠፋነው የተሻለ ለመሥራት በማሰብ ነውና።
___
በዚያ
ውስ ላይ የጠፉ ፋይሎች የሚታገቱበት «Recycle Bin» የተባለ የጠፉት መገኛ እያለ ምን ችግር ሊመጣብን ነው።
___
ችግር የሚኾ
ነው «Undo» ብለን ወይም «Restore» አድርገን መመለስ በማንችልበት መልኩ ፋይሎችን ካጠፋናቸው ነው።
___
ለዚኽም እኮ ነው
የ «IT» ተማሪዎች «Undo» ባትኖር ኖሮ እኮ አንመረቅም ነበር ይላሉ የሚባለው።
___
በስህተት እናጠፋለን በ
ስህተት ያጠፋነውንም ነገር በ«Undo» እና በ«Restore» እንመልሳቸዋለን።
___
ነገር ግን በ«Undo» እና በ
«Restore» እንዳይመለስ አድርገን «Permanently Delete» ካደረግነው በራሳችን ስናዝን ከመኖር ውጭ የጠፉትን ኹሉ መመለስ አንችልም።
___
አውቀንም ኾነ በስህተት «CTRL+DE
L»ን ከተጫንነው ፋይላችንን «Recycle Bin» ከተባለው የጠፉት መሰባሰቢያ ካምፕ ላይ አናገኘውም።
___
በዚኽም የተነሣ ለአንድ ቀንም ቢኾን እንኳ
ያ ያጠፋነው ፋይል አስፈላጊ ኾኖ ብናገኘው ጸጉራችንን ከመንጨት ከንፈራችንን
___
ከመምጠጥ ውጭ ነበረን እኮ ከማለት ውጭ «Undo
» እና «Restore» እንኳ ተባብረው ሊመልሱት አይችሉም።
___
አሁን ስለ ኮምፒዩተር እያስተማርኩ እንዳይመስላችሁ ስለራሳችን ስለሥራችን ስለተግባራችን እንጅ። _አንድ ሰው ወንጀል ሊሠራም ላይሠራም ይችላል፣ በኾነ ምክንያት ብቻ
«Permanently Delete» እንዲደረግ ይፈረድበታል።
_ማን እንደሚፈርድበት እንኳ አይታወቅም ብቻ የኾነ አካል «Permanentl
y Delete» አድርጎት ዳግም ላናገኘው እንሰናበተዋለን። በዚህ መልኩ በርካታ ለሀገር ለወገን የሚጠቅሙ በርካታ ሰዎችን አጥተናል።
_እነ በላይ ዘለቀ፣ እነመንግሥቱ እና ግርማሜ ንዋይ፣ እነ አቡነ ጴጥሮስ፣ እነ አ
ቡነ ሚካኤል፣ እነ አቡነ ቴዎፍሎስ፣ እነቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ፣ እነበዓሉ ግርማ፣ እነ ኢንጅነር ቅጣው እጅጉ፣ እነ ሳሙኤል አወቀ ወዘተ ወዘተ።
_ በነገራችን ላይ ዘርዝሬ መጨረስ እንደማልችል አውቃለሁ ግን የተወሰኑትን በየዘመናቱ «
Permanently Delete» የተደረጉ ሰዎችን ነው የጠቀስሁላችሁ።
_ እነዚህ ሰዎች በማን «Permanently Delete» እንደተደረጉ እንዴት እንዲጠፉ እንደተ
ደረጉ የሚታወቅ ነገር የለም።
_በርግጥ በስቅላት እና በጥይት ተደብድበው በሰው ፊት በአደባባይ «Permanently Delete» የ
ተደረጉትን ማን እንዳጠፋቸው እናውቃለን። ታሪክም መዝግቧቸው ስለሚገኝ በዚያ እናውቃለን።
_አብዛኞቹ ግን በማን እንዴት እንደጠፉ በራሱ አይታወቅም።
እኛ ሰዎች ነን። ዘመናችን ከዚህ እስከ እዚህ
ተብሎ የተገደበ፣ ቋሚ ኾኖ ለዘለዓለም የሚኖር ዘላለማዊ ሰው እንደሌለም እናውቃለን።
_ታዲያ አንዱ አንዱን ያጠፋው ዘንድ ምን ዓይነት ሰይጣን ነው የመከረው? ይችን አጭር ዘመን መታገስ እንዴት ያቅተ
ናል? አንተ አጠፋኸውም አላጠፋኸውም አንተም እርሱም በኾነ ዘመን ላይ ሳትወዱ በግድ መጥፋታችሁ አይቀርም እኮ።
_ ታዲያ የኾነ ጊዜ ላይ ያ ያጠፋነው ሰው ለሰው ለወገን ቢያስፈልግ «Undo» እና «Restore» አድርገን ልንመልሰው
እንዴት እንችላለን?
___
ሰዎች ነንና እናጠፋለን፣ እንሳሳታለን፣ ሕግ ልንጥስ ሥርዓት ልናፈርስ እንችላለን።
___
ነገር ግን ይህ ጥፋት ኾኖ ቢገ
ኝ እንኳ ማሰር እንጅ መግደል መፍትሔ ይኾናል ብየ አላስብም።
___
የታሰሩ ሰዎች «Recycl
e Bin» ውስጥ እንደሚገኙ የጠፉ ፍይሎች ይቆጠራሉ።
___
እነዚኽ በእስር ቤት የሚገኙ ሰዎች ለሀገር ለ
ወገን አስፈላጊ ኾነው ቢገኙ ባስፈለጉ ሰዓት ከእስር «Undo» እና «Restore» በማድረግ
ፈትቶ ማሠራት ይቻላል።
___
እነ በላይ ዘለቀ፣ እነመንግሥቱ እና ግርማሜ ንዋይ፣ እነ አቡነ ጴጥሮስ፣ እነ አቡነ ሚካኤል፣ እነ አቡነ ቴዎፍሎስ፣ እነቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ፣
እነበዓሉ ግርማ፣ እነ ኢንጅነር ቅጣው እጅጉ፣ እነ ሳሙኤል አወቀ ወዘተ ወዘተ
___
በተባለ እስር ቤት ቢኾኑ ኖሮ ዛሬ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ የሀገሪቱ መንግሥት በወሰነበት ጊዜ በቀላሉ ከእስር ፈትቶ ለሀገር ለወገን በጠቀሙ ነበር።
___
ነገር ግን ዳግም «Undo» እና «Restore» አድርገን እንዳናገኛቸው ኾነው «Permanently Delete» ተደርገዋልና ከንፈር ከመምጠጥ ጸጉር ከመንጨት ያለፈ ነገር ልናደርግ አንችልም።
___
ዛሬ አያስፈልገንም ብለን ያጠፋነው ፋይል ነገ እንደሚያስፈልገን ስለምናውቅ «Recycle Bin» ውስጥ እንደምናጠራቅመው ኹሉ ዛሬ
___
አጥፍተዋል ወንጀለኞች ናቸው የምንላቸውን ሰዎችም ነገ አስፈላጊ ስለሚኾኑ እስር ቤት ውስጥ ብናጠራቅማቸው ይሻላል።
___
ከእስር ቤት ውጡ በሚል ቃል ብቻ ማስወጣት ይቻላልና «Permanently Delete» የተደረጉ ፋይሎችን ዳግም
___
መመለስ እንደማንችል ኹሉ ማን እንደኾነ እንዴት እንደኾነ ሳይታወቅ ሰውንም በሞት ማስወገድ ለነገ ቁጭትን የሚፈጥር ስለኾነ እንደ ሰው አስበን ብንኖር መልካም ነው።
@BiniGirmachew
@BiniGirmachew
@BiniGirmachew
#ሼር
4.3K viewsedited 05:08