#Tigray ከዓመታት በኃላ በትግራይ ያሉ #ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ ምዝገበ እየተካሄደ ይገኛል። የትግራይ ትምህርት ቢሮ ለዓመታት በኮቪድ-19 እና በጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የቆየውን መደበኛ ትምህርት ለማስጀመር ከሚያዚያ 18 ጀምሮ ምዝገባ እንደሚከናወን እና ሚያዚያ 23 ትምህርት እንደሚጀመር ማሳወቁ የሚዘነጋ አይደለም። ተማሪዎች ያለፋቸውን ጊዜ ለማካካስ በሳምንት 3 የትምህርት ፕሮግራሞች የነበሩትን ወደ 5 እና 6 በመቀየር አንድ ሴሚስተር የሚጨርሰውን ጊዜ ለማሳጠር እንደሚሰራ መነገሩም ይታወሳል። በትግራይ ጦርነት ምክንያት ክፉኛ ከተጎዱት መካከል #ተማሪዎች ዋነኛዎቹ ሲሆኑ ተማሪዎች ለበርካታ ወራት ከትምህርት ርቀው ይገኛሉ። እንደ ህፃናት አድን ድርጅት (Save the Children) መረጃ በትግራይ 2.3 ሚሊዮን ሕጻናት ወደ ትምህርት ገበታቸው አልተመለሱም። ፎቶ ፦ ድምፂ ወያነ @atc_news @atc_news @atc_news @atc_news 11.4K viewsMuJa. M, 16:17