Get Mystery Box with random crypto!

በትግራይ ክልል ጉዳት የደረሰባቸውን ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ ነው በትግራይ ክ | አድማስ ሬድዮ- Admas Radio

በትግራይ ክልል ጉዳት የደረሰባቸውን ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ ነው

በትግራይ ክልል የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በተወሰደው እርምጃ ፣ ጉዳት የደረሰባቸውን የማምረቻ ተቋማት ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ገልጸዋል፡፡

በክልሉ የሚገኙ ጉዳት የደረሰባቸው ተቋማት ወደ ቀድሞ የማምረት ተግባራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የጉዳቱን መጠን የሚያጠና ኮሜቴ አቋቁሞ ወደ ክልሉ መላኩን ተናግረዋል፡፡

ጥናቱን መነሻ በማድረግ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለችግሩ መፍትሔ ለመስጠት ዝግጁ መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡

የማምረቻ ኢንዱስትሪዎችን ወደ ቀደመ የምርት ሂደት ለመመለስ ከሚደረገው ጥረት በተጓዳኝ በክልሉ የመሰረታዊ ሸቀጦች አቅርቦት ችግር እንዳይከሰት ሚኒስቴሩ ከተጠሪ ተቋማትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር በትኩረት እየሰራ ይገኛልም ነው ያሉት፡፡

የማምረቻ ተቋማቱን ወደ ቀድሞ የስራ እንቅስቃሴ መመለስ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር እና የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሃላፊነት ብቻ ባለመሆኑ ሁሉም የዘርፉ ባለድርሻ አካላትና ግለሰቦች ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ማቅረባቸውን ከንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

@admasradio