Get Mystery Box with random crypto!

Amhara Sport

የቴሌግራም ቻናል አርማ amharasport — Amhara Sport A
የቴሌግራም ቻናል አርማ amharasport — Amhara Sport
የሰርጥ አድራሻ: @amharasport
ምድቦች: ስፖርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.60K
የሰርጥ መግለጫ

የሚዲያ ሽፋን የተነፈገውን የኢትዮጵያ ስፖርት ለማሳደግ ከሰፈር እስከ ጠፈር በትኩረት እንዘግባለን !!

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 20

2022-09-08 13:25:18
የጣና ሞገዶቹ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በመከወን ላይ ይገኛሉ !

በአሰልጣኝ አብሀም መብራቱ እየተመሩ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸዉን በባህርዳር ስታዲየም እየከወኑ የሚገኙት የጣና ሞገዶቹ ከአምስት ቀናት የበዓል ዕረፍት በኋላ ዝግጅታቸውን እንደሚቀጥሉ ሲገለፅ ከዚህ ጋር ተያይዞም በቀን ሁለት ጊዜ ልምምዱን ሲከዉን የቆየዉ ቡድኑ በቀጣዩ አመት ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ እንደሚቀርብ ይጠበቃል።

@Amharasport
3.9K views10:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 11:18:44
የአማራ ባንክ ጣና ዋንጫ ውድድር ከፊታችን መስከረም ስድስት ጀምሮ እንደሚደረግ ተገልጿል !!

አማራ ባንክ ከባህርዳር ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባባር ለመጀመሪያ ጊዜ በሚያዘጋጀዉ ዉድድር ዙሪያ በተሰጠ መግለጫ ዉድድሩ መስከረም 6 ጀምሮ እስከ 14 የሚቆይ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም አማራ ባንክ የታይትል ስፖንሰር በመሆኑ ምክንያት ለውድድሩ አምስት ሚሊዮን ብር እንደሚከፍልም ተገልጿል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ውድድሩ ከተቻለ በስድስት ወይም በአራት የሀገር ዉስጥ እና ሁለት የዉጭ ሀገር ክለቦች የሚደረግ ሲሆን ፤ ተሳታፊ ክለቦቸም:-

1, ባህርዳር ከተማ
2, ድሬዳዋ ከተማ
3, መቻል
4, ኢትዮጵያ መድን ሲሆኑ እንዲሁም ሁለት ተጨማሪ ክለቦች ከዩጋንዳ ሞደርን ጋዳፊ እና ሚሳተፉ ይሆናል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ፋሲል ከነማ ባለባቸዉ የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ እና የኮንፌዴሬሽን ካፕ የመልስ ጨዋታ ምክንያት በውድድሩ ላይ የመሳተፋቸዉ ነገር እስከ አሁን ድረስ የተረጋገጠ አለመሆኑም ተገልጿል።

@Amharasport
3.9K views08:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 17:43:00
የጣና ካፕ ውድድር በስድስት ክለቦች መካከል ከመስከረም 6 ጀምሮ እንደሚከናወን ታውቋል !!

ከመስከረም ስድስት ጀምሮ በአራት የሀገር ዉስጥ እና ሁለት የዉጭ ሀገር ክለቦች መካከል ለመጀመሪያ ጊዜ በሚከናወነዉ የጣና ካፕ የእግርኳስ ዉድድርን አማራ ባንክ የስያሜ መብት ባለቤት መሆኑ ሲገለፅ ከዚህ በተጨማሪም ዉድድሩን በተመለከተ የሚኖሩትን ዝርዝር ጉዳይች በተመለከተ ባንኩ ጳጉሜ ሶስት በዋና መስሪያ ቤቱ መግለጫ  እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

soccer Ethiopia

@Amharasport
1.7K viewsedited  14:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 18:01:44
ተጠናቀቀ !!!!!

ሩዋንዳ 0-1 ኢትዮጵያ

(22' ዳዋ ሆቴሳ)

ኢትዮጵያ በአልጄርያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ሀገራት ቻምፒዮንሺፕ (ቻን) ውድድር ማለፋን አረጋገጠች።

በመጨረሻው ዙር ማጣርያ ሩዋንዳን የገጠመው ብሔራዊ ቡድናችን ከሜዳው ውጪ ባሳካው ድል በድምር ውጤት 1-0 አሸንፎ የቻን ማጣርያ ጉዞውን ምንም ሽንፈት እና ጎል ሳያስተናግድ በድል አጠናቋል።

እንኳን ደስ አለን !

@Amharasport
2.0K views15:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 16:53:51
እረፍት | ሩዋንዳ 0 - 1 ኢትዮጵያ

                          ዳዋ ሆቴሳ

@Amharasport
2.4K views13:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 15:12:19
በቻን የመጨረሻ ዙር ማጣርያ የመልስ ጨዋታ ሩዋንዳን የሚገጥመው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰላለፍ

ድል ለኢትዮጵያ !

@Amharasport
2.8K views12:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 21:15:16
አቡበከር ናስር ሁለተኛ ግቡን አስቆጥሯል !

የዋልያዎቹ እና የማሜሎዲ ሰንዳውንሱ የፊት መስመር አጥቂ አቡበከር ናስር ሁለተኛ ግቡን ለሰንዳውንስ ማስቆጠር ችሏል።

ቡድኑ ሰንዳውንስ ከሱፐር ሱፖርት ዩናይትድ ጋር ባደረጉት ጨዋታ የማሸነፊያዋን ሁለተኛ ግብ ከመረብ አሳርፏል ።

@Amharasport
3.3K viewsedited  18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 12:14:50
የአማራ ክልል የወከላቸዉ የተከበሩ አቶ መላኩ ፈንታ 27 ድምፅን ብቻ ማግኘት ችለዋል። በተቃራኒው ከኦሮሚያ ክልል የተወከሉት እና ነባሩ ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ በ94 ድምፅ አሸናፊ ሲሆኑ፤ ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የተወከሉት ኢንጅነር ቶኪቻ አለማየሁ 17 ድምፅ ማግኘት ችለዋል።

ዉጤቱን እንዴት ተመልክታችሁት ?

@Amharasport
4.1K views09:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 11:54:57
#ሰበር_ዜና

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን ለቀጣዮቹ አራት ዓመታት ለመምራት በአብላጫ ድምፅ አቶ ኢሳያስ ጅራ መመረጣቸውን ጉባኤ ይፋ አድርጓል ።

አቶ ኢሳያስ ጅራ ለሁለተኛ የስራ ዘመን ፌዴሬሽኑን ለመምራት በሀላፊነት ተመርጠዋል ።

አቶ ኢሳያስ 94
አቶ መላኩ 27
አቶ ቶኪቻ 17

Amhara Sport
3.9K views08:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 11:27:33
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የምርጫ ጠቅላላ ጉባኤ በመካሄድ ላይ ይገኛል !

የባሕል እና ስፖርት ሚንስቴሩ አቶ ቀጀላ መርዳሳ ፣ የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት ፣ የፊፋ እና ካፍ ታዛቢዎች ፣ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ፣ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት የተገኙበትን ጉባኤ ሚኒስትሩ አቶ ቀጀላ በንግግር ከከፈቱ በኋላ አጀንዳ ፀድቆ እንዲሁም ቃለ ጉባኤ የሚይዙ ግለሰቦች ተመርጠው በአሁኑ ሰዓት የ2014 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት መቅረብ ጀምሯል።

ዝርዝር መረጃዎችን እየተከታተልን የምናደርስ ይሆናል

Photo Tikvahsport

@Amharasport
4.2K views08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ