Get Mystery Box with random crypto!

ATC NEWS

የሰርጥ አድራሻ: @atc_news
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 116.41K
የሰርጥ መግለጫ

#ADDIS_ABABA : ETHIOPIA
ለመልዕክት 👇🏻
@mujaabot
For Advertisement👇🏿
@atcads

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 69

2023-04-30 18:13:55
Kerawd Shopping Center

ሁሉም ምርጫዎ በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያገኙበት ቻነል
ባሉበት ይዘዙን ያሉበት ድረስ በነፃ እናደርሳለን



t.me/kerawdshoppingcenter
http/:www.ksc
@Karesc23/251954887440
11.5K viewsMuJa. M, 15:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 18:13:37
በርካታ የመኪና ግብይት አማራጭ ያሉትን ይህን ቻናል ይቀላቀሉ፣ ይጎብኙ፣ ይገበያዩ!

http://T.me/EthioCarMarket
10.8K viewsMuJa. M, 15:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 14:05:13
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች በከተማው የተገነቡ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ።

ጉብኝቱ የተካሄደው ለሚኩራ ክፍለ ከተማ በመገንባት ላይ በሚገኘው የገበያ ማዕከል፣መገናኛ አከባቢ በመገንባት ላይ የሚገኘው የትራፊክ መቆጣጠሪያ ማዕከል፣እንዲሁም በቅርቡ ግንባታቸው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት በጀመሩት አብርሆት ቤተመ ፀሕፍት እና ወዳጅነት ፓርክ ቁጥር 2 ነው።

ጉብኝቱ በዋናነት መምህራን በትውልድ ግንባታ ሂደቱ የአንበሳውን ድርሻ እንደመወጣታቸው በከተማው በከፍኛ ወጪ የተገነቡ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተው በሀገር ግንባታ ሂደቱ የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ለማስቻል ታስቦ መካሄዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አሊ ከማል አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ መምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት አቶ ድንቅአለም ቶሌሳ በበኩላቸው በጉብኝቱ ትላልቅ ፕሮጀክቶች በከፍተኛ ፍጥነት ተገንብተው መጠናቀቃቸውን ከማረጋገጣቸው ባሻገር መምህራን ያፈሯቸው ባለሙያዎች ይህን የመሰለ ግንባታ ገንብተው በመመልከታቸው ከፍተኛ ደስታ እንደፈጠረባቸው አስረድተዋል።

የጉብኝቱ ተሳታፊ መምህርን እና የትምህርት አመራሮች እነዚህን ታላላቅ ፕሮጀክቶች መመልከታቸው ከፍተኛ ደስታ እንደፈጠረባቸው ጠቁመው የጉብኝቱን መርሀ ግብር ላዘጋጀው ትምህርት ቢሮ ምስጋና አቅርበዋል።


፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
12.1K viewsMuJa. M, 11:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 09:59:01
በአዲሱ የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ መዋቅራዊ አደረጃጀት መሠረት የከተማ ልማት ጥናት ፋካልቲ እና የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፋካልቲ ተብሎ ይጠሩ የነበሩ ታጥፈውና የሙዚቃና ስነ-ጥበብ ትምህርት ክፍል አካቶ የቢዝነስ፣ ቴክኖሎጂና ቮኬሽናል ኢዱኬሽን ኮሌጅ በሚል ስያሜ እንደአዲስ መደራጀቱ ዛሬ ሚያዚያ 19/2015 ዓ.ም ይፋ ተደርጓል፡፡

በዚሁ አዲስ ኮሌጅ ስለመቋቋሙ ይፋ በተደረገበት መርሀግብር ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና እንደገለፁት፣ ኮተቤ የሀገሪቱ ብቸኛ የትምህርት ዩኒቨርስቲ ሆኖ መስከረም 24/2014 ዓ.ም በአዋጅ ከተቋቋመበት ማግስት ጀምሮ ተልዕኮውን ማዕከል ያደረጉ ዘርፈ- ብዙ ሥራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል። ከእነዚህም አንዱ የትምህርት ሥርዓታችንን ክፍተት የሚሞላ የቢዝነስ፣ ቴክኖሎጂና ቮኬሽናል ኢዱኬሽን ኮሌጅ የማቋቋም ሥራም አንዱ ነበር ። በዚሁ መሠረት በሂደቱ የሚያስፈልጉ የማቋቋሚያ ሰነዶች እና ካሪኩለም ፍሬም ወርክን ጨምሮ የተለያዩ የሽግግር ሥራዎች ተጠናቅቀው ዛሬ ኮሌጁ አመራር ተሰይሞለት በይፋ መቋቋሙን አብስረዋል።


በመጨረሻም ኮሌጁን በዲንነት እንዲመሩ የተሾሙት ዶ/ር ይፍሩ ዋቅቶሌ በየደረጃው ካሉ የሥራ ባልደረቦች ጋር በመሆን ኮሌጁን የማደራጀት ከፍተኛ ኃላፊነት እንዲወጡ ከአደራ ጭምር በማሳሰብ የሽግግር ሰነድ ርክክቡ ተከናውኗል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የህዝብና አለምአቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት

፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
3.6K viewsMuJa. M, 06:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 08:24:30
የኢንተርኔት አገልግሎት ላለፉት ሁለት ሳምንታት መቋረጡ በትምህርታቸው ላይ ጫና እየፈጠረባቸው እንደሚገኝ የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተናገሩ፡፡

አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ ከመምህራን የሚሰጣቸውን የቤት ሥራም ሆነ በግላቸው የሚፈልጉትን ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት መቸገራቸውን ተማሪዎቹ ለሪፖርተር ጋዜጣ ተናግረዋል፡፡

ምንም እንኳን ከየካቲት ወር ጀምሮ በመላ አገሪቱ የኢንተርኔት አገልግሎት የተቋረጠ ቢሆንም፤ ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ ግን አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ መቋረጡን ተማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ በወልድያ፣ በቆቦ እና በአላማጣ ከተሞች የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ #ሪፖርተር


፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
6.4K viewsMuJa. M, 05:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 21:42:50
#Update

ከ63ሺህ በላይ የትምህርት አመራሮች እና መምህራን የተሳተፉበት ውይይት መድረክ በሁሉም ክፍለ ከተማዎች በከሰአት ውሎውም ተጠናክሮ ቀጥሎ ነበር።

የውይይት መድረኩ "የትምህርት ተቋማት ለመማሪያ መምህራን ለማስተማር"በሚል መርህ በ77 የመወያያ ማዕከላት የተካሄደ ሲሆን በነገው እለትም የሚቀጥል ይሆናል።


ውይይቱ የጋራ መግባባትን ለመፍጠር ፤ የትምህርት ስርአቱ የተሳለጠ እንዲሆንና ዘመኑን የዋጀ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር ይረዳል።


፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
10.4K viewsMuJa. M, 18:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 19:17:12
#Tigray

ከዓመታት በኃላ በትግራይ ያሉ #ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ ምዝገበ እየተካሄደ ይገኛል።

የትግራይ ትምህርት ቢሮ  ለዓመታት በኮቪድ-19 እና በጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የቆየውን መደበኛ ትምህርት ለማስጀመር ከሚያዚያ 18 ጀምሮ ምዝገባ እንደሚከናወን እና ሚያዚያ 23 ትምህርት እንደሚጀመር ማሳወቁ የሚዘነጋ አይደለም።

ተማሪዎች ያለፋቸውን ጊዜ ለማካካስ በሳምንት 3 የትምህርት ፕሮግራሞች የነበሩትን ወደ 5 እና 6 በመቀየር አንድ ሴሚስተር የሚጨርሰውን ጊዜ ለማሳጠር እንደሚሰራ መነገሩም ይታወሳል።

በትግራይ ጦርነት ምክንያት ክፉኛ ከተጎዱት መካከል #ተማሪዎች ዋነኛዎቹ ሲሆኑ ተማሪዎች ለበርካታ ወራት ከትምህርት ርቀው ይገኛሉ።

እንደ ህፃናት አድን ድርጅት (Save the Children) መረጃ በትግራይ 2.3 ሚሊዮን ሕጻናት ወደ ትምህርት ገበታቸው አልተመለሱም።

ፎቶ ፦ ድምፂ ወያነ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
11.4K viewsMuJa. M, 16:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 19:15:34
በርካታ የመኪና ግብይት አማራጭ ያሉትን ይህን ቻናል ይቀላቀሉ፣ ይጎብኙ፣ ይገበያዩ!

http://T.me/EthioCarMarket
8.7K viewsMuJa. M, 16:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 19:15:26
#Ad

ከ9ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ የ #Mathematics ሁሉንም ቻፕተሮች ቲቶርያል ቪድዮ ከፍላቹህ መጠቀም ለምትፈልጉ የ2015 የዩንቨርሲቲ መግቢያ ተፈታኝ ተማሪዎች #ምዝገባ ጀምረናል።


ሺድዮዎቹ የተዘጋጁት በቀጥታ ከተማሪዎች የመማሪያ መጽሀፍት ነው።

ቪዲዮዎቹ በአብዘሃኛው የተዘጋጁት በ Screen recorder ሲሆን ሰፊ ማብራሪያ የሚፈልጉ ርዕሶች በቦርድ ተሰርተዋል።

ሁሉም ቪድዮዎች ክፍያ የፈፀሙ ተማሪዎች ብቻ የሚገቡበት Private የቴሌግራም ቻናል ላይ ተጭነዋል።

ክፍያ ፈፅመው ቪድዮዎቹ የሚገኙበት ቻናል ላይ የሚቀላቀሉ ተማሪዎች በራሳቸው ፕሮግራም መሰረት በቲቶርያሎቹ ይማራሉ።

እነኚህን ቪዲዮዎች ከፍለው የሚማሩ ተማሪዎች በቲቶርያሉ ላይ ያልገባቸውን ማንኛውም ጥያቄ መጠየቅ ይችላሉ።

ክፍያ የፈፀሙ ተማሪዎች ቪድዮዎቹ የሚገኙበት ቻናል ላይ የሚቆዩት የዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተና እስኪወስዱ ድረስ ብቻ ነው።


ቪድዮዎቹ የቀረቡበት ዋጋ
*G9 all Chapters 200ብር
*G10 all Chapters 200ብር
*G11 all Natural Chapters 250ብር
*G12 all Natural Chapters 250ብር

4ቱንም ለሚፈልጉ ተማሪዎች የ2010 እና የ2011 #UEE Solution Video ተጨምሮ በ1000 ብር ቀርቧል።


#REMEDIAL ፕሮግራም ለምትማሩ ተማሪዎች የምትማሯቸውን የ #Mathematics ሁሉንም ቻፕተሮች ከዚሁ ቲቶርያል ተቀንሰው በ300 ብር ቀርቦላቹሃል።

ፊዚክስ መማር ለምትፈልጉ በነፃ Click

ለመመዝገብ @muedu
ለተጨማሪ መረጃ 0977894547
8.6K viewsMuJa. M, 16:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 14:05:02
የዩኒቨርሲቲ ምሩቃንን አሰልጥኖ ወደ ውጭ ሀገር ለስራ ለማሰማራት እንቅስቃሴ መጀመሩን የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ገለጸ

የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲ ምሩቃንን አሰልጥኖ ወደ ውጭ ሀገር ለስራ ለማሰማራት እንቅስቃሴ መጀመሩን አስታወቀ። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 85 ሺህ ዜጎችን ወደ ውጭ ሀገር ለስራ ለማሰማራት አቅዶ ማከናወን የቻለው 66 በመቶ ብቻ ነው ብሏል። በዚህ ጊዜ ውስጥ ስድስት ሚሊዮን ዜጎች በስራ ፈላጊነት መመዘገባቸውንም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይህን የገለጸው ትላንት ሐሙስ ሚያዝያ 19፤ 2015 የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸሙን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበበት ወቅት ነው። የስራ እና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል፤ በስራ እድል ፈጠራ፣ በቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና እንዲሁም በውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ላይ መስሪያ ቤታቸው ያከናወናቸውን ስራዎች ለፓርላማው አብራርተዋል።

የሚኒስትሯን ሪፖርት ተከትሎ ጥያቄዎችን ከሰነዘሩ የፓርላማ አባላት አንዱ የሆኑት አቶ ዮሃንስ መስፍን፤ “የውጭ ሀገር የስራ አማራጮችን ተጠቅሞ ለዜጎች ብቁ ስራ ዕድል ለመፍጠር ምን ታስቧል?” የሚል ጥያቄ አቅርበዋል። በስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የአሰሪ እና ሰራተኛ ጉዳይ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታው አቶ አሰግድ ጌታቸው ለዚህ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፤ ከውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ጋር በተያያዘ የመዳረሻ ሀገራትን ለማበራከት ጥናት መጀመሩን ተናግረዋል።


፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
12.4K viewsMuJa. M, 11:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ