Get Mystery Box with random crypto!

Amhara Sport

የቴሌግራም ቻናል አርማ amharasport — Amhara Sport A
የቴሌግራም ቻናል አርማ amharasport — Amhara Sport
የሰርጥ አድራሻ: @amharasport
ምድቦች: ስፖርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.60K
የሰርጥ መግለጫ

የሚዲያ ሽፋን የተነፈገውን የኢትዮጵያ ስፖርት ለማሳደግ ከሰፈር እስከ ጠፈር በትኩረት እንዘግባለን !!

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 21

2022-08-26 18:04:28
ዋልያው አቻ ተለያይቷል !

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለቻን አፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ባደረገው የመጨረሻ የማጣርያ ጨዋታ ያለ ምንም ግብ በአቻ ውጤት ተለያይቷል ።

ዋልያዎቹ የመልስ ጨዋታቸውን በቀጣይ ሳምንት ነሐሴ 29 በሩዋንዳ የሚያደርጉ ይሆናል ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሩዋንዳ ጋር የሚያደርገውን የደርሶ መልስ ጨዋታ ካሸነፈ ለቻን የአፍሪካ ዋንጫ ማለፉን ያረጋግጣል ።

@Amharasport
4.1K viewsedited  15:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 15:11:00
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰላለፍ !

@Amharasport
4.0K views12:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 12:48:13
ፋሲል ከነማ ጋምቢያዊ አጥቂ አስፈርሟል !

በዝውውር መስኮቱ በርከት ያሉ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸዉ መቀላቀል ችለዉ የነበሩት ፋሲል ከነማዎች በተቃራኒው ከፊት መስመር አጥቂዎቻቸዉ ኦኪኪ አፎላቢ እና ሙጅብ ቃሲም ጋር ከተለያዩ በኋላ ግን እስከ ትላንት ድረስ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች ሳያስፈርሙ መቆየታቸው ይታወሳል።

አማራ ስፖርት ከደቂቃዎች በፊት ባረጋገጠው መረጃ መሰረት አፄዎቹ ጋይራ ዮፍ የተባለዉን ጋምቢያዊ አጥቂ ማስፈረማቸዉ ታውቋል። ተጫዋቹ ከዚህ ቀደም ለእስራኤሎቹ ለአል ፋሀም ኤፍሲ ፣ ራማት ሀስሻሮን እና ቢን ይሁዳ ለመሳሰሉት ክለቦች እንዲሁም ለጋምቢያዉ ዋሊዳን ክለብ መጫወት የቻለ ሲሆን በአፄዎቹ ቤትም ለአንድ አመት ለመቆየት ፊርማዉን አኑሯል።

@Amharasport
4.4K viewsedited  09:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 08:45:37
ዋልያዎቹ ጨዋታቸውን ዛሬ ያደርጋሉ !

በሀገር ውስጥ የሚጫወቱ ተጫዋቾች ብቻ በሚካፈሉበት የቻን አፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ ዋልያው የመጨረሻ ማጣርያ ጨዋታውን ከ ሩዋንዳ ጋር ዛሬ ከቀኑ 10:00 ሰዓት ያከናውናል ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በደርሶ መልስ ጨዋታ የሩዋንዳ አቻቸውን ካሸነፉ ለቻን አፍሪካ ዋንጫ ማለፋቸውን ያረጋግጣሉ ።

@Amharasport
4.0K views05:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 21:23:30
የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ለ35 ተጫዋቾች ጥሪ ተላልፏል !

ኢትዮጵያ በመጀመርያው ዙር ማጣርያ ከኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ጋር ለምታደርገዉ ጨዋታ ለ35 ተጫዋቾች ጥሪ ተደርጓል።

#ግብ_ጠባቂዎች
አላዛር ማርቆስ – ሀዋሳ ከተማ
አቡበከር ኑራ – ኢት. መድን
ፋሲል ገ/ሚካኤል – ባህር ዳር ከተማ

#ተከላካዮች
መላኩ ኤልያስ – አርባ ምንጭ ከተማ
ኃይለሚካኤል አደፍርስ – ኢትዮጵያ ቡና
ብርሃኑ በቀለ – ሀዲያ ሆሳዕና
ዓለምብርሃን ይግዛው – ፋሲል ከነማ
ረመዳን የሱፍ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
እያሱ ለገሰ – ድሬድዋ ከነማ
አሸናፊ ፊዳ – አርባ ምንጭ ከተማ
መልካሙ ቦጋለ – ወላይታ ዲቻ
አሰጋኸኝ ጴጥሮስ – ድሬድዋ ከተማ
ሚሊዮን ሰለሞን – አዳማ ከነማ
አማኑኤል ተርፉ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

#አማካዮች
አስጨናቂ ጸጋዬ – ኢትዮጵያ መድን
እንዳልካቸው መስፍን – አርባ ምንጭ
ቡቃታ ሸመና – አርባ ምንጭ
አብዱልከሪም ወርቁ – ኢትዮጵያ ቡና
ወንድማገኝ ኃይሉ – ሀዋሳ ከተማ
አበባየሁ ሀጂሶ – ወላይታ ዲቻ
ብዙአየሁ ሰይፈ – ወልቂጤ ከነማ
ከነአን ማርክነህ – መከላከያ

#አጥቂዎች
ዱሬሳ ሹቢሳ – ባህር ዳር ከተማ
ጫላ ተሺታ – ኢትዮጵያ ቡና
ናትናኤል ገ/ሚካኤል – ፋሲል ከነማ
እዮብ ዓለማየሁ – ሀዋሳ ከነማ
መሀመድ ኑር ናስር – ኢትዮጵያ ቡና
አዲሱ አቹላ – መከላከያ
ተሾመ በላቸው – መከላከያ
መስፍን ታፈሰ – ኢትዮጵያ ቡና
አቡበከር ናስር – ደቡብ አፍሪካ
አህመድ ሁሴን – አርባ ምንጭ ከተማ
ይገዙ ቦጋለ – ሲዳማ ቡና
ብሩክ በየነ – ኢትዮጵያ ቡና
ፍቃዱ ዓለሙ – ፋሲል ከነማ
4.7K viewsedited  18:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 18:05:42
የበዛብህ መለዮ ብቸኛ ግብ ዋልያዎቹን አሸናፊ አድርጋለች !

ኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከዩጋንዳ ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም አድርጓል።

ብሄራዊ ቡድናችን ጨዋታውን 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የብሄራዊ ቡድናችንን ጎል በጨዋታው መጠናቀቂያ ሰአት በዛብህ መለዮ ማስቆጠር ችሏል።

@Amharasport
6.8K viewsedited  15:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 16:55:51
የአቋም መፈተሻ ጨዋታ

እረፍት | ኢትዮጵያ 0 - 0 ዩጋንዳ

@Amharasport
6.1K views13:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 16:54:18
ባህርዳር ከተማ ግብ ጠባቂ አስፈርሟል !!

አይቮሪኮስታዊው ግብ ጠባቂ ኤሊዘር ኢራ ቴፕ የጣና ሞገዶቹን ተቀላቅሏል።

ለባህርዳር ከተማ ሶስተኛ የዉጭ ዜጋ ተጫዋች የሆነዉ ግብ ጠባቂዉ ኤሊዘር በጣና ሞገዶቹ ቤትም የሁለት አመት የስምምነት ዉል ፈርሟል።

ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ገፃችን ይቀላቀሉ

https://t.me/AmharaSport
https://t.me/AmharaSport

ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ

@Amharasport
6.0K viewsedited  13:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 21:40:56
አብዱልከሪም ንኪማ እና ባህርዳር ከተማ ተለያይተዋል !!

ከዚህ ቀደም ለቅዱስ ጊዮርጊስ መጫወት የቻለዉ እና የዉድድር አመቱን በባህርዳር ከተማ ቤት ማሳለፍ የቻለዉ ቡርኪናፋሶዋዊዉ አማካይ አብዱልከሪም ንኪማ የአንድ ዓመት ቀሪ ኮንትራት እየቀረው ነው ከባህርዳር ከተማ ጋር በስምምነት መለያየቱ ተረጋግጧል።

ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ገፃችን ይቀላቀሉ

https://t.me/AmharaSport
https://t.me/AmharaSport

ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ

@Amharasport
6.4K viewsedited  18:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 20:35:48
ዋልያዎቹ የወዳጅነት ጨዋታ ሊያደርጉ ነዉ !!

በአልጄርያ አስተናጋጅነት ለሚከናወነው የቻን ውድድር ለማለፍ የመጨረሻ የማጣርያ ጨዋታውን ከሩዋንዳ ብሔራዊ ቡድን ጋር ነሐሴ 20 እና ነሐሴ 29 የሚያከናውነው ብሔራዊ ቡድናችን ልምምዱን ዛሬ መጀመሩ የሚታወስ ሲሆን ለጨዋታዎቹ ዝግጅት እንዲረዳው ከዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን ጋር ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎችን ለማድረግ ከስምምነት ተደርሷል።

በዚህም መሰረት የመጀመርያው ጨዋታ ሐሙስ ነሐሴ 12 የሚደረግ ሲሆን ሁለተኛው ጨዋታ ደግሞ ነሐሴ 14 ይከናወናል። ሁለቱም ግጥሚያዎች አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ስታዲየም ላይ የሚደረጉም ይሆናል።

ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ገፃችን ይቀላቀሉ

https://t.me/AmharaSport
https://t.me/AmharaSport

ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ

@Amharasport
7.9K viewsedited  17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ