Get Mystery Box with random crypto!

አድማስ ሬድዮ- Admas Radio

የቴሌግራም ቻናል አርማ admasradio — አድማስ ሬድዮ- Admas Radio
የቴሌግራም ቻናል አርማ admasradio — አድማስ ሬድዮ- Admas Radio
የሰርጥ አድራሻ: @admasradio
ምድቦች: ሙዚቃ
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 1.80K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ከሰሜን አሜሪካዋ ደማቅ ከተማ አትላንታ እየተዘጋጀ በመላው ዓለም የሚተላለፈው
የ አድማስ ሬድዬ የቴሌግራም ቻናል ነው።
www.admasradio.info
melethio23@gmail.com
mike@admasradio.info

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2021-02-01 21:30:58
137 views18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-01 19:48:47
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 734 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፣ 106 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 6 ሺህ 216 የላቦራቶሪ ምርመራ 734 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 138 ሺህ 384 ደርሷል።

በሌላ በኩል የዛሬውን 106 ጨምሮ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 122 ሺህ 968 ሆኗል።

አሁን ላይ ቫይረሱ ካለባቸው 13 ሺህ 311 ሰዎች መካከል 230 ሰዎች በጽኑ ሕሙማን መከታተያ ክፍል ውስጥ ይገኛሉ።

በተጨማሪም የ10 ሰዎች ሕይወት ማለፉ መረጋገጡን ተከትሎ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 103 ደርሷል።

በአገሪቱ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊዮን 968 ሺህ 768 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

@admasradio
174 viewsedited  16:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-01 19:34:55 ዐበይት ዜናዎች

1፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ትግራይ ክልልን ለሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት ክፍት እንዲያደርግ የሚጠይቅ ዘመቻ እንደጀመረ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ ረድዔት ድርጅቶች ዕርዳታ ለማጓጓዝ ያቀረቧቸው በርካታ ጥያቄዎች ፍቃድ እንዳላገኙ የገለጠው ድርጅቱ፣ የረድዔት ሠራተኞችም ለመግባት ፍቃድ እንዳላገኙ አውስቷል፡፡ በክልሉ የሰላማዊ ሰዎች ጭፍጨፋ፣ የዘፈቀደ የከባድ መሳሪያ ድብደባ፣ ከፍርድ ውጭ ግድያ እና ዝርፊያ ስለመበራከቱ በቂ ማስረጃ አለ- ብሏል አምነስቲ፡፡

2፤ በኢትዮጵያው ትግራይ ክልል እስካሁን ትርጉም ያለው ዕርዳታ ለተረጅዎች እንዳልደረሰ የኖርዌይ ስደተኞች ካውንስል ዋና ጸሃፊ ጃን ኢግላንድ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡ ማዕከላዊ እና ምዕራባዊ ትግራይ እንዲሁም 2 የኤርትራዊያን ስደተኛ መጠለያዎች ለረድዔት ድርጅቶች እስካሁን ተደራሽ አልሆኑም፡፡ ተደራሽ የሆኑት መቀሌ እና ለአውራ ጎዳናዎች ቅርብ የሆኑ ተረጅዎች ብቻ ናቸው፡፡ ለረድዔት ድርጅቶች ፍቃድ አሰጣጡ ወጥነት የሌለው እና የተንዛዛ እንደሆነ የጠቀሱት ዋና ጸሃፊው፣ እንዲህ ያለ የተጓተተ አሠራር አይቼ አላውቅም ብለዋል፡፡ መንግሥት ሁኔታዎችን ማስተካከል ቢፈልግ ባንድ ቀን ማስተካከል ይችላል በማለትም አክለዋል፡፡ ረድዔት ድርጅቶች የችግሩን ክብደት አጉልተው አለማሳየታቸውም ውድቀት እንደሆነ አውስተዋል፡፡

3፤ በፊንላንድ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር የተመራ የአውሮፓ ኅብረት የሰብዓዊ ሁኔታ አጣሪ ቡድን ወደ ኢትዮጵያው ትግራይ ክልል እንደሚጓዝ ዩሮ ኦብዘርቨር ድረገጽ ተሰምቷል፡፡ የኅብረቱ ልዑክ በቀጣዮቹ ጥቂት ሳምንታት ወደ ሥፍራው ይጓዛል ተብሏል፡፡ በክልሉ ግጭት 3 የውጭ መንግሥታት ተሳትፈዋል ያሉት ውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ፣ ዐለማቀፉ ኅብረተሰብ በክልሉ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እንዲያጣራ ጠይቀዋል፡፡

4፤ በአማራ ክልል ከሌሎች ክልሎች የተፈናቀሉ 270 ሺህ ተፈናቃዮች እንደሚገኙ ኢትዮ ኤፍኤም ዘግቧል፡፡ ተፈናቃዮቹ በተለያዩ ማንነትን መሠረት ባዳረጉ ጥቃቶች እና ግጭቶች ምክንያት ከትግራይ፣ ከኦሮሚያ፣ ደቡብ እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የተፈናቀሉ ናቸው፡፡ አብዛኞቹ ተፈናቃዮች የተጠለሉት፣ በምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜን ወሎ እና ራያ ቆቦ ነው፡፡

5፤ ደቡብ ሱዳን ከዐለም ሀገራት በሙስና ከመጨረሻው ሁለተኛውን ደረጃ እንደያዘች የሀገራትን የሙስና ደረጃ የሚያወጣው ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ባወጣው አዲስ ሪፖርት አስታውቋል፡፡ ሱማሊያ ደሞ ሦስተኛ ደረጃ ይዛለች፡፡ ደረጃው የወጣው ከ180 ሀገራት ሲሆን፣ መለኪያው በመንግሥት ተቋማት የሚፈጸም ሙስና ነው፡፡

6፤ አልሸባብ በሞቃዲሾ ባለሥልጣናት እና ፖለቲከኞች በሚያዘወትሩት አንድ ትልቅ ሆቴል ላይ በፈጸመው ጥቃት 15 ሰዎች እንደተገደሉ የሱማሊያ ዜና ምንጮች ዘግበዋል፡፡ በአሸባሪዎቹ ጥቃት ከተገደሉት መካከል የቀድሞ መከላከያ ሚንስትር የነበሩ አንድ ጀኔራል ይገኙበታል፡፡ አሸባሪዎቹ ሆቴሉን ሰብረው የገቡት ትናንት ሌሊት ሲሆን፣ ዛሬ ከ7 ሰዓታት ተኩስ ልውውጥ በኋላ የመንግሥት ወታደሮች ሆቴሉን ተቆጣጥረዋል፡፡ ጥቃቱን ያደረሱት 4ቱ ታጣቂዎች ተገድለዋል ተብሏል፡፡

(ዋዜማ ራዲዮ)
@admasradio
167 views16:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-01 19:34:44
151 views16:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-01 19:15:39
በከተማዋ በሁለት ተጨማሪ አካባቢዎች እሳት ለማስነሳት የተደረገው ሙከራ መክሸፋን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገለፀ።

በከተማዋ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች እየታዩ ያሉ የእሳት ቃጠሎዎች በከተማው ህዝብና አመራሮች፣ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ሰራተኞች፣ የፀጥታ አካላትና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የጋራ ርብርብ የከፋ ጉዳት ሳያደርሱ መቆጣጠር መቻሉን የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል ።

የጥፋት አላማቸው ያልተሳካላቸው አካላት ሆን ብለው ህብረተሰቡን ለማሸበር እያደረጉት ያለው ተግባር እንደማይሳካ ተገልጿል ።

ህብረተሰቡ ሳይደናገጥ ተገቢውን ጥንቃቄ እያደረገ፣ ሳይዘናጋ ነቅቶ አካባቢውን በመከታተል እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መረጃ በመለዋወጥ ያለምንም ስጋት መደበኛ እንቅስቃሴውን ማስቀጠል ይኖርበታል ተብሏል ።

የጥፋት ተግባራትን በማክሸፍና ህብረተሰቡን ከአደጋ በመታደግ ላይ ያላችሁ ባለድርሻ አካላትና ነዋሪዎችን በሙሉ የከተማ አስተዳደሩ አመስግኗል

(AMN)
@admasradio
157 views16:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-01 19:08:25
አቶ ልደቱ አያሌው በምርጫ የሚሳተፉ ከሆነ ለአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባነት ሊሆን እንደሚችል

የኢትዬጵያውያን ዴሞክራያዊ ፓርቲ መስራች እና የቀድሞው ሊቀመንበር አቶ ልደቱ አያለው በዘንድሮ አመት በሚካሄደው 6ኛው ሐገራዊ ምርጫ ላይ ለአዲስ አበባ ከንቲባነት ሊወዳደሩ እንደሚችሉ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

የጤና ሁኔታቸው ምርጫው ላይ መወዳደር የሚያስችላቸው ከሆነ ለአዲስ አበባ ከንቲባነት ሊወዳደሩ እንደሚችሉ የጠቆሙት አቶ ልደቱ በሐገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄደው ምርጫ ብዙም ፋይዳ አለው ብለው እንደማያምኑ ለጣቢያችን ገልጸዋል፡፡

@admasradio
154 views16:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-01 18:28:19
መልካም ምሽት መልካም ግዜ በያላችሁበት ተመኘን


@admasradio
166 views15:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-01 17:48:07
‹‹የሸገር ድጋፍ ሰጪ አውቶቡሶች አገልግሎት ውል ይቋረጣል›› በሚል የወጣው መረጃ የተሳሳተ ነው ተባለ

የሸገር ድጋፍ ሰጪ አውቶቡሶች አገልግሎት ውል በ1 ወር ጊዜ ውስጥ ይቋረጣል በሚል በአንዳንድ መገናኛ ብዙሃን የተላለፈው መረጃ የተሳሳተ ነው ሲል በአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አረጋዊ ማሩ በተለይ ለብስረት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

መረጃው የተላለፈው ከቢሮው እውቅና ውጪ መሆኑን ውድ የከተማዋ ነዋሪዎች እንዲያውቁት ሲሉ ቢሮው አጽንኦት ሰጥቷል፡፡

በድጋፍ ሰጪ አውቶቡሶች አገልግሎት ቀጣይ ሁኔታን በተመለከተ በከተማዋ ካቢኔ ሲወሰን የሚገለፅ መሆኑን አቶ አረጋዊ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የሚታየውን የትራንስፖርት እጥረት ለመቅረፍ ፣ የትራንስፖርት ቢሮ ከአገር አቋራጭ ትራንስፖርት ማህበራት ጋር ከጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ውል ተይዞ ወደ ስራ መገባቱ ይታወሳል፡፡

(ብስራት ራዲዮ)
@admasradio
174 views14:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-01 17:48:07
በትግራይ ክልል ጉዳት የደረሰባቸውን ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ ነው

በትግራይ ክልል የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በተወሰደው እርምጃ ፣ ጉዳት የደረሰባቸውን የማምረቻ ተቋማት ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ገልጸዋል፡፡

በክልሉ የሚገኙ ጉዳት የደረሰባቸው ተቋማት ወደ ቀድሞ የማምረት ተግባራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የጉዳቱን መጠን የሚያጠና ኮሜቴ አቋቁሞ ወደ ክልሉ መላኩን ተናግረዋል፡፡

ጥናቱን መነሻ በማድረግ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለችግሩ መፍትሔ ለመስጠት ዝግጁ መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡

የማምረቻ ኢንዱስትሪዎችን ወደ ቀደመ የምርት ሂደት ለመመለስ ከሚደረገው ጥረት በተጓዳኝ በክልሉ የመሰረታዊ ሸቀጦች አቅርቦት ችግር እንዳይከሰት ሚኒስቴሩ ከተጠሪ ተቋማትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር በትኩረት እየሰራ ይገኛልም ነው ያሉት፡፡

የማምረቻ ተቋማቱን ወደ ቀድሞ የስራ እንቅስቃሴ መመለስ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር እና የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሃላፊነት ብቻ ባለመሆኑ ሁሉም የዘርፉ ባለድርሻ አካላትና ግለሰቦች ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ማቅረባቸውን ከንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

@admasradio
159 views14:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-01 17:48:07
በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረውን የትራንስፖርት አገልግሎት በማስጀመር የፌዴራል ፖሊስ አባላት ትልቁን ድርሻ እንደተወጡ ተገለጸ

በትግራይ ክልል ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የትራንስፖርት አገልግሎት በማስጀመር የፌዴራል ፖሊስ አባላት ትልቁን ድርሻ እንደተወጡ የመቀሌ ከተማ መንገድና ትራንስፖርት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ከበደ አሰፋ የመንግስትን ጥሪ በመቀበል ስራውን የጀመረው ጽህፈት ቤቱም ፣ ባሉት ውስን ሠራተኞች ፋይሎችን በማደራጀትና የተሰባበሩትን በመጠገን ወደ ስራ በመግባት ለመቐለ ከተማ ህብረተሰብ አገልግሎት እየሰጠ እንዳለ አቶ ከበደ አሰፋ ገልፀዋል፡፡

የሚያስፈልገውን የትራንስፖርት አገልግሎት በአራቱም አቅጣጫ ኬላዎች ህጋዊ እንቅስቃሴ እንዲፈጠርና ከታሪፍ ውጭ የሚያስከፍሉ አሽከርካሪዎችን በማስተማር ፌዴራል ፖሊስ እየሰራ ስለመሆኑም ጠቁመዋል፡፡

ኃላፊው አክለውም የፌዴራል ፖሊስ የስራ ጫናን ለመቀነስ የክልሉ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ የክልሉን ትራፊክ ፖሊስና የመንገድ ትራንስፖርት ተቆጣጣሪ ሰራተኞችን ወደ ስራ በማሰማራት አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ ስለመሆኑም ተናግረዋል፡፡

ሰላም ወዳዱ የትግራይ ህዝብ ቀድሞ ወደ ነበረበት እንዲመለስ ፣ የታመሙ ህክምና እንዲያገኙ ፣ ልጆች እንዲማሩ የሁሉም ሰው ኃላፊነት መሆኑን በመገንዘብ ከፀጥታ ኃይሉ ጎን በመቆም አስተማማኝ ሰላሙን ማረጋገጥ አለበት ሲሉ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ብስራት ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

@admasradio
148 views14:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ