Get Mystery Box with random crypto!

በማለዳ ንቁ !

የቴሌግራም ቻናል አርማ bemaleda_neku — በማለዳ ንቁ !
የቴሌግራም ቻናል አርማ bemaleda_neku — በማለዳ ንቁ !
የሰርጥ አድራሻ: @bemaleda_neku
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.24K
የሰርጥ መግለጫ

(2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕ. 13)
----------
11፤ በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ደኅና ሁኑ። ፍጹማን ሁኑ፥ ምክሬን ስሙ፥ በአንድ ልብ ሁኑ፥ በሰላም ኑሩ፥ የፍቅርና የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል።
14፤ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን፡፡
@bemaledaa_neku_bot

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-07-27 10:30:55 ማራናታ !

የሚጠብቁት ናቸው የሚያገኙት፤ የሚፈልጉት ናቸው የሚሰሙት፡፡ ዓለም ሳያየው ምሰክሮቹ ያዩት ከመጀመሪያው ጀምሮ ስለነበሩ ነው፡፡ ዘይት ይዘው የተዘጋጁት እንጂ ተኝተው የቆዩት ከሠርጉ አልታደሙም፡፡ እርሱ ሲል ቀጥሮናል፦

      "እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ። አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።"

                                                                     (ራእ. 22፥13)

.. የታወቀ ነው፤ ሥጋና ደካማ ነውና ፈርተናል፡፡ ስለዚህ በሮቻችንን ዘግተናል፡፡ ሁሉንም በጥርጣሬ እናያለን፡፡ በሰው ያለው ይታወቃልና ሰውን ማመን ከብዶአል፡፡ ሲሆን የምናየው፥ ቀጥሮን ያላየነውን እንድንረሳ እየታገለን ነው፡፡ በነፍሳችን ሰይፍ እያለፈ ያደረጀነውን እንድናፈረስ ዕለቶች ሁሉ ይተናነቁናል.. ፡፡

ሆኖም..
     ሆኖም የተጻፈውን ሁሉ ሥጋ እያለበሰ ስላስነበበን ተስፋችን እርግጠኛ ነው፡፡ ነገ ነገ የመሆኑን ያህል የታመነ ነው፡፡ እንዴት እንደኖርን እናውቃለን፡፡ ሥጋቶች ከበውን ብንከዳውም ስማችንን እንደቀደመው እየጠራ በፍቅሩ ያለች ምሕረቱን ደጋግሞ አሳይቶናል፡፡ የነበረውን ሁሉ እየገለጠ ሲተርክልን ልባችን እንዴት እንደተቃጠለ እናስታውሳለን፡፡ ስለእርሱ እንደሚታረዱ በጎች የተቆጠርንባቸውን እነዚያን ቀናት እንዴት እንረሳቸዋለን? ..ለማንኛውም "ዓመፀኛው ወደ ፊት ያምፅ፥ ርኵሱም ወደ ፊት ይርከስ፥ ጻድቁም ወደ ፊት ጽድቅ ያድርግ"፡፡ ፈቃድ ሁሉ የድርሻውን ይወጣ፡፡ እርሱ ግን ወደተዘጉት ደጆች እየመጣ ነውና የተከፈቱ አደባባዮች ታውከዋል፡፡ (አሞ. 5፥17) እንደሚመጣ የሚሰማም ና ይበል። አሜን፥ ሐዋዝ ኖላዊ ሆይ፥ ሳቃችን አንተ ነህና በቶሎ ና! ማራናታ!

@bemaleda_neku
11.0K views07:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 18:44:32
12.2K views15:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 13:46:58 ጨለማን ከመክሰስ አንድ ሻማ መለኮስ

ስለ እውነት ሲወሳ: እውነትን የማወቅ ሂደት ሦስት ደረጃዎች እንዳሉት ይታመናል:: አንደኛ፥ የእውነት ዳር ዳሩ ሲገባን ሳናውቅ በመክረማችን እንገረማለን:: ለጥቆ ግማሽ ድረስ ሲገባን ሐሰትን የምንታዘብ: ሲልም የምንተች እንሆናለን:: በመጨረሻ የእውነት ጥጉ ሲረዳን እውነት ላልገባቸው ሐሰቶች እናዝናለን: የሚያደርጉትን ስላለማወቃቸው እንማልዳለን:: (ሉቃ. ፳፫፥፴፬) እኛ እስከ የቱ መጥተናል?

አብዛኞቻችን ባለነቀፌታዎች ነን (እርከን ሁለት!):: የመሰሉንን ሆነ የሆኑን ስሕተቶች ለማንኳሰስ እንፈጥናለን:: በተቃራኒው የምንችለውን ስሕተት በምንችለው ለማረም እንዘገያለን (ዘግይተንም ብናርም ሸጋ ነበር):: ምክንያት?

ምክንያቱም መተቸት ቀላል ነው:: የገለባ ያህል አይመዝንም፡፡ ማብጠልጠል፣ መንቀፍ፣ ማዋረድ፣ ማማት፣ ችግር ማውራት እንደ እፉዬ ገላ ቀሊል ነው:: ስሕተት ላይ ለመጮህ ስሕተት ማየት ይበቃል:: ከበድ የሚለው የተወረወረውን መደልደል፣ የተዛነፈውን ማቅናት፣ የተበላሸውን ማሳመር ነው:: በክብደት ማዕረግ ለማጌጥ ደግሞ ልብ ይፈልጋል:: ከየዋህነት የተዋሐደ ልባምነት! (ማቴ. ፲፥፲፮)

ዲያቢሎስ ዓለምን በጨለማ ሥርዓት አጽልሞ የብርሃን ጮራን ለማፈን የጠቀመው: የእውነትን መንገድ ከቻለ በሙሉ ካልቻለ በግማሽ መዝጋቱ ነው:: ኋላም ባልተሞላ ክፍተት የርሱን ሐሰት አስገብቶ: በተገመሰ እውነት ውሸትን ከመንቀፍ ውጪ እንዳናስተምራት ያጠበናል (ስንት የሚማሩ ሐሰቶች ተማረው ጠፉ ይሁን?)::

ዘመናችን: ከተሠሩ ክፋቶች ይልቅ ስለ ተሠሩ ክፋቶች በተነዙ ድምፆች ሳይጎዳ አይቀርም:: ሐሰት አቅመ ቢስ ናት:: ለመቀጣጠል ማገዶ ትፈጃለች:: በአንጻሩ እውነት በደማቁ ለመንደድ አንድ እንጨት በቂዋ ነበር:: ሆኖም አፋችን: መልካምነት ዓይንን የሚያቃጥሉ ጢስ ክፋቶች ብዙ እንዲጨሱ ነፋስ ወሬን የማርገብገብ ሚናውን ጥሩ ተጫውቶ: አየር ጊዜያችንን በሽብር ሽታ አውዶታል::

"የሰው ጆሮ" ያለህ ሆይ ስማማ! በስብዕና ከተማ ከተነቀፉ ክፋቶች የተከወኑ ደግነቶች ሚዛን ይደፋሉ፤ ከተሰደቡ ጥፋቶች የተፈጸሙ ልማቶች ይጠቅማሉ:: እንኪያስ ካደረጉት ክፋት የምናደረገው በጎነት ይበልጣልና እጃችንን ከመጠቆም የተሻለን መደገፍ እናሰልጥነው:: ሌላው ቢቀር ግፍ በዛ ከምንል የየራስ ግፋችንን እስቲ እንቀንስ:: የኔ ትንሽ ሥራ ምን ይለውጣል አንበል:: የሻማ አንዳንዶች የዓለምን ጥቁረት እንደሚያበሩ እንወቅ (ለዚህም ምስክሬ ሐዋሪያት ናቸው)፤ ያወቅነውንም በማመን አንድ መስኮት እንክፈት፤ ያኔ.. የ40 ዓመቱ ቀጠሮ በ40ኛ ቀኑ ይደርሳል፤ የከነዓን ረጅም ጉዞ በአጭር መንገድ ያልቃል::

@bemaleda_neku
3.4K views10:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 23:45:59 3ኛ. ጋኔን (ሲበዛ አጋንንት)፦ ዕሩቅ ውዱቅ (የተራቆተ የወደቀ) ማለት እንደሆነ የተለያዩ መንፈሳዊ መጽሐፍት አስቀምጠዋል:: በዚህ ትርጓሜ መሠረት እንዲሁ ሁሉም ርኩሳን መናፍስት የተጣሉ እንደመሆናቸው አጋንንት ቢባሉ የተሳሳተ አይሆንም:: ሆኖም አጋንንት የሚለው ስያሜ በአመዛኙ ተቀባይነት ያገኘው በማቴዎስ ወንጌል (ምዕ 12) ላይ የተቀመጡት "በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል" እና "[ርኩስ መንፈስ] ከእርሱ የከፉትን ሌሎች ሰባት አጋንንት ከእርሱ ጋይ ይወስዳል" የሚሉትን አገላለጾች መሠረት በማድረግ: አጋንንት የሚባሉት የዲያቢሎስን ውሸት ተቀብለው ሠራዊቱ (ጭፍራዎች) ሊሆኑ የፈቀዱት መናፍስት ናቸው የሚለው ሐቲት ነው:: ስንጠቀልለው አንድም አጋንንት ማለት የተገፈፉ፣ የተጣሉ ማለት ከሆነ ሁሉንም ርኩሳን መናፍስት የሚመለከት ጥሪ ሲሆን: አንድም የወንጌላቱንና የአባቶችን አስተያየት ብንከተል አጋጋንት የሚሰኙት የሰይጣን ሠራዊቶች አሊያ ተገዢ አገልጋዮች ናቸው ልንል እንችላለን::

ከዚህ የምንረዳው መናፍስት አበዛዛቸውን እንዲሁም የጥፋት ስልታቸውን በመከተል ለያይቶ መጥራት አስቸጋሪ እንደሆነ ነው:: ስያሜዎቻቸው በአጠቃላይ ወደ አንድ ክፉና ዓመፀኛ ወደሆኑ የመናፍስት ነገድ የሚያመሩ እንጂ መደብ መደባቸውን ለያይቶ የሚያስቀምጡ ሲሆኑ አይገኝም:: ቀድሞውኑ መናፍስቱ ከሰው ልጅ አንጻርና እንደ ሰው ልጅ ጠላትነታቸው ለሰው ልጅ ቋንቋ የተገለጠና ራሱም የሰው ልጅ በተለያየ ምክንያት የሚያወጣላቸው ዓይነተ ብዙ ስያሜ እንጂ የየራሳቸው መጠሪያ እንዳላቸው የሚናገሩ መጽሐፍት የሉም (በግሌ አላገኘሁም፤ ጥቆማ ካለ በማመስገን እቀበላለሁ፤ በእርግጥ መጽሐፈ ሄኖክ ዝርዝር የጠቀሳቸው: የአጋንንት ስሞች ናቸው ያላቸው አሉ:: ሆኖም ከነዚሁ ስሞች አንዳንዶቹ በጠቅላላው ኔፍሊም ከሚሰኙ: ውላቸው ሳይለይለት እስከዛሬ የውዝግብ ርእስ ከሆኑ: በዘፍጥረት ምዕ. 6 ከተጠቀሱት ጋር ሲያያዙ እናነባለን:: ይህን የመሰለው ምክንያት እንደሚጠቁመው: ተጨማሪ ጥልቅ መንፈሳዊ ጥናትን መጽሐፉ መፈለጉን ነውና በደፈናው ማጣቀሻ አድርገን ለማምጣት ለጊዜው የተመቸ አይደለም::) አሁን: ሦስቱን የመናፍስት ወደ ሰው ሕይወት መግቢያ መንገዳቸውን መሠረት ያደረገ ስያሜአቸውን እንዳስስ::

ብዙ ሰዎች: የዛር፣ የመተትና የቡዳ መንፈስ ሲባል እገሌ እገሌ ተብሎ እንደተሰየመ ነጠላ ስም አድርገው ይወስዳሉ:: ግን  አይደለም:: ይልቅስ ዛር፣ መተት/ድግምት፣ ቡዳ የመናፍስቱ የመግቢያ መንገዶች የተለያዩበት (የታወቁበት) ስያሜዎች ናቸው:: ዛር ሲባል በዘር ውስጥ ቁራኛ ሆኖ የሚመጣ ርኩስ መንፈስን ያመለክታል፤ መተት/ድግምት ሲሆን ልዩ ዓላማ በመያዝ ተልኮ የመጣ መሆኑን ያመለክታል፤ ቡዳ ደግሞ ተሻጋግሮ የመጣ መንፈስን ይመለከታል:: ሦስተኛው: ቡዳ ሲባል: በቀደመው ማኅበረሰብ የሚታወቀው፣ ከሰው ዓይን ላይ አንድ መልካም ነገር አይቶ ተነሥቶ የሚመጣው መንፈስ ብቻ የሚመስላቸው ብዙዎች ናቸው:: ነገር ግን እንዳለንበትም: ዘመኑን እንደዋጀው የመናፍስት የጥፋት ሥርዓት ከሆነ የምናስተውለው: የቡዳ መንፈስ ብዙ ዓይነት ጊዜውን የተከተለ ማንነት እንደያዘ ልንረዳ ያስፈልጋል:: ለምሳሌ ትውልዱ ውስጥ ተንሰራፍተው የገቡት የዝሙት መናፍስት  በዝሙት ፊልሞች፣ ምስሎች፣ ንባቦች አማካኝነት ቡዳ ሆነው ወደ ሰውነት ይገባሉ:: በዚህ ጊዜ የዝሙት ቡዳ የሚል: ግብሩንና የገባበትን መንገድ የሚጠቁምን ስያሜ መንፈሱ መለያው አድርጎ ይይዛል::

መናፍስት እንደ ስምሪታቸው፣ ጥፋትን የመግለጪያ አካሄዳቸውና ዘዴያቸው፣ እንደ ግብራቸው፣ እንደ ዝንባሌያቸውና ሰው ራሱ አከባቢን፥ ልማድን፥ ባሕልንና ዕውቀትን ባማከለ አሰያየም እንደሚጠራቸው: የተለያዩ ስያሜዎችን ያገኛሉ:: ለምሳሌ ሁሉንም በአንድ አንድ ምሳሌ ብንመለከት: እንደ ስምሪታቸው የዓይነጥላ መንፈስ፣ እንደ ጥፋትን (ከተነቃባቸው በኋላ ውጊያንም ቢሉ) የመግለጪያ አካሄዳቸውና ዘዴያቸው የሰላቢ መንፈስ፣ እንደ ግብራቸው (ከፊተኛው ጋር ይሳመካል) የሰዶም መንፈስ፣ እንደ ዝንባሌያቸው (ከጥፋት አካሄድና ስምሪት ጋር ይይዛል) የሔርሜት መንፈስ፣ ሰው ራሱ እንደሚያወጣላቸው ስም (እነዚህ በብዛት የዛር መናፍስት የንግሥና ስሞች ናቸው) ጠቋር፣.. እየተባሉ ይጠራሉ:: በተጨማሪ በመጽሐፍ ቅዱስ አባዶን፣ ሌጌዎን፣ የሟርት መንፈስ፣.. በትርጓሜ መጽሐፍ እንደ ራእየ ዮሐንስ ላይ ደግሞ አብስትዮን (የሰው አእምሮ የሚለዋውጥ መንፈስ ነው) ሲባሉ ከላይ ባነሳናቸው መመደቢያዎች ውስጥ ስፍራ ሊያገኙ የሚችሉ የመናፍስት ስሞች ተጠቅሰዋል (በማርቆስ ወንጌል (ምዕ. 5) "ሌጌዎን ነን" ሲሉ ስማቸውን ራሳቸው የጠሩት መናፍስት ከሙሉ ታሪኩ ልናውቅ እንደምንችለው መቃብራት አከባቢ የሚኖሩ መናፍስት እንደመሆናቸው የመቃብር መናፍስት፣ በተለየ ስያሜም ከልከልዮስ ሲባሉ ዛሬ ይጠራሉ፤ (በማለዳ መያዝ ቅጽ 2፣ መምህር ግርማ ወንድሙ))::

አስጀምራ የምታስፈጽም ፈቃደ እግዚአብሔር ሳትለየን ትቆይ እንጂ: የመናፍስቱን ስያሜ በተመለከተ እዚህ ከተጻፈው ዘርዘር ያሉ አንቀጸ አሳቦችን የያዘ መጽሐፍ ላይ የሚከተብ ስለሚሆን ለማሰላሰያ ዕውቀት ያህል ከላይ የተጻፈውን ያህል ከተገለጠ ይበቃል:: የዚህ ጽሑፍ ዋናው መልእክት ግን የውጊያውን ትምህርት በአንድም በሌላም መንገድ የተማሩ ምእመናን የመናፍስቱ የስም አበዛዝን ተከትሎ እየተወናበዱ ስላለና ብቻም ሳይሆን መናፍስቱ የስማቸውን ብዛት ተከትለው የማጭበርበሪያ ጥበቦችን በመጠቀም ሰዎችን ግራ የማጋባት ሥራ ስለሚሠሩ እንጠንቀቅ ለማለት ያህል ነው:: ለምሳሌ አንድ በዕድሉ መዘጋጋት (እኔ መንፈሳዊ ዕድል ብል ደስ ይለኛል፤ የሥጋ ዕድል ተዘጋም አልተዘጋም ያው መጨረሻው ከመቃብር ስለማይሻገር: ሲሆን የሥጋ ዕድል በተሳካ ቁጥር መንፈሳዊ ሕይወትን የሚቃወምበት የራሱ ተጻራሪ ጎን ስላለው) ምክንያት ሲቸገር የከረመ ምእመን የተዋጋው መንፈስ ተይዞለት ሲናዘዝ "የዕድል መተት ነኝ" ሊል ይችላል:: ይቆይና ሌላው መንፈስ "ቡዳ ነኝ" ይል ይሆናል:: ሁለቱም ዞሮ ዞሮ የሰውን ነፍስ እስከወዲያኛው ለማጥፋት ሲሉ ዕድልን የማጥፋት አጋጣሚን እንደሚጠቀሙ ግለሰቡ ያልተገነዘበ እንደሆነ: በመተት ገባሁኝ ባዩ "የዕድል ነኝ" ስላለ: እርሱ ከወጣ በኋላ ቡዳው አሁንም ዕድሉን ሲዘጋበት ሰውየው ነገሩ ይወናከርበታል:: የመናፍስት ስም እየተጠራ ግብራቸውና የግብር ጠባያቸው በሚገለጽበት ትምህርቶች ላይ: ምእመናን በስማቸው እንጂ አንዱ ከአንዱ የሚለዩበትን መስመር ያጡታል:: እየበረቱ ወደ ሃይማኖት ጥልቅ ጎዳና እየተጓዙ ያሉ ምእመናን ሲኖሩ ደግሞ: የውጊያው ይዘት ሕይወታቸው ተከትሎ ስለሚለዋወጥ የመናፍስቱ ስም እየለዋወጡ መምጣት፣ መተጋገዝ፣ ስምሪት መቀያየርና የግብር ጠባይ መወራረስ ግራ መጋባታቸውን ጨምሮ የትኛውን መንፈስ መቼ እንደሚዋጉት ይዘበራረቅባቸዋል:: ስለሆነ: ምእመናን የመናፍስቱን ዓይነተ ብዙ ስያሜ እንደ መረጃ እየሰበሰቡ: በስማቸው ሥር የተገለጠውን ግብር፣ የግብር ጠባይና የመግቢያ መንገዳቸውን ግን እንደ ዕውቀት በልዩ ትኩረት በመማር: በዚህ ትምህርት የተመሠረተ ራስን የማስተካከል ሥራ ቢኖራቸው እላለሁ:: ያክርመን!

@bemaleda_neku
9.3K viewsedited  20:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 23:42:28 አስማተ ርኩሳን መናፍስት

ስሞች የሚለው የአማርኛ ብዙ ቁጥርን አመልካች ቃል በግእዙ አስማት ይባላል:: በዚህ የቋንቋ ትርጓሜ መሠረት አስማተ መናፍስት ስንል የመናፍስት ስሞች ስለማለታችን የተረዳ ይሆናል:: አንዳንድ ነጥቦችን በዚህ ስያሜአቸው ዙሪያ አጠር አድርገን እንደሚከተለው እንመልከት::

                ዲያብሎስ
         |
        |                             |
  ሰይጣናት________አጋንንት
                        |
    የሚገቡባቸው 5 መሠረታዊ መንገዶች

- መተት/ድግምት ፦ የጥፋት ስምሪት ከልዩ ተልዕኮ ጋር ተሰጥቶአቸው በሰዎች (መታች/ደጋሚ እና አስመታች/አስደጋሚ) አማካኝነት የሚመጡ መናፍስት
- ቡዳ ፦ ብዙ ጊዜ: ከሰው ውስጥ የቆዩ ሆነው ወደሌሎች በራሳቸው ፈቃድ ተነሥተው የሚመጡ መናፍስት (የብርጭቆ ውኃ ወደሌላኛው እንደሚቀዳው ያይደለ የሻማ እሳት ሌላን ሻማ እንደሚለኩሰው ያለ አመጣጥ ነው የሚመጡት፤ በአጭሩ ተነሥተው ሲመጡ ከመጡበት ተቀንሰው የሚሄዱ አይደለም)
- ዛር ፦ ከወላጆች ወደ ልጆች በዘር በኩል በማለፍ የትውልድን ሐረግ እየተከተሉ የሚመጡ መናፍስት
- በኃጢአት ግብር ፦ ኃጢአትን እንደ ይለፍ ፈቃድ በመውሰድ የሚገቡ መናፍስት
- የሚያንዣብቡ መናፍስት ፦ ሰውን ከሩቅ ተከታትለው አሊያ በሚዞሩበት ሰዓት ወይንም ግለሰቡ እነርሱ በወቅቱ ባሉበት ቦታ በመጣ ጊዜ በፍላጎታቸው የሚገቡ መናፍስት

ታሪኩ ከዓለመ መላእክት እንደሚጀምረው: በእግዚአብሔር እውነት ላይ በማዕረግና በከተማ ከፍ ብሎ የነበረው አንድ መንፈስ ከዋሸ በኋላ እርሱን ጨምሮ የተከተሉትና ለመከተል ያቅማሙ መናፍስት በአንድ ላይ ከሰማይ ስፍራ ተወግዘው እንዲለዩ ሆኖዋል:: (ይሄ: ሰማይ ላይ ጭራሽ አይገኙም ማለት አይደለም፤ ሰማይ (ሥዕለ-ማይ ይሉታል) ሲባል ከፍጡርነቱ በተጨማሪ የራሱ መንፈሳዊ ትርጓሜዎች አሉት:: ከነዚህ መካከል ነፍስ፣ መላእክት፣ ጽድቅ፣.. ይገኙበታል:: ስለዚህ ከሰማይ ተባረሩ ሲባሉ እነዚህንና መሰል ትርጓሜዎችን እንደ አየገባቡ ታሳቢ ማድረግ እንጂ ከፍ ብለው በአየር የሚንቀሳቀሱ መናፍስት የሉም የሚል አመለካከት እንዳይመላለስብን ይገባል:: ጳውሎስም በኤፌሶን (ም. 2) መልእክቱ "በአየር ላይ ሥልጣን ያለውን" ሲል ጠቅሶ የለየው ክፉ መንፈስን እንደሆነ አበው በአንድምታ መጽሐፋቸው ያስቀምጣሉ::) ዮሐንስ በራእይ መጽሐፉ "ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ" ሲል: መጀመሪያ የካደውና ዓመፅ ያስነሳው መንፈስ ከነተባባሪዎቹ ወደ ምድር እንደተወረወሩ የጻፈልን መንፈሳዊ ታሪክ ነው ከዓለመ መላእክት የሚጀመረው ትረካ እንዲኖር አንድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምክንያት የሆነው:: (ራእ. 12:9) ከአጻጻፉ ላይ ልናነብ እንደምንችለው 'ዘንዶው' ሲል የሚጠራውን መንፈስና ተከታዮቹን (መላእክቱም ሲል ያመላከታቸው) መሪና ተመሪዎች አድርጎ ለያየቶ አስቀምጦአቸዋል:: ከፍ ብሎ የተቀመጠው (ከፍታው በተፈጥሮ አይደለም) መንፈስ ሲዋሽ: ውሸቱን የተቀበሉትና ለመቀበል የዳዱት: በተለያየ ከተማ የነበሩትን ነገደ መላእክት ነው ባለራእዩ "ከእርሱ ጋር ተጣሉ" የሚለን (ውሸቱን ተቀብለው የመጣላቸውን ምክንያት በሚመለከት የተለያዩ አስተያየቶች አሉ፤ ከነዚህ መካከል አንዳንዶቹ ሐሰቱን ተቀብለው በዋሸው መንፈስ አስተዳደር ውስጥ እንገባለን ብለው የተጣሉ አሉ የሚሉ ሲሆኑ: አንዳንዶቹ መጀመሪያ የተሰማውን የሐሰት ቃል እንደ መነሻ ወስደው: ከላይ ያለው እንደኛ ሆኖ ሳለ ከፍ ማለቱን ሰበብ አድርጎ እገዛችኋለሁ ካለ እኛም ከሥራችን (በከተማ አቀማመጥ) ያሉትን እንመራቸዋለን ሲሉ በማመፃቸው የተጣሉ ናቸው ይላሉ)::

ዋናው እንዲወሰድ የሚፈለገው የታሪክ እውነታ ግን: ከሰማይ ስፍራ ተለይተው የተጣሉት የዓመፃ መናፍስት በቁጥር እጅግ በርካታ ስለመሆናቸው ነው (በሰው የአእምሮ ልክ ተሰፍሮ ሊወሰን አይችልም):: ከዚህም የተነሣ ሁሉንም በየተናጠል ለይተው ለይተው የሚጠሩ ስያሜዎች ከቶውኑ ሊኖሩ አይችሉም:: አጠቃላይ ግን: የሰውን ልጅ መፈጠር ተከትሎ እንደመጣው የመናፍስቱ ቅያሜ: ማንነታቸው እንዲገለጥ ከፈቀዱበት መገለጫ ጠባይ (ጠባይ የሚለው ቃል ባይስማማውም እንደ ጽሑፍ ልማድ እንጠቀመው) አንጻር በመሠረታዊነት ለሰው ልጅ የተገለጡ ስያሜዎች አሏቸው:: እነርሱም ፦

1ኛ. ዲያቢሎስ፦ ዖፍ ሥሩር፤ ነድ ውዑይ፤ ፈታዊ ማለት ነው፤ ዖፍ ሥሩር አለ ለመሳት ይፋጠናልና:: ነድ ውዑይ አለ ደዌ ትኩሳት እየሆነ ያማልና (አንድም ባሕርየ ተፍጥሮው በእሳት የተመሰለ ነውና)፤ ፋታዊ አለ አምላክነት ሲሻ ተገኝቷልና:: (ትምሕርተ ኅቡዓት) በዚህ ስያሜ አተረጓጎም መሠረትነት: አንድም ዲያቢሎስ ፈታዊ እንደመባል ቅድሚያ አምላክ ነኝ ሲል የዋሸውን፣ ዮሐንስ ዘንዶው ሲል የጠራውን አንድ መንፈስ ለይቶ ሲያመለክት፤ አንድም እኛም ከሥራችን ያሉትን እንገዛለን እንደሚለው አስተያየት ዘንዶው የተባለውን ጨምሮ መሪ ነን ለሚሉ በየደረጃቸው ከፍ ከፍ ያሉ መናፍስት የሚሰጥ ስያሜ ሲሆን: አንድም ዖፍ ሥሩር፣ ነድ ውዑይ እንደመባል ዘንዶውንም ሆነ ሁሉንም መናፍስት ስያሜው ይወክላል::

2ኛ. ሰይጣን (ሲበዛ ሰይጣናት)፦ መስተቃርን፣ መስተጻርር ማለት ነው (የጽድቅ ተቃዋሚ፣ በጎን ተቃራኒ ጠላት ለማለት ነው):: (ራእየ ዮሐንስ አንድምታ) ወደዚህኛው ስም ስንመጣ: እንደ ዮሐንስ አጻጻፍ ከሄድን ዘንዶውን "ዲያቢሎስና ሰይጣን የሚባለው" ሲል እንደሚጠራው: መጀመሪያ የዋሸው፣ በትንቢተ ኢሳያይስ (ም. 14) እና ሕዝቅኤል (ም. 28) ላይ በቁጥር አንድ ብቻ ሆኖ የተገለጠው፤ በራሳቸው በመናፍስቱ መዋቅርና አደረጃጀት እንደ አለቃ ተደርጎ የሚቆጠረው፤ አንዳንዶች ሳጥናኤል ሲባል ይጠራም እንደነበረ (የስም ግብሩን ቢቀይርም አሁንም በዚህ ስም ራሱን ሲጠራ ይደመጣል) የሚገልጹት፤ ሌሎች ደግሞ የኢሳያይስን ቃለ ትንቢት በመያዝ "የንጋት ኮከብ" መባሉ በአርማይኩ ቋንቋ የሚታወቀውን ሉሲፈር ያመለክታል የሚሉትን መንፈስ ለይቶ የሚጠራ ስያሜ ነው:: ለዚህም እንደ ተጨማሪ ማስረጃ የሚጠቀሰው በወንጌለ ሉቃስ (10፡18) ላይ "ሰይጣንን እንደ መብረቅ ከሰማይ ሲወድቅ አየሁ" የሚለው የመድኃኒታችን ንግግር ነው:: ግን: ሰይጣን የሚለው ስም እንደ አባቶች ትርጓሜ (መስተቃርን፣ መስተጻርር እንዳሉት) እና በተለያዩ ቀደምት መጽሐፍት ለምሳሌ እንደ መጽሐፍተ መነኮሳት (ማር ይስሐቅ፣ ፊልክስዮስ፣ አረጋዊ መንፈሳዊ) ያሉት: ሰይጣነ ዝሙት፣ ሰይጣነ ጸሪፍ (ስድብ)፣ ሰይጣነ ትዕቢት፣.. ሲሉ ከተለያዩ ግብራቱ ጋር እንደሚያያዙት ደግሞ ከሄድን በእርግጥ ሰይጣን የሚለው ስም የአንድ መንፈስ ብቻ ስም ነውን? የሚል ጥያቄ ያስነሣል:: ምክንያቱን መስተጻርር፣ መስተቃርን በሚለው ብናይ: ሁሉም ርኩሳን መናፍስት እንደ ጽድቅ ጠላትነታቸው፣ እንደ እውነት ተቃዋሚነታቸው ሰይጣን ተብለው ሊጠሩ ይገባል:: የጸሎት መጽሐፍትም (እንደ ሰይፈ መለኮት ያሉት) ሰይጣንን በብዙ ቁጥር ሰይጣናት ሲሉ ከአንድ በላይ የሆኑ መናፍስት የሚጠሩበት መሆኑን ያመለክታሉ:: ዞሮ ዞሮ ነገርየውን በአንድምታ አገላለጽ አንድ መልክ ብንሰጠው: አንድም ሰይጣን መባል እንደ ራእየ ዮሐንስና ሉቃስ አጻጻፍ አንድን መንፈስ የሚያመለክት የዘንዶው ሌላ መጠሪያ ሲሆን: አንድም መስተቃርን፣ መስተጻርር እንደሚለው የግብር አተረጓጎም ሁሉም ክፉ መናፍስት የሚጠቀለሉበት ስም ይሆናል::
7.1K viewsedited  20:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 22:06:50 በእንተ ፍቅር !

ሰው ከፍቅር ልዕልና ሲደርስ ኃጥእ፣ ጻድቅ፣ መናፍቅ፣ አማኝ፣ ዘመድ፣ ባዕድ ሳይል ሁሉን ይወዳል ይላሉ አባቶቻችን:: (፪ኛ የጴጥሮስ መልእክት አንድምታ) ይሄን ፍቅር ግሪኮች አጋፔ ሲሉ ጠርተውታል:: መጽሐፍም እግዚአብሔር "ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና" የሚለው ስለዚህ ሁሉን ስለሚወድ ፍቅር ነው:: (ዮሐ. ፫፥፲፮) ይሄ የፍቅር ልክ፥ ጠበል ነው:: ደዌያትን ሁሉ የሚፈውስ ኃያል ጠበል!

እስቲ እኛም ከዚህ ጠበል እንቋደስ:: እንቋደስና ሕመምተኛዋን ዓለም እንፈውሳት:: ዙሪያችንን እንጂ ሁሉንም መፈወስ አይጠበቅብንም:: በመሠረቱ ፍቅር አንድ ሆኖ ተዘርቶ ብዙ ፍሬ ሆኖ ይበቅላል:: ይሄም ፍሬ የመረረውን ያጣፍጣል፤ ተስፋን ይቀጥላል፤ ውስብስብንም ያቀላል:: አልገባ ብሎን እንጂ የመኖር ክብደቶች የተጫኑን የፍቅር ትከሻ ስለሌለን ነው:: 'ዓለም የተሸናፊዎች መድረክ አይደለችም' የሚሉ ርእዮቶች ዕውቀቶቻችን ከበው ስለመሸናነፍ አፎካከሩን እንጂ በፍቅር ከተቃመስነው ተፈጥሮ የተሰጠውስ በቂ ነበር:: ..እስቲ ፍቅርን ላለመስጠት ፍቅር አልተሰጠኝምን እንተው:: ፍቅር የምንረከበው ስጦታ ሳይሆን የምናቀብለው አስተሳሰብ ነው:: ሁለንተናችን ለአስተሳሰባችን ይገዛልና፥ ፍቅር ማሰቢያችን ከሆነ ዘንዳ የነፍስያችን ውበት በሥጋ መልካችን ይታያል:: በዚህም መታየት ውስጥ በሰማይ የተፈቀደው በጎ ፈቃድ በምድርም ይገለጣልና ከዚያን ወዲያ ርሃብና ጦርነት አይኖሩም፤ መከራና ሥቃይ ቦታ አያገኙም፤ ሰልፍና ሁከት ሊታወቁ አይችሉም:: አስቀድመው የሞሉ ጽዋዎች እንኳ ቢኖሩ በረከት እንጂ መቅሠፍትን አያፈሱም:: ምክንያቱም ፍቅር የቋጠረው ደመና የሕይወት እንጂ የጥፋት ውኃን አይይዝም:: ሕግጋትም ቢሆኑ በአንዱ ትእዛዝ ተፈጽመዋልና ስለ ኃጢአት የሚሸጉሩት አንድስ መቀርቀሪያ አይኖርም::


@bemaleda_neku
9.0K viewsedited  19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 13:52:23 ዘመን በክፋቶች ሲከበብ፣ አስተሳሰቦች ከእውነት ክበብ ሲወጡ፣ በዓመፃ ምክንያት ፍቅር ሲቀዘቅዝ፣ ውሸት በሁሉም አቅጣጫ ሲንሰራፋ.. ማንም የማይሠራባት ሌሊት ትመጣለች:: (ዮሐ. ፱፥፬) በዚህች የጨለማ ወቅት ሰዎች አይተያዩምና ማንም ለማንም አይደርስም:: ምልጃዎች አይሰሙም:: የእውነትና የምሕረት ቃሎች ይታፈናሉ:: በዚያች ማታ: ጥቁር ሥልጣን ያላቸው ክፉዎች ብቻ ይበረቱባታል:: ንግግራቸው በግድም እንኳ ይደመጥባታል:: ሰይፍና ጎመድ ይዘውም እውነትን ያስሩ ዘንድ ይከብባሉ:: (ራእ. ፳፥፱) እውነትም ኃያል ሳለች: ኃይል አልባ አቅመ ቢስ ትሆናለች:: ምክንያቱም የሚሰማት፣ የሚጠብቃት፣ የሚመሰክርላት አንድስ ወዳጅ አይኖራትም:: እኛም: በዚያች: ነግቶም ማታ፣ መሽቶም ማታ በሆነች ጊዜ ውስጥ ነን ያለነው::

ይሄን እንዲሁ ያልኩት አይደለም:: የምንማማርበት፣ የምንተጋገዝበት ጊዜ ያለፈበት የሚመስል ሁኔታ ውስጥ ስላለን ነው:: በዚህ ሰዓት ትምህርቶች፣ ተግሣፆች ዋጋ አጥተዋል:: ልመናም የሚሆንለት አይደለም:: ነገሩ ብዙም ባያስገርምም: ትንሽ የሚያሳዝነው የመጋደሉን ትምህርት ተምረዋል የተባሉ ወንድም እህቶቻችንም በአዙሪቱ ዛቢያ አብረው ሲሽከረከሩ ማየቱ ነው:: የክፉዎቹን ነገር ያላወቁት፣ በዓለመ መላእክት ተጀምሮ በሰው ባሕርይ ውስጥ በመገለጽ የቀጠለውን "ጥልቅ" ውጊያ ያልተረዱት፣.. የሚያደርጉትን ቢያደርጉ ይታዘንላቸዋል እንጂ አይታዘንባቸውም:: (ራእ. ፪፥፳፬ ፤ ሉቃ. ፳፫፥፴፬) ምክንያቱም ነብዩ እንደሚለው ራሳቸው ከራሳቸው ጋር አይደሉም:: (ኤር. ፲፥፳፫)

ቅሬታ የሚጭረውስ: በተወሰነ ልክም ቢሆን የውጊያውን ዓለም በሕይወት ተረድተውታል የተባሉ ወገኖቻችን እንዳልተረዱ ሆነው ሲመላለሱ ነው:: አሁን ግራ ያጋባል:: ለተስፋ መቁረጥም ይጋብዛል:: "መዋጋታችን በሰማይ አለቅነት ከነበሩ ከክፋት መንፈሳዊያን ጋር ነው" የሚለውን ቃል በኑሮ የተማሩ (?) ምእመናን ግርግሮችን ተቀላቅለው በየማኅበራዊ ሚዲያው ሲሰዳደቡ፣ የጥላቻ ቃላትን ሲያስተላልፉ፣ መዋጋታቸውን ደምና ሥጋ ከለበሱ ወገኖች ጋር ሲያደርጉ፣ ...

ስለዚህ ልክ ነው!.. ጽልመት የነገሠባት ሌሊት ሰማያችንን አጥቁራለች:: (ማር. ፲፫፥፳፬) እንደየአኗኗራችን በየአመለካከታችን ነግሣለች:: የሌሊቷ ጨለማነት ድምፆችን ሳይቀር ማፈን እስኪችል ያህል ድቅድቅ ያለ ነው (ሐሰት ቃሎች ጆሮዎችን በሚዘበዝቡበት በዚህ ወቅት: ዝም ያሉ አንደበቶች ምንኛ ብፁዓን ናቸው?):: ወደየትም ብንሄድ በጎነት ብርቅ ሆናለች:: ለምልክት ያህል ትኖራለች:: ዓይኖቻችንን በራሳችን ላይ ልናኖራቸው አልቻልንም:: በጎነት ጠፋች ሲባል: ወደ ውጪያቸው እንጂ ወደ ውስጣቸው የሚያተከሩ ማስተዋሎች የሉንም:: ስለሆነ ጥበብ ተሠውራለች:: በአንጻሩ በዓይነተ ብዙ አጀንዳ መካሰስ ተለምዳለች:: መንፈሳዊ ልምምዶች ቋጥኝ የመሸከም ያህል ከብደዋል:: በተቃራኒው የጽድቅ ዕሴቶችን የሚጋፉ ልምምዶች ለአፈጻጸም ቀለውናል:: እንደ ግል መጽናት ደግሞ እንደ ጋራ መደማመጥ፣ መረዳዳት፣ መተሳሰብ፣.. ተቀብረዋል:: ፍቅረ ቢጽ የተአምር ያህል በቀላሉ የማይገኝ ሆኖዋል:: አሁን እንኳ ይሄን አንብበን: ከደቂቃዎች በኋላ በላዩ ላይ ሌላ ዘወር ያለ ነገር ስናይበት አሊያ ስንሰማበት: የተነበበው እንዳልተነበበ ሆኖ ይጠፋል:: በገሐድ የማይታዩት በውስጣችን ግን የሚታዩት ክፉዎች መናፍስት ማጤናችንን ጠምጥመው ይዘዋል:: በየሰከንዱ ከውስጣችን በሚያጋሩት ሹክሹክታ: የኅሊና ድምፆችን እንደወረደ አስተናግደን በሰመመን እንድንጓዝ አስገድደዋል:: ውጪያዊ ሕዋሶቻችንም የነርሱ የሆነውን ብቻ እንዲሰበሰቡ አዋዋላችንን ሸብበዋል:: .. ከዚህ ሁሉ ማምለጥ የሚቻለው በፍቅር ነበረ:: እግዚአብሔርንና ሰውን በማፍቀር ነበረ:: ግን የለም:: ፍቅር የለም! .. አዎን፤ ማንም የማይሠራባት ሌሊት ከየልባችን ሰፈፍ ጠልላለች::
.
.
.

ቢሆንም:
ግን ደሞም እርግጠኛም ነኝ ሌሊቱ ይነጋል:: ማታ ዘወትሩን ሁሉ ተረኛ አትሆንም:: ቀኒቱ ፈረቃዋን ጠብቃ ትመጣለች:: ይሄ: ነፋስን የተከተለ ከንቱ ተስፋ እንዳይመስላችሁ! ይልቅስ ከጨቀየ ልቡና የመሸገ የጸዳሉ ቅንጣት: ስለቀኒቱ በምልዓት መገለጥ ከዐረቦኑ እያቀመሰ ያለመወላወል የሚያስመሰክረው በእውነት ጋሻ የተከበበ እምነት ነው፤ እምቢተኝነትን በልዝብ መውደዱ ሰርጅቶ ያሸነፈ ምናብን ሳይቀር የሚማርክ የተዋረደ ማንነትን የተቆጣጠረ ክቡር ኃይል ነው፤ ዓመፃ ከሰነጣጠቀው ከነፍስ ሰሌዳ ላይ ዕውቀቱን ጽፎ የሚያጽፍ የቅዱስ መንፈስ ንባብ ነው:: (ማቴ. ፲፥፳) እነሆም: በድንቁርና ጨለማ ውስጥ የክብሩን ዕውቀት ብርሃን ለልባችን የሚያበራ እግዚአብሔር ስሙ ይመስገንና: ምንም ሳያወላዳ በደመነፍስ ሲያመላልሰን የከረመውን የመናፍስቱ ግርዛዜ ያነሣዋል፤ እያነሣውም ነው:: ወንጌል: በጨለማ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ብርሃን ወጣላቸው የምትለው ይሄንን ነው:: (ም. ፬፥፲፮-፲፯) እንኪያስ የወይን ጠጅ ስካር እንደተወው ሁሉ ድንገት የምንነቃበት ጊዜ ያልተቀጠረ አይደለም:: (ሮሜ. ፲፫፥፲፩) ግና እንዳይረፍድብን! የዘይት ማሠሮአችንን በሰዓቱ ሳንሞላ ተኝተን: ሙሽራው ሲመጣ አላውቃችሁም እንዳይለን:: (ማቴ.. ፳፭) ቢያንስ ስንተኛ: ዘይቱን ይዘን እንተኛ:: ፍቅርን ያከበሩ አባቶቻችን ዘይትን ፍቅርም ብለው ይተረጉማሉ:: እንግዲያ ፍቅርን ሳንሸሽ እንዳለንበት ልዕልና እንኑር:: ባልንጀራዎችን ያለምንም መሥፈርት እንደራስ መውደድ ይግዛን:: ከዕንቅብ በታች ሊያኖሩት የማይቻል: ሌሊት የሌለበት በራሱ ብርሃን የሆነው ፍጹሙ ስብዕና "ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ" እንዳለን: እየመሹ እየነጉ ወደየግል ምጽዓቶቻችን እየወሰዱን ባሉት ቀናት ውስጥ ብዙውን ደቂቃ በበጎነት እናሳልፈው:: (ም. ፭፥፲፮) እንዲህ ሲሆን ከደጋግ ምሥራቆች የሚፈነጥቀው የንጋቱ ጮራ ያኮረፈውን የዓለም ሰማይ ወገግ ያደርገዋል::

"የብርሃኑ ፍሬ በበጎነትና በጽድቅ በእውነትም ሁሉ ነውና ለጌታ ደስ የሚያሰኘውን እየመረመራችሁ: እንደ ብርሃን ልጆች ተመላለሱ::" (ኤፌ. ፭፥፱-፲)
@bemaleda_neku
12.5K viewsedited  10:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 13:48:35
ኢትዮጲያ ሆይ: ተነሽ... ..ተነሺና የተነሡብንን ተነሽባቸው!
9.1K viewsedited  10:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 12:57:30 ዲያቢሎስን መዋጋት አማራጭ አይደለም፡፡ እንክርዳድ እንዳይበቅል ክፉ ዘርን ማስወገድ የግድ ነው፡፡ ክፉውን ዘር የሚዘራው ደግሞ የክፋት መንፈስ ነው፡፡ በቤታችን፣ በዙሪያችንና በምድራችን የምናየው ክፉ ፍሬ ሁሉ ከውስጣችን ባለ ክፉ ዘር የበቀለ ነው፡፡ እናም በአምላክ እርሻ ውስጥ ገብቶ የሚኮተኩተውን ወንጀለኛ ካላስቆምነው እንዲያድግ የሚጠበቀው ክፉ የሚያፈራው ዛፍ ነው፡፡

     "ነገር ግን አስቀድሞ ኃይለኛውን ሳያስር ወደ ኃይለኛው ቤት ገብቶ ዕቃውን ሊበዘብዝ የሚችል የለም፥ ከዚያም ወዲያ ቤቱን ይበዘብዛል።"

                                                                       (ማር. 3፥27)

ያለንባት ሥጋዊት ዓለም የክፉው መንፈስ ርስት ናት፡፡ ይሄን በብዙ ማብራሪያዎች በቀደሙት ክፍሎች ላይ ስላነሳነው፥ አንመለስበትም፡፡ በሥጋ ፈቃድ 'ብቻ' ታጥራ ያለቺው ዓለም የዲያቢሎስ ቤት ናት፡፡ ወደዚህች ቤት ገብቶ ባለቤቱ ያከማቻቸውን የክፋት ክምሮች ለመበተንና የደበቃቸውን የጽድቅ እውነቶች ለመበዝበዝ አስቀድሞ "የኔ ነው" እያለ አስተዳዳሪነትን ተጠምቶ የሚንጎራደደውን ቀማኛ መቀፍደድ ያስፈልጋል፡፡ አለበዚያ ባለንብረት ነኝ ይላልና ከሰው ውስጥ ተጠምቆ የተሰናዳው የእግዚአብሔር ወይን እንዳያብብ ፍሬውን አጫንቆ ይይዛል፡፡

ዓለም ላይ የሚስተዋሉት ክፋቶች እንዲቆሙ ክፋትን የሚመራውና የሚሠራው መንፈስ መቆም አለበት፡፡ ይሄ ነው ሰይጣንን መቃረን ከሆነ ነጠላ ጉዳይ የተያያዘ አይደለም የሚያሰኘው፡፡ ብርሃን እንዲገለጥ ጨለማው መገፈፍ አለበት፡፡ ጽልመት ያጠቆረው ክፍል ውስጥ ገብተህ መጋረጃውን ካልገለጥክ ጸዳልን እንዴት ታያለህ?

የመዳንን መንገዱ አለመዳንን የሚዋጋ ጠላትንም መዋጋት ነው፡፡ እውነት እንደ ዘበት የምንሰማትና የምናወራት አይነት አይደለችም፡፡ ሐሰትን በመታገል ውስጥ የምንኖራት ማንነት ናት፡፡ ላልጨነቀው፣ ለጊዜው ላልቸገረው፣ በልምድ ለቆየው፣ ያለማወቅ እሾህ ላነቀው የማይጨበጡ መናፍስትን መፋለም የማይመስሎ መስሎ እንዲሰማው በራሳቸው በመናፍስቱ ይገደዳል፡፡ ሁሉን የሰው ልጅ በየተናጠል ለማጥፋት በየሰኮንድ ርዝማኔው የሚቻኮለው የጥፋት መንፈስ ግን በሥራ ላይ ነው፡፡ ስለዚህ?

       "በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤ በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት።"

                                                              (1ኛ ጴጥ. 5፥8-9)

የሚቀድሰውም ሆነ የሚያረክሰው ከውስጥ የሚወጣው ነው ብለናል አይደል? ..ከማይታየው ውስጥ የሚወጣው በሚታየው ውጪ ላይ ይገለጣል፡፡ በማይታየው ውስጥም ሀሳብ፣ ፍላጎት፣ ስሜት፣ ዕውቀት፣ ወዘተ.. አሉ፡፡ እነዚህ ሥጋና ደም የላቸውም፡፡ ክፉውም መንፈስ ሥጋና ደም የለውም፡፡ በመሆኑ ከውስጥ የገባ ክፉ መንፈስ ከነዚህ ባሕርያት ጋር ራሱን ያስጠልላል፡፡ በሀሳቦች ውስጥ አማራጭ ሆኖ ይቀመጣል፡፡ ለሔዋን ጆሮ ያስደመጠውን ምክር ይለግሳል፡፡ ይህን ምክር ከተቀበለ ሀሳብ ጋር የተጋባ ስሜት ክፉ ቃልን ይወልዳል፡፡ ስድብ ወደ ውጪ ይገለጣል፣ ሐሜት ይደመጣል፣ ሐሰት ይነገራል፡፡ ሐዋሪያውማ ተናግርዋል እኮ.. በመጠን ኑሩ፥ ንቁ!

ጴጥሮስ "የሚውጠውን ፈልጎ" ስለማለቱ ያስተውሏል፡፡ አንድ ሕልውና ያለው አካል ዋጠህ ማለት የራሱ አደረገህ፣ እንደ ምግብ ተመገበህ፣ ከራሱ ጋር አስማማህ፣ አንተን ወደ ውስጡ አስገባህ (ከለለህ) ማለት እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ እንግዲህ በመንግሥታትና በሕዝቦች መካከል የምናየው ሰልፍና ሁካታ የዚህ በክፉ የመዋጥ ውጤት ነው፡፡ ሰውነት ተውጦ አውሬነት ተገልጦአል፡፡ መልካምነት ተበልቶአል፡፡ ያለ ትርፍ ምላሽ በጎ መሆን ስላቅ ሆኗል፡፡ አንባቢ ምን ተረዳህ?.. የጴጥሮስ መልእክት የሚስማማው ጽድቅን እየኖሩ ቅድስናቸውን ላላስዋጡ ሰዎች ነው፡፡ እኔና አንተ ግን በዘንዶው ሆድ ውስጥ ቁጭ ብለናል፡፡ በኃጢአት ተውጠናል፤ ቅናትንም የዕለት እንጀራ አድርገነዋል፤ ከኛ የሚወጣው ሁሉ ክፉው ኃይል ተመግቦ ያገሳው ሆኗል፡፡ ልብ ይዘን ተፈጥረን ሁለተኛ ልብ ፍለጋ ልብ ይሰጠን እያልን ተቀምጠናል፡፡ ምን ይሻላል?

"በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት" ይሻላል፡፡ ጸንቶ ከመቃወም የሚሻል መፍትሔ የለም፡፡ ዲያቢሎስን ከመዋጋት የተለየ መንፈሳዊ ትግል የለም፡፡ በይሁዳ ማሳሰቢያ ነገራችንን እንፈጽማለን ፦

     "እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፤ "ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኃጢአተኞች፥ እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ፥ ልባችሁን አጥሩ።" (የውስጡም ሲጠራ ለውጪውም እንዲሁ ይሆናል፥ እኛ ስንጠራ ዓለምም ትጸዳለች)

                                                                      (ይሁዳ. 4፥8)

ተጠናቀቀ!

@bemaleda_neku
15.3K views09:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 12:53:16 (የመጨረሻው ክፍል)

ላነሳው የፈለኩት ትልቁ የዚህ ማጠቃሊያ ክፍል ነጥብ ዲያቢሎስን መዋጋት ማለት ክፉውን ሁሉ መፋለም ነው የሚለውን ነው፡፡ በራስም ሆነ በዓለም ላይ ያለውን ክፋት ሁሉ በጽድቅ ተቃርኖ መታገል የምእመንነት ዋነኛው ኃላፊነት ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እባብ ወደ ሔዋን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ በሰው ልጆች ሕልውና ውስጥ በመከሰት ግራና ቀኝ ስለሚያደርጉት የርኩሰትና የቅድስና መተናነቅን በሚያስተነትኑ ታሪኮች የተሞላ መጽሐፍ ነው፡፡ በክፉው ዕውቀት እና በደጉ ዕውቀት መካከል የሚዋተት የባሕሪያችን የዘመናት ጉዞ ዓለምን አሁን እስካለችበት ድረስ አምጥቷል፡፡ በቃ ከፀሐይ በታች አዲስ ነገር የለም! መልካምና ክፉ ተብለው ከተከፈሉት ውጪ ያለ አንድም ነገር የለም፡፡

እግዚአብሔር መልካም ነው፡፡ የእርሱ መልካምነት ከእርሱ የተገኙትንም ሁሉ ነገሮች መልካም አድርጓቸዋል፡፡ በእርሱ እውነትና ፈቃድ ውስጥ ለመኖር ይሄን መልካምነት መምረጥ የውዴታ ግዴታ ነው፡፡ ሌላ ቀመር፣ ስልት፣ ንድፈ ሀሳብ የለም፡፡ የሃይማኖት መንገድ ሌላ ጎዳና የለውም፡፡ አምላክን ለማወቅና እርሱን ባወቅንበት ዕውቀት ውስጥ ለመቆየት መልካሙን መቀበልና ተቀብሎ መግለጥ ያስፈልጋል፡፡

ይሄ በእንዲህ ሳለ፥ መልካምነት የማይሳማማው ፍጡር በምድራችን ላይ እንዳለ አማኞች ያለ መዘንጋት ማጤን ይገባቸዋል፡፡ እግዚአብሔርንና የእግዚአብሔርን ሁሉ የሚቃወም ባዕድ ኃይል ባለንባት ዓለም ላይ አለ፡፡ የበጎ ነገር ጠላት ሲሆን የምናየው ማንኛውም ነገር የዚህ ተቃዋሚ መንፈስ ውክልና ነው፡፡

እንደጠቀስነው ከእግዚአብሔር ባሕርይ ነቅተው የወጡት ሁሉ መልካም ሲሆኑ፥ ሰው መሆንም መልካምነት ነው፡፡ ክፉው ደግሞ መልካሙን ይፋለማል ካልን ሰው እንዳንሆን ይጻረራል ማለትን እናገኛለን፡፡ የዲያቢሎስ ሥራ በጠቅላላው እግዚአብሔር መልካም እንደሆነ አስቀድሞ ያየውን ሰውነትን እንዳንኖር ማድረግ ላይ ያጠነጥናል፡፡ ይሄንን በሚገባ ካልተረዳነውና ካልስተዋልነው፥ ከእግዚአብሔር ጋር ያኖረናል የምንለውን መንፈሳዊ ሕይወት መኖር በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡

ነገሩ (አለመረዳቱና አለማስተዋሉ)፥ እንኳን መንፈሳዊውን ተሸብበንበት ያለውን ሥጋዊውን አኗኗር እንኳ በቅጡ መኖር የሕልውና ጥያቄ ውስጥ እንዲወድቅ ያደርጋል፡፡ በመሠረቱ ከመንፈሳዊነት የጀመረ ነጻነት ነው በሥጋው ኑሮአችን ሊገለጥ የሚችለው፡፡ ዕረፍት ያላገኘ ውስጥ የትም ቢወርድ የትም ቢወጣ እፎይ ሊል አይችልም፡፡ የሰላም መንፈስ ያለገራው ሕሊና መረጋጋትን ቢናፍቅ እንጂ አያገኝም፡፡ በማንነት መዝገባችን ላይ የተጻፈው ክታብ መልካሙ ጽሑፍ እስካልሆነ ድረስ በመሬታችን የምንመለከተው ውጥንቅጥ ሁሉ ለዘለቄታው ሊሰክን አይችልም፡፡

       "መልካም ሰው ከልቡ መልካም መዝገብ መልካም ነገርን ያወጣል፥ ክፉ ሰውም ከክፉ መዝገብ ክፉ ነገርን ያወጣል።"

                                                                    (ማቴ. 12፥35)


የዲያቢሎስ መሠረታዊ ፍልሚያ እግዚአብሔር በፈቃዱ ያስገኘውን መልካም ሰው እንዳንሆን መታገል ነው ብለናል፡፡ ይሄን ትግሉን ለማሳካትም በስብዕና ማኅደር ውስጥ ዘልቆ በመግባት የርሱን የክፋት ባሕርይ ያሰፍራል፡፡ እንደ ባላጋራነቱ ተፈጥሮአዊው መዝገባችንን አስቀድሞ በመጋራት የርሱን ማንነት ለኛ ያጋራናል፡፡ ከዛ በኋላ ወደ ውጪ ሲገለጥ የሚታየው ሁሉ ከውስጥ የታሰበው፣ የተፈለገውና የተለመደው ይሆናል፡፡

ጌታ ለተማሪዎቹ ያዛቸዋል፡፡ መንግሥተ ሰማያት መቅረቧን ስበኩ እያለ ይልካቸዋል፡፡ መስበክ ብቻ ሳይሆን የተቸገሩትንም እንዲያግዙ እንዲህ ይሳስባቸዋል፦

       "ድውዮችን ፈውሱ፤ ሙታንን አስነሡ፤ ለምጻሞችን አንጹ፤ አጋንንትን አውጡ፤ በከንቱ ተቀበላችሁ፥ በከንቱ ስጡ።"

                                                                      (ማቴ. 10፥8)


አጋንንትም 'ወጡ' መባሉ መቼም ከውስጥ ወደ ውጪ ነው፡፡ ከሰው ውስጥ! የሰው ውስጡ ደግሞ መዝገቡ ነው፡፡ መዝገብ ባለበት በዚያ ልብ ደግሞ ይኖራል፡፡ በዚህ መዝገብ የተጻፈው በሕይወት ፊት ላይ ይነበባል፡፡ የምናስበውን እንናገራለን፣ የምንፈልገውን እንከውናለን፡፡ ከውስጣችን ያለው ውጪያችንን ይነግራል፡፡ በገሐድ የምትታየዋ የዛሬይቱ ዓለም የብዙ ውስጠቶች ውጤት ናት፡፡

ዓለም እኔ፣ አንተ፣ አንቺና ሁላችንን ነን፡፡ የእያንዳንዳችን የሕይወት መልክ የዓለምን ነባርም ነባራዊም መልክ አስገኝቷል፡፡ ዓለም ላይ ሲገለጥ የታየው ሁሉ ዓለም ውስጥ የምንኖረው እኛ የገለጥነው ነው፡፡ እንግዲህ ዓለም ክፉ ናት፣ ኢ-ፍትሐዊ ናት፣ ውሸታም ናት፣.. ስንል የዓለም መዝገቧ ስለሆንነው እኛ እያወራን ነው፡፡ ስንት ርኩስ ሀሳቦች፣ ክፉ ቃሎች፣ ስግብግብ ድርጊቶች፣ ዝብርቅርቅ መሻቶች፣ ትዕቢት ጠባዮች፣ ዓመፃ ስሜቶች ይሁኑ ዓለምን ያበላሹት?.. ቤቱ ይቁጠራቸው!

አንባቢ! በልብ መዝገብህ ውስጥ ተጽፎ እስኪታተም ድረስ ደጋግሜ እጽፈዋለሁ፡፡ ክፉ የሆነው ሁሉ ከክፉው ዲያቢሎስ ነው፡፡ ዓለም ስትፈጠር ክፉን አውቃ አልተፈጠረቺም፡፡ ዘፍጥረት አንድን ማንበብ የምለውን ያረጋግጥልሃል፡፡ መልካም ሳይሆን የተፈጠረ አንድም ነገር የለም፡፡ የፈጣሪ መልካምነት የተፈጠረውን ሁሉ መልካም አድርጎ አስገኝቶታል፡፡

ስለዚህ ዓለምን አበላሹ የምንላቸው በኛ የተገለጹ ክፋቶች ሁሉ ከክፉው መንፈስ ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡ ከልብ ውስጥ የሚወጡት "መግደል፥ ምንዝርነት፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ በውሸት መመስከር፥ ስድብ" ሁሉ የእርሱ ናቸው፡፡ (ማቴ. 15፥19) ይህንን በመተማመን ክፉውን መዋጋት ካልጀመርን በእርግጥም ዓለምን ከመክፋት የሚመልሳት የጽዋው ሙላት ብቻ ይሆናል፡፡ የጽዋውም ሙላት መቅሠፍት ነው፡፡ ከመቅደስ ጀምሮ እያንዳንዱን ክፋት እየመነጠረ የሚያጠፋ ታላቅ መቅሠፍት!

ከውስጥ የሚወጣው ነው የሚያረክሰው፡፡ ዓለም በመላዋ በክፋት እንድትያዝ ያደረጋት የአብዛኞቻችን በመልካም ያልተያዘ ውስጥ ነው፡፡ በሌላ አባባል በሕይወታችን ውስጥ ያሉ ክፉ መናፍስት ዓለምን አክፍተዋታል፤ በባሕርያቸው ባለው ጥላቻ ፍቅርን አቀዝቅዘዋታል፡፡ ፖለቲካ፣ ቴክሎኖጂ፣ ሳይንስ፣ ጥበብ፣.. ከፍታውን አግኝቷል በምንልበት በዚህ የሥልጣኔ ዘመን ክፋትም የራሱን የከፍታ ጫፍ እንዳገኘ እናያለን፡፡ ሰውነት ጎድሎ፥ ለሰው የሚያስፈልጉት ቁሶች ግን ሞልተዋል፡፡ በጎነት ከሰው ሕልውና ሸሽታለች፡፡ ውሸት አምሮባታል፥ ወፍራለች፡፡ ግብዝነት ተለምዳለች፡፡ ገንዘብ ከጭንቅላት ዙፋን ነግሣለች፡፡ ደግነት ተደብቃለች፡፡ እውነት መኖሯ እስኪያጠራጥር ድረስ ዝምታን መርጣለች፡፡ ይሄ ሆኖ ሳለ ነገሩን ይበልጥ የሚያከፋው ደግሞ የዓለም እንዲህ መክፋት ምናችንም ያልሆነ ያህል የሚሰማን ጥቂት የምንባል አይደለንም፡፡ አዎ በትክክልም.. ከውስጣችን የተከማቸ አንዳች ክፉ ጉድ አለ!

"ዓለሙን ሁሉ የሚያስተው ዲያቢሎስ.." ሲል የእግዚአብሔር ቃል የሚነግረንን እያየን የማናይ ዓለማዊያን፥ ከብዙ መልካም ነገር ስተንና ሌሎችንም እያሳትን ይኸው አለን፡፡ (2ኛ ጢሞ. 3፥13) ቅድስናን የሳቱ አእምሮዎች ምን ያህል ቀውስ እስከዛሬ አመጡ ይሁን? ጽድቅን የሳቱ ልቦናዎች ምን ያህል እርግማንን አቆዩልን ይሁን? ከእግዚአብሔር የሳቱ መሪዎች ምን ያህል ጦርነት አስከተሉ ይሁን?..
9.8K views09:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ