Get Mystery Box with random crypto!

ATC NEWS

የሰርጥ አድራሻ: @atc_news
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 116.41K
የሰርጥ መግለጫ

#ADDIS_ABABA : ETHIOPIA
ለመልዕክት 👇🏻
@mujaabot
For Advertisement👇🏿
@atcads

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 68

2023-05-09 19:01:27
#የሐዘን_መግለጫ!

●●●●●

የአንደኛ ዓመት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪያችን የነበረው ተማሪ አበባው ስንሻው መጸዳጃ ቤት ውስጥ ገብቶ የመጸዳጃ ቤቱን በር በመቆለፍ በራሱ ቀበቶ ራሱን አጥፍቶ በመገኘቱ ዩኒቨርሲቲያችን የተሰማዉን ጥልቅ ሐዘን ይገልፃል። ተማሪው እዚህ አሳዛኝ ውሳኔ ላይ እንዲደርስ ያበቁትን ጉዳዩች ተጨማሪ ማጣራት የሚያስፈልግ ቢሆንም ፈተና ከበደኝ በሚል ሲጨናነቅ እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ። ስለሆነም ለቤተሰቦቹ ፣ ለጓደኞቹና ለዩኒቨርስቲያችን ማህበረሰብ በሙሉ መፅናናትን እንመኛለን!

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
19.5K viewsMuJa. M, edited  16:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 19:00:06
በርካታ የመኪና ግብይት አማራጭ ያሉትን ይህን ቻናል ይቀላቀሉ፣ ይጎብኙ፣ ይገበያዩ!

http://T.me/EthioCarMarket
17.3K viewsMuJa. M, 16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 17:09:20
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ 6ኛ እና 8 ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ቀናት ይፋ አደረገ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ የ 8ኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 19 እና 20 እንዲሁም የ 6ኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 26 እና 27 እንደሚሰጥ ተናግረዋል::


አያይዘውም ቢሮው ከተማ አቀፍ ፈተናዎቹን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመስጠት ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን የተናገሩ ሲሆን ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቹን የበለጠ ማዘጋጀት እንዲችሉ ከከተማና ክፍለ ከተሞች ጋር በጋራ በመሆን የሞዴል ፈተናዎችን እንዲሰጡ አሳስበዋል ::


በ 2015 ዓ. ም 75,100 የ8ኛ እንዲሁም 75,078 የ 6ኛ ክፍል ተማሪዎች ከተማ አቀፍ ፈተናውን እንደሚወስዱ ከስራ ክፍሉ ያገኘነው መረጃ ያሳያል ::


፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
19.8K viewsMuJa. M, 14:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 14:18:10
በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አንድ ተማራ ተገድሎ ተገኘ


ዛሬ ግንቦት 01/2015 በደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ አንድ ተማሪ ተገድሎ መገኘቱን እና በዚህም ምክንያት በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ስጋት መፈጠሩን የተቋሙ ተማሪዎች ነግረውናል።

በጉዳዩ ዙሪያ ለቲክቫህ መረጃ የሰጡት የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ድርቧ ደበበ (ዶ/ር)፤ "ፖሊስ ጉዳዩን የያዘው መሆኑንና ምርመራ እያደረገ እንደሚገኝ" ገልጸዋል።

ሟቹ ተማሪ "ቅዳሜ ዕለት የታየ መሆኑን ለሦስት ቀናት ጠፍቶ መቆየቱን" ኃላፊዋ አመልክተዋል።

የተማሪውን ተገድሎ መገኘት ተከትሎ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ አለመረጋጋት መፈጠሩንና የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችም ከፀጥታ አካላት ጋር መጠነኛ ግጭት ውስጥ ገብተው እንደነበር ከተማሪዎቹ ሰምተናል።አሁን ላይ አለመረጋጋቱ በፀጥታ አስከባሪዎች ቁጥጥር ስር እንደሚገኝም ለማወቅ ተችሏል።

ዩኒቨርሲቲው በበኩሉ የተማሪው ማንነትና የግል ማህደር በማጣራት ላይ መሆኑንና በቀጣይ መረጃ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

በዚህ ዓመት ብቻ የተቋሙ ተማሪ ተገድሎ ሲገኝ ይህ የመጀመሪያ አለመሆኑንም ተማሪዎቹ ጨምረው ጠቁመዋል።


፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
20.1K viewsMuJa. M, 11:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 14:07:37

ባሳለፍነው ቅዳሜ ማለትም በቀን #21/08/2015 ከጥዋቱ 1፡50 ላይ በእንጅባራ ዩንቨርሲቲ በተምዶ ኪዳነምህረት መግቢያ በመባል በሚታወቀው በር በኩል የዩንቨርሲቲው የሆቴልና ቱሪዝም ማኔጅመንት ተማሪ የሆነችው ተማሪ ኤደን ገብሩ ከቤተክርስቲያን መልስ የግቢ መታወቂያ ( ID Card ) አለመያዟን ተከትሎ ከዩንቨርሲቲው ተረኛ የጥበቃ ሠራተኞች ጋር በተፈጠረ አለመግባባት በደረሰባት አካላዊ ጥቃት ምክንያት በአሁኑ ሰዓት ተማሪዋ ከባድ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ በርካታ የእንጅባራ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ጥቆማ አድርሰውናል።

ይህንን ጥቆማ በመቀበል ጉዳዩን ለማረጋገጥ ጉዳት የደረሰባት ተማሪ ጋር እንዲሁም የዩንቨርሲቲው ተማሪዎች ህብረትን አናግረናል።


<ተማሪ ኤደን ገብሩ ጋር በደወልንበት ጊዜ ተማሪዋ በስልክ ለማውራት አቅም ስላጠራት አጠገቧ ከነበሩት ጓደኞቿ ነው መረጃውን ያገኘነው>

ጉዳት በደረሰባት ተማሪ የእጅ ስልክ ደውለን ያገኘነውን መረጃ በአጭሩ ለመግለፅ

[ተማሪዋ ወደ ቤተክርስትያን ስትሄድ የግቢ መታወቂያ ትረሳለች። ወደ ግቢ ስትመለስ የግቢ መታወቂያ እንዳልያዘች በመንገር በመመገቢያ ካርድ ያስገቧት ዘንድ የጥበቃ ሠራተኞችን ስትጠይቅ አንዱ ጥበቃ ይገፈትራታል። አትገፍትረኝ ብላ እጁን ለማስለቀቅ ስትሞክር በጥፊ ይመታታል። ለምን በጥፊ ትመታኛለህ ስትለው በድጋሚ ገፍትሮ ጥሎ ጭኗ አካባቢ ይረግጣታል። ጭኗ አካባቢ የረገጣት ህመም ሲበረታባት ሌሌች ጥበቃዎች ጣልቃ ገብተው ወደ ግቢ እንድትገባ ይፈቅዱላታል። ዶርም ገብታ መታወቂያዋን ይዛ ክስ ለመመስረት ዲሲፕሊን ቢሮ ሄዳ ሰኞ ትመለስ ዘንድ ነግረዋት ከቢሮ ስትወጣ ራሷን ሳተች።አሁን ላይ ማህፀኗ አካባቢ የተቋጠረ ደም እንዳለ እንደተነገራትና ህመሙ ምናልባትም ቀዶ ህክምና ሊያስፈልገው እንደሚችል በእጅ ስልኳ መረጃ የሰጡን ከጎኗ ያሉ ጓደኞቿ ነግረውናል። ጓደኞቿ በተጨማሪ እንደነገሩን ከሆነ ተማሪዋ ሽንት ለመሽናትና ለመንቀሳቀስ እጅጉን እየተቸገረች እንደሆነ ገልፀው ዩንቨርሲቲው ጉዳዩን አለባብሶ ለማለፍ እንዳይሞክር ድምፅ እንሆንላት ዘንድ ጠይቀዋል።]


ይህን ጉዳይ በተመለከተ የእንጅባራ ዩንቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ፕሬዘዳንት የሰጠን ምላሽ

ዩንቨርሲቲው መረጃው የደረሰው ቢሆንም ጉዳዩ በመጣራት ሂደት ላይ እንዳለ ፕሬዝዳንቱ ነግረውናል።አሁን ላይ ተማሪዋ የህክምና እርዳታ እያገኘች እንዳለ ገልፀው የህመሟን ምክንያት ማለትም ተማሪዋ ያቀረበችውን ምክንያት በተጨማሪም ራሷን ስታ በምትወድቅበት ጊዜ የመታት ነገር መኖር አለመኖሩን የባለሙያ ማረጋገጫ እንደሚያስፈልግና እንደ ፀጥታም መጠየቅ ያለባቸው ነገሮች በመኖራቸው ጉዳዩን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እያጣሩ እንደሚገኙና በሚናፈሱ ወሬዎች ላይ ብቻ ተመስርቶ የግል አስተያየት መስጠት እንደማይገባ ገልፀውልናል።


፨የተማሪ ኤደን ገብሩን ጉዳይ በተመለከተ የሚኖሩ መረጃዎችን ይዘን እንመለሳለን።


፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
5.6K viewsMuJa. M, 11:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 14:06:30
5.3K viewsMuJa. M, 11:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 14:05:46
ማጣቀሻ
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው ተማሪዎች ያወጡትን ኖት, ጥያቄ እና ሌሎች አጋዥ መፅሀፎችን በ PDF መሸጥ እና መግዛት የሚያስችላቸው ድህረገፅ ተከፈተ።

ለአጠቃቀም በጣም ምቹ የሆነው ማጣቀሻ ሻጮች ኖት አውጥተው ፈተና ሲያልቅ ከመጣል ይልቅ ወደ PDF ለውጠው ማጣቀሻ ላይ Upload በማድረግ ሌሎች ተማሪዎች በገዙ ቁጥር ገቢ የሚያገኙበት ሲሆን ገዢዎች ደግሞ ጊዜ ሳያጠፍ የቀደምት(senior) እና የእኩያ(fellow) ተማሪዎችን ኖቶች እና ሌሎች አጋዥ መርጃዎችን ገዝተው በማንበብ ማንኛውንም ጽንሰ-ሐሳብ በቀላሉ መረዳት እንዲችሉ እና ለፈተና ብቁ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል።

በተጨማሪም ማጣቀሻን በመጠቀም ተማሪዎች በ አሳይመንታቸው ፣ ፕሮጀክታቸው... ላይ ፈጣን እገዛ ማግኘት ይችላሉ።


https://mataqesha.com
4.4K viewsMuJa. M, 11:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 14:05:39
United Travel and Educational Consultancy:
100 GARANTED Outstanding opportunity for JOB seekers. In

CANADA
ROMANIA
turkey

%garanted work process

Call right away, register, and fly to work and settle abroad

Contact: United Travel and Education Consultancy.
Contact us

+251936464527
+251928970548

   Telegram
@Unconsultancy
@tesfartma91
untravelconsultancy7@gmal.com

www.unitedconsultancy.com

Address

Addis Ababa
Infront of Getfam, Tigat Business Center 4th floor Office No 2l F3_23

Hawassa
Piyasa London Buliding 4th floor

ህልሞን እናሳካለን በታማኝነት እናገለግሎታለን።
4.3K viewsMuJa. M, 11:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 11:07:01
#የትምህርትና_ስልጠና_ባለሥልጣን

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በ2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን መረጃ አሟልተው የላኩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ዝርዝር ይፋ አድርጓል።

እስካሁን አንድ ዩኒቨርሲቲ፣ አንድ ተቋም እና 18 ኮሌጆች የተሟላ መረጃ መላካቸውን ባለሥልጣኑ ገልጿል።

(የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን የተሟላ መረጃ የላኩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ከላይ ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ።) #ETA


@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
7.5K viewsMuJa. M, 08:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 18:16:36
የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድሮችን ሊያስተናግድ ነው::

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር ተወካዮች በቀጣይ የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎችን ከ22ኛው ሳምንት ጀምሮ የሚያስተናግደውን የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ለአራተኛና ለመጨረሻ ጊዜ ዛሬ ረፋድ ላይ ተመልክተዋል።

ቀደም ባሉ ምልከታዎቻቸው የሊጉ የበላይ አካል በሜዳውና ከሜዳው ውጪ ያሉ መሻሻል የሚገባቸውን ጉዳዮች ባስቀመጠው መመሪያ መሠረት ተፈፃሚ መሆናቸውን ተዟዙሮ ከተመለከተ በኋላ ሊጉ በቀጣይ ሀዋሳ ላይ እንደሚደረግ ማረጋገጫ ሰጥቷል። በዚህም መሠረት ፕሪምየር ሊጉ የ22ኛ ሳምንት ጨዋታውን በአዳማ ከጀመረ በኋላ ከመጨረሻ ሁለት ጨዋታዎች ጀምሮ እስከ 27ኛው ሳምንት ድረስ ሀዋሳ የሊጉን ውድድር ታስተናግዳለች::

@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
13.4K viewsMuJa. M, 15:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ