Get Mystery Box with random crypto!

ATC NEWS

የሰርጥ አድራሻ: @atc_news
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 116.41K
የሰርጥ መግለጫ

#ADDIS_ABABA : ETHIOPIA
ለመልዕክት 👇🏻
@mujaabot
For Advertisement👇🏿
@atcads

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 71

2023-04-24 20:01:44
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች የፈተና ምዝገባ እስከ ሚያዝያ 20 ድረስ ብቻ እንደሚካሄድ ተገለጸ

የ2015 ት/ት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች የፈተና ምዝገባ እስከ ሚያዝያ 20/2015 ድረስ ብቻ እንደሚካሄድ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

አገልግሎቱ፤ ማንኛውም የሥም፣ የፆታ፣ የተፈጥሮ/የማህበራዊ ዘርፍ እና የፎቶ ማስተካከያ ከፈተና በፊት ስለማይደረግ እያንዳንዱ ተፈታኝና እና መዝጋቢ ትክክለኛነቱን የማጣራትና የማረጋገጥ ኃላፊነት እንዳለበት አሳስቧል።

ይህ መሆን ያለበትም ምዝገባው በበየነ መረብ በመሆኑ በትምህርት ቤት ደረጃ የተካሄደው የምዝገባ መረጃ በቀጥታ በማንም ሳይነካ ወደ ተቋሙ የመረጃ ቋት የሚገባ በመሆኑ ነው ሲል አስረድቷል።

ከሚያዚያ 20/2015 በኋላ በግለሰብ ወይም በተቋም በኩል የሚመጡ ተመዝጋቢዎችን አላስተናግድም ሲል በጥብቅ ያሳሰበው አገልግሎቱ፤ ፈተናው የሚሰጠው በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥና የመፈተኛ ጊዜን ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኋላ እንደሚገለጽ አስታውቋል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት እስካሁን የመፈተኛ ጊዜ አልተገለጸም ያለ ሲሆን፤ ተፈታኞች ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል።


፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
15.0K viewsMuJa. M, 17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 20:00:51
#Remedial Mathematics #Natural

ከላይ ያሉትን ቻፕተሮች በሙሉ የገፅ ለገፅ ቲቶርያል ቪድዮዎችን መግዛት የምትፈልጉ የናቹራል ሳይንስ ተማሪዎች #300ብር ከፍላቹህ ለአራት ወራት መጠቀም ትችላላችሁ።

መግዛት የምትፈልጉ @muedu

For Entrance
https://t.me/ATC_EUEE/11
11.7K viewsMuJa. M, 17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 20:00:37
በርካታ የመኪና ግብይት አማራጭ ያሉትን ይህን ቻናል ይቀላቀሉ፣ ይጎብኙ፣ ይገበያዩ!

http://T.me/EthioCarMarket
11.2K viewsMuJa. M, 17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 19:59:54
ልዩ የበአል ቅናሽ ለተማሪዎች

የተለያዩ አዳዲስ እና ዱባይ ዩዝድ ላፕቶፖችን በጥራትና በቅናሽ
ከ #ሄኒ_ኮምፒውተር ያገኛሉ።

ከአንድ አመት ዋስትና ጋር

ለተማሪዎች ልዩ ቅናሽ አለን።

የቴሌግራም ቻናላችን ላይ ዋጋቸውንና የላፕቶፖችን ዝርዝር መረጃ አስቀምጠናል።
ይመልከቱን
                
                 https://t.me/henicom
                 https://t.me/henicom
                
አድራሻ: አዲስአበባ፣ መገናኛ፣

: +251911903060
    
  Home of Laptops!
13.1K viewsMuJa. M, 16:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 12:29:58
#Update

ሚያዚያ 15/2015 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ የነበረው የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ምዝገባ ለአምስት ቀናት ተራዝሟል።

ምዝገባው ከመጋቢት 20/2015 ዓ.ም ጀምሮ በኦንላይን ሲከናወን መቆየቱ ይታወቃል።

የተፈታኞቹ ምዝገባ እስከ ሚያዝያ 20/2015 ዓ.ም ድረስ ብቻ እንደሚካሄድ የትምህትርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ከሚያዚያ 20/2015 ዓ.ም በኋላ በግለሰብም ሆነ በተቋም የሚመጡ ተመዝጋቢዎችን #የማያስተናግድ መሆኑን አገልግሎቱ አሳስቧል።

በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠው የ2015 ትምህርት ዘመን ፈተና የመፈተኛ ጊዜን ከምዝገባው መጠናቀቀ በኋላ የሚገለጽ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል።

፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
16.9K viewsMuJa. M, 09:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 19:22:15
የ5 አመቱን ህፃን አፍኖ በመውሰድ የ1.5 ሚሊዮን ብር ክፍያ የጠየቀው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ!


የአጋች ታጋች የወንጀል ጉዳይ ልፋትን የጠየቀ አዲስ አበባን ጨምሮ አራት ከተሞችን ያደረሰ እንደሆነ ተገልፆል፡፡

ህፃኑ በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የጠቆመ ሲሆን በህፃኑ እገታ ዋና ወንጀል ፈፃሚ የሆነው አማኑኤል ተክላይ የተባለው ግለሰብ ቤተሰባዊ ጉዳይን ምክንያት በማድረግ  የ5 ዓመቱን ህፃን ናታኒ ጎይቶምን ሚያዚያ 3 ቀን 2015 ዓ/ም አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው አለም ባንክ ስድስት ጎጆ ከሚባል አካባቢ ከሚገኘው የህፃኑ ወላጆች ቤት አፍኖ በመውሰድ 1.5 ሚሊዮን ብር ካልተከፈለው ልጁን እንደሚገድለው ይዝታል፡፡

የህፃኑ መታገት መረጃው የደረሰው አዲስ አበባ ፖሊስ ከብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት እንዲሁም ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ጋር በጥምረት ባከናወነው ብርቱ የምርመራና የክትትል ተግባር ሦስት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ህፃኑን ለወላጆቹ ማስረከቡን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ወንጀል ፈፃሚዎቹ ከአርባ ምንጭ ቀጥሎ አዋሳ ከዚያም አዳማ ከተማ  እየተዘዋወሩ አድራሻቸውን ለማጥፋት ጥረት ቢያደርጉም የፖሊስ የክትትልና የምርመራ አባላት 24 ሰዓት ባደረጉት ጠንካራ ክትትል እና ምርመራ ሚያዝያ 14 ቀን 2015 ዓ/ም ቢሾፍቱ ከተማ ሸማኔ ሜዳ አካባቢ ህፃን ናታኒም ጎይቶም ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስበት ማግኘታቸው ታውቋል፡፡ ተጠርጣሪው አማኑኤል ተክላይ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ለፖሊስ በሰጠው ቃል የህፃኑ አክስት ገንዘብ ስለወሰደችበት ብሩን ለማስመለስ ወንጀሉን እንደፈፀመ አስረድቶ ባልጠቀቀው ሁኔታ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ተናግሯል።

@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
8.0K viewsMuJa. M, 16:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 19:15:44
ልዩ የበአል ቅናሽ ለተማሪዎች

የተለያዩ አዳዲስ እና ዱባይ ዩዝድ ላፕቶፖችን በጥራትና በቅናሽ
ከ #ሄኒ_ኮምፒውተር ያገኛሉ።

ከአንድ አመት ዋስትና ጋር

ለተማሪዎች ልዩ ቅናሽ አለን።

የቴሌግራም ቻናላችን ላይ ዋጋቸውንና የላፕቶፖችን ዝርዝር መረጃ አስቀምጠናል።
ይመልከቱን
                
                 https://t.me/henicom
                 https://t.me/henicom
                
አድራሻ: አዲስአበባ፣ መገናኛ፣

: +251911903060
    
  Home of Laptops!
7.7K viewsMuJa. M, 16:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 19:15:27
በርካታ የመኪና ግብይት አማራጭ ያሉትን ይህን ቻናል ይቀላቀሉ፣ ይጎብኙ፣ ይገበያዩ!

http://T.me/EthioCarMarket
6.9K viewsMuJa. M, 16:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 14:57:53
#JimmaUniversity

ጅማ ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዘኛ ቋንቋ መመዘኛ ፈተና (IELTS Test) በተቋሙ ዋና ግቢ ለመስጠት ከብሪቲሽ ካውንስል ጋር ተስማምቷል፡፡

ፈተናው በጅማ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ መሰጠቱ የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ እንዲሁም በምዕራብ የሀገሪቱ ክፍል የሚኖሩና ፈተናውን ለመውሰድ ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል፡፡

ምዝገባ በማድረግ ነጻ የመዘጋጃ የኦንላይን ኮርሶችን፣ ነጻ የሙከራ ፈተናዎች፣ በየትኛውም ቦታ ለመዘጋጀት የሚያስችል የሞባይል መተግበሪያ እንዲሁም ቪዲዮዎችና ተጨማሪ ግብዓቶችን ማግኘት ይችላሉ፡፡

በኦንላይን ለመመዝገብ፦

ieltsregistration.britishcouncil.org

ፈተናው የሚሰጠው፦ ሰኔ 17/2015 ዓ.ም

ለበለጠ መረጃ፦

➧ 0471112202
➧ ero@ju.edu.et
➧ www.ju.edu.et

@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
10.7K viewsMuJa. M, 11:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 13:37:00 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመምህራን ማኅበር በሥሩ ከሚገኙት አባላት መካከል የ29,500 አባላቱ የመኖሪያ ቤት ችግር እንዲፈታለት ከንቲባ አዳነች አቤቤን በደብዳቤ ጠይቋል።
የማኅበሩ ፕሬዚዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ ለሪፖርተር ቃለ ምልልስ ሰጥተው ነበር። በዚህ ቃለምልልስ ምን አሉ ?
- ማህበሩ ከሁለት ሳምንት በፊት ለከንቲባዋ በጻፈው ደብዳቤ፣ በአስተዳደሩ ሥር የሚገኙ መምህራን የቤት ጥያቄ እንዲፈታ ጠይቋል፡፡
- የመምህራን ጥያቄ እየበረታ በመምጣቱ ከንቲባዋ ከመምህራን ጋር በ2013 ዓ.ም. በነበራቸው ስብሳሰባ፣ መምህራን በማኅበር ተደራጅተው ቤት እንዲገነቡ እንደሚደረግ ቢገለጽም፣ እስካሁን ምንም ዓይነት ተስፋ ሰጪ ነገር እየታየ አይደለም።
- ለከንቲባዋ በተፃፈው ደብዳቤ ለመምህራን የኑሮ ውድነትን የሚያረግቡ ድጎማዎች እንዲደረጉ፣ ከንቲባዋ በመድረክ ላይ የገቡት ቃል ወደ ታች ወርዶ እንዲፈጸምና በከተማ አስተዳደሩ በተጀመሩ ልማቶች የመምህራን ጥያቄዎች እልባት እንዲያገኙ ተጠይቋል።
- የመምህራን የደመወዝ ጥያቄ የከተማ አስተዳደሩ የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት ከተቻለ በልዩ ትኩረት በከተማው ደረጃ ውሳኔ ሰጥቶበት እንዲፈታ፣ ካልሆነም ደግሞ የሚመለከተው የፌዴራል ተቋም ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት እልባት መስጠት እንዲቻል እንዲደረግ ጥሪ ቀርቧል።
- የኑሮ ውድነት ማረጋጊያ ድጎማ 3,000 ብር የሚሰጥ ቢሆንም፣ ገንዘቡ ከችግሩ ጋር አብሮ የማይሄድ በመሆኑ ቢያንስ በእጥፍ እንዲያድግ መምህራኑ ይፈልጋሉ።
በተጨማሪ ለከንቲባዋ በተፃፈው ደብዳቤ ....
ለመምህራን ሁለተኛ መ/ ቤታቸው የሆነው የመኖሪያ ቤት ጥያቄ፣ ግንቦት 2013 ዓ.ም. መምህራንን ባወያዩበት ወቅት መምህራን በማኅበር ተደራጅተው ቤት እንዲገነቡ እንደሚደረግ የተገለጸ ቢሆንም፣ ነገር ግን እስካሁን በተፈለገው ርቀት ወደ ሥራ አለመገባቱን ያትታል፡፡ 
በዚህ የተነሳ ባለፉት ወራት ምንም ዓይነት ለውጥ አለመኖሩ መምህራንን ተጠቃሚ ከማድረግ ይልቅ፣ ጉዳዩን በተቃራኒ በጥርጣሬ እንዲያዩት አነሳሽ ምክንያት ከመሆኑም በላይ ተስፋ አስቆራጭነቱ እየሰፋ የመጣ ስለመሆኑ ይገልጻል።
ይህ ጉዳይ መምህራን ቃል የገቡልንን አልተገበሩልንም (አላስተገበሩልንም) የሚል ስሜት ፈጥሮ የመምህራንን ሞራል ያላሸቀ ፣ ቤት ባላቸውና በሌላቸው መምህራን መካከል የፍትሐዊነት ጥያቄ ያስነሳ መሆኑም በደብዳቤው ተመላክቷል፡፡
መምህራን የሚያገኙት የደመወዝ መጠንና በአሁኑ ወቅት ያለው ፦ የቤት ኪራይ ዋጋ፣ በተጨማሪም የኑሮ ውድነት መምህራንን ተረጋግተው እንዳያስተምሩ ጫና እየፈጠረ በመሆኑ ከንቲባዋ ለመምህራኑ በገቡት ቃል መሠረት ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠት፣ የመምህራን የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ " አጥብቀን እንጠይቃለን " ብሏል።
በአሁኑ ወቅት ያለውን የኑሮ ውድነት መምህራኑ ከሚያገኙት ደመወዝና የኑሮ መደጎሚያ ጋር ተቋቁሞ መኖር ከባድ መሆኑን የሚያስረዳው ደብዳቤው፣ የከተማ አስተዳደሩ ከዚህ ቀደም ባደረገው የኑሮ መደጎሚያ ላይ ወቅቱን የሚመጥን ማሻሻያ እንዲያደርግ ጠይቋል፡፡
ለከንቲባዋ የተላከው ደብዳቤ በመምህርነት ሙያ ላይ 40 ዓመትና 18 ዓመት ያገለገሉ መምህራን በአንድ ቋት ውስጥ አንድ ዓይነት ደመወዝ ስኬል መካተታቸውን ጠቅሶ፣ ይህም አግባብነት የሌለው በመሆኑ እንደ መንግሥት አስቸኳይ እልባት ያስፈልገዋል ብሏል፡፡
ግንባታው የተጀመረው የመምህራን ሆስፒታልና ሁለገብ ማዕከል ግንባታው እንዲፋጠን፣ መንግሥት በገንዘብም ሆነ በቁሳቁስ ድጋፍ እንዲያደርግና የቴክኒክና ሙያ ማሠልጠኛ መምህራን የሥራ ላይ ዋስትና የሌላቸው በመሆኑ፣ ከሥራው ባህሪ አንፃር የሥራ ላይ ዋስትና/ኢንሹራንስ እንዲፈቀድላቸው በሚል አክሎ ጠይቋል፡፡

(ሪፖርተር ጋዜጣ)
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
11.3K viewsMuJa. M, 10:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ