Get Mystery Box with random crypto!

Amhara Sport

የቴሌግራም ቻናል አርማ amharasport — Amhara Sport A
የቴሌግራም ቻናል አርማ amharasport — Amhara Sport
የሰርጥ አድራሻ: @amharasport
ምድቦች: ስፖርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.60K
የሰርጥ መግለጫ

የሚዲያ ሽፋን የተነፈገውን የኢትዮጵያ ስፖርት ለማሳደግ ከሰፈር እስከ ጠፈር በትኩረት እንዘግባለን !!

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 22

2022-08-10 22:33:45
አማካዩ ሱራፌል ዳኛቸው ከዋልያዎቹ ስብስብ ውጪ ሆኗል !!

በአልጄሪያ አስተናጋጅነት በሚከናወነው የቻን ውድድር ላይ ለመሳተፍ የማጣሪያ ጨዋታዎች እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የደቡብ ሱዳን አቻውን በደርሶ መልስ ውጤት ረቶ በመጨረሻው ዙር ከሩዋንዳ ጋር ለመፋለም ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ ማስተላለፉ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከደቂቃዎች በፊት ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት ቡድኑ በዛሬው ዕለት ተሰባስቦ የጂምናዚየም ልምምድ ማድረግ የጀመረ ሲሆን ወሳኝ አማካዩ ሱራፌል ዳኛቸውን ግን በጉዳት ምክንያት ከስብስቡ ውጪ አድርጓል። በምትኩም የሀዋሳ ከተማው ወንድማገኝ ኃይሉ ጥሪ እንደተደረገለት ተገልጿል።

ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ገፃችን ይቀላቀሉ

https://t.me/AmharaSport
https://t.me/AmharaSport

ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ

@Amharasport
6.7K viewsedited  19:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 18:39:37
የጣና ሞገዶቹ በያዝነው ሳምንት መጨረሻ ዝግጅት ይጀምራሉ !!

በአሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ እየተመሩ በዝውውር መስኮቱ በንቃት በመሳተፍ በርከት ያሉ ተጫዋቾችን ማስፈረም የቻሉት ባህርዳር ከተማዎች የቅድመ ዉድድር ዝግጅታቸውን በያዝነዉ ሳምንት መጨረሻ ቅዳሜ ነሐሴ 7 እንደሚጀምሩ ታውቋል።

ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ገፃችን ይቀላቀሉ

https://t.me/AmharaSport
https://t.me/AmharaSport

ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ

@Amharasport
5.7K viewsedited  15:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 18:22:27
ፋሲል ከነማ የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ የቅድመ ማጣሪያ ተጋጣሚውን አውቋል።

ቡድኑ ይህንን ዙር የሚያልፍ ከሆነ በሁለተኛ ዙር ማጣሪያ ከሴፋክሲን (ቱኒዚያ) ጋር የሚፋለም ይሆናል።

ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ገፃችን ይቀላቀሉ

https://t.me/AmharaSport
https://t.me/AmharaSport

ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ

@Amharasport
5.3K viewsedited  15:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 09:28:11
አፄዎቹ በዛሬዉ ዕለት በይፋ የቅድመ ዉድድር ዝግጅታቸውን የሚጀምሩ ይሆናል !!

በነሐሴ ወር መጨረሻ ለሚጠብቃቸው የአፍሪካ ኮንፌደሬሽን ካፕ እና በመስከረም ወር ለሚጀምረው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዉድድር የቅድመ ዉድድር ዝግጅታቸውን በዛሬዉ ዕለት ነሐሴ 2 በባህርዳር ከተማ የሚጀምሩ ይሆናል።

በተጨማሪም አፄዎቹ የኮንፌዴሬሽን ካፕ ተጋጣሚያቸውን በነገዉ ዕለት አመሻሽ የሚያዎቁም ይሆናል።

ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ገፃችን ይቀላቀሉ

https://t.me/AmharaSport
https://t.me/AmharaSport

ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ

@Amharasport
5.6K viewsedited  06:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 23:41:49
አሰልጣኝ ዉበቱ አባተ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል !!

በአፍሪካ ሀገራት ቻምፒዮንሺፕ ውድድር የመጨረሻ ዙር ማጣርያ ሩዋንዳን የሚገጥመው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለሚያደርገው ዝግጅት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አደረጉ።

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ ሲያደርጉ ከደቡብ ሱዳኑ ጨዋታ ስብስባቸው ዉስጥ የአንድም ተጫዋች ለውጥ አላደረጉም።

ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ገፃችን ይቀላቀሉ

https://t.me/AmharaSport
https://t.me/AmharaSport

ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ

@Amharasport
5.8K viewsedited  20:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 17:44:53
የአማራ ክልል እግር ኳስ ክለቦች ሻምፒዮና ውድድር በኬሚሴ ከተማ እየተካሄደ ነው !!

33 ክለቦች የሚሳተፉበት የአማራ ክልል እግር ኳስ ክለቦች ሻምፒዮና ውድድር ከትናንት ጀምሮ በኬሚሴ ከተማ በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ሲሆን ውድድሩ ከወዲሁ አጓጊ ሁኗል።

በቻምፒዮናው የተሻለ ውጤት የሚያስመዘግቡ ክለቦች በ2015 ዓ.ም በአማራ ሊግ የሚሳተፉበትን ዕድል ያገኛሉ።

ቻምፒዮናው ትናንት ሲጀመር በመክፈቻ ጨዋታ ቢፍቱ ወሎ ከለጋምቦ ከተማ ጋር የተገናኙበት ጨዋታ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቅ ፣ ራያ ቆቦ አበርገሌን 3ለ 1 በሆነ ውጤት ረቷል። በሌላ ጨዋታ ሀይቅ ከተማ ከ እንጅባራ ያደረጉት ጨዋታ በሀይቅ የ 2ለ1 አሸናፊነት ተጠናቋል።

ጃዊ ከተማ ከአራዳ ክፍለ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ ከፍተኛ ፉክክር ተስተናግዶበት በጃዊ 3ለ 2 አሸናፊነት ሲጠናቀቅ
አማኑኤል ከተማ ከጠባሴ ክፍለ ከተማ አንድ እኩል በሆነ ውጤት ነጥብ ተጋርተዋል።በሌላ ጨዋታ መኮይ ባህርዳር ዩንቨርስቲን 2ለ0 ረቷል ።

ዛሬ በተካሄዱ ጨዋታዎች መርጦለማሪያም 4ለ1 በሆነ ውጤት ገበዘማሪያምን ሲረቱ ፣ ሉማሜ አዋበል ባቲ ከነማን 2ለ1 ረቷል።ኮምቦልቻ ስ/አካዳሚ 3ለ 2 ቱሉ አውልያን ሲያሸንፍ ፣ ቡልጋ ከተማ ጠንካራውን እስቴ ወረዳ 1ለ0 አሸንፏል።

ወግዲ ወረዳ 1ለ 0 አምደወርቅን ሲያሸንፍ ገነት አቦ ከተማ ከጣቁሳ ያደረጉት ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።


@AmharaSport
1.3K viewsedited  14:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 17:29:08
አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ እና መከላከያ መለያየታቸው ተረጋግጧል !!

ያለፉትን ሁለት አመታት ያህል ከመከላከያ ጋር ጥሩ የሚባል አመትን ማሳለፍ የቻሉት አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ከክለቡ ጋር በስምምነት መለያየታቸው ተረጋግጧል።

አሰልጣኝ ዮሐንስ በ2013 የዉድድር አመት መከላከያን ከከፍተኛ ሊግ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ካሳደጉ በኋላ በያዝነዉ አመት ደግሞ አዲስ አዳጊዉ ክለባቸዉ በሊጉ እንዲቆይ ማድረግ ችለዉ ነበር።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ተሰናባቹን አሰልጣኝ በመተካት አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝን ወይም አሰልጣኝ ገ/መድህን ሀይሌን ወደ ጦሩ ቤት ለማምጣት ንግግር ላይ ስለመሆናቸዉ ከክለቡ አካባቢ የሚወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ።

@Amharasport
1.3K viewsedited  14:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 16:42:53
ኢትዮጵያ ቡና የመስመር ተጫዋቹን መስፍን ታፈሰን አስፈርሟል !!

የሀዋሳ ከተማዉ የመስመር ተጫዋች መስፍን ታፈሰ በዛሬዉ ዕለት ሁለት አመት በሚቆይ የኮንትራት ዉል ቡናማዎቹን መቀላቀሉን ክለቡ ይፋ አድርጓል።

ከሀዋሳ ታዳጊ ቡድን ጀምሮ ያለፉትን ሶስት አመታት በሀዋሳ ከተማ ዋናዉ ቡድን ጥሩ ግልጋሎት መስጠት የቻለዉ ተጫዋቹ ወሳኙን አጥቂያቸውን ወደ ደቡብ አፍሪካ ለሸኙት ቡናማዎች ትልቅ ዝዉዉር እንደሆነ ዕርግጥ ሆኗል።

ኢትዮጵያ ቡና ኃይለሚካኤል አደፍርስ እና አብዱልአዚዝ ቶፊቅን እና መስፍን ታፈሰን ማስፈረሙ ሲረጋገጥ በቀጣይ ቀናትም ተጨማሪ ተጫዋቾች ወደ ክለቡ እንደሚቀላቀሉ ይጠበቃል።

@Amharasport
1.6K viewsedited  13:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 12:47:43
ሞጣ ከነማ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈ

በኢትዮጵያ የክለቦች ሻምፒዮና ሞጣ ከነማ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል።

በሀዋሳ ከተማ በመካሄድ ላይ ባለው የክልል ክለቦች ቻምፒዮና የምድቡን ሶስተኛ ጨዋታውን ትናንት ከዶዮገና ከተማ ጋር የተጫወተው ሞጣ ከነማ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የጥሎ ማለፉን ምድብ ተቀላቅሏል።

ሊንኩን ተጭነው የቴሌግራም ገፃችን ይቀላቀሉ።
━━━━⊱✿⊰━━━━

https://t.me/AmharaSport
https://t.me/AmharaSport
https://t.me/AmharaSport


@AmharaSport
2.4K views09:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 10:21:59
ፋሲል ከነማ እና ድሬዳዋ ከተማ ቅጣት ተጥሎባቸዋል !!

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት በመመርመር የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

ድሬዳዋ እግር ኳስ ክለብ ክለቡ ከ ባህርዳር ጋር በነበረው የ28ኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ ግጥሚያው ከተጠናቀቀ በኋላ የክለቡ ደጋፊዎችና የቡድን አመራሮች አፀያፊ ስደብ ስለመሳደባቸው ሪፖርት የቀረበበት ሲሆን የክለቡ ደጋፊዎችና የቡድን አመራሮች በዕለቱ ባጠፉት ጥፋት ክለቡ ብር 75,000 /ሰባ አምስት ሺህ/ እንዲከፍል ተወስኗል ።

ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ክለቡ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር በነበረው የ30ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ ከ68ኛው ደቂቃ ጀምሮ ስፖርታዊ ጨዋነትን ያልተከተለ ድጋፍ ስለመስጠታቸው እና ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ የጥበቃ ሃይሎች ሊቆጣጠሩት ባልቻለ ሁኔታ ወደ መጫወቻ ሜዳ ጥሰው ስለመግባታቸውና ስለማወካቸው እንዲሁም ለሜዳሊያ አስጣጥ ስነስርዓት አፈጻጸም እንቅፋት ስለመሆናቸው ሪፖርት ቀርቦበታል ።

በዚህም የክለቡ ደጋፊዎች በዕለቱ ባጠፉት ጥፋትና ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ጥፋት ከተቀጡት ቅጣት ሊታረሙ ባለመቻላቸው ክለቡ ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ/ እንዲከፍልና በሜዳቸው የሚጫወቱትን ቀጣይ ሁለት ጨዋታዎች ያለደጋፊ በዝግ ስታዲየም እንዲያደርጉ ወስኗል ።

@Amharasport
2.9K viewsedited  07:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ