Get Mystery Box with random crypto!

‹‹የሸገር ድጋፍ ሰጪ አውቶቡሶች አገልግሎት ውል ይቋረጣል›› በሚል የወጣው መረጃ የተሳሳተ ነው ተ | አድማስ ሬድዮ- Admas Radio

‹‹የሸገር ድጋፍ ሰጪ አውቶቡሶች አገልግሎት ውል ይቋረጣል›› በሚል የወጣው መረጃ የተሳሳተ ነው ተባለ

የሸገር ድጋፍ ሰጪ አውቶቡሶች አገልግሎት ውል በ1 ወር ጊዜ ውስጥ ይቋረጣል በሚል በአንዳንድ መገናኛ ብዙሃን የተላለፈው መረጃ የተሳሳተ ነው ሲል በአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አረጋዊ ማሩ በተለይ ለብስረት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

መረጃው የተላለፈው ከቢሮው እውቅና ውጪ መሆኑን ውድ የከተማዋ ነዋሪዎች እንዲያውቁት ሲሉ ቢሮው አጽንኦት ሰጥቷል፡፡

በድጋፍ ሰጪ አውቶቡሶች አገልግሎት ቀጣይ ሁኔታን በተመለከተ በከተማዋ ካቢኔ ሲወሰን የሚገለፅ መሆኑን አቶ አረጋዊ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የሚታየውን የትራንስፖርት እጥረት ለመቅረፍ ፣ የትራንስፖርት ቢሮ ከአገር አቋራጭ ትራንስፖርት ማህበራት ጋር ከጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ውል ተይዞ ወደ ስራ መገባቱ ይታወሳል፡፡

(ብስራት ራዲዮ)
@admasradio