Get Mystery Box with random crypto!

በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረውን የትራንስፖርት አገልግሎት በማስጀመር የፌዴራል ፖሊስ አባላት ትል | አድማስ ሬድዮ- Admas Radio

በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረውን የትራንስፖርት አገልግሎት በማስጀመር የፌዴራል ፖሊስ አባላት ትልቁን ድርሻ እንደተወጡ ተገለጸ

በትግራይ ክልል ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የትራንስፖርት አገልግሎት በማስጀመር የፌዴራል ፖሊስ አባላት ትልቁን ድርሻ እንደተወጡ የመቀሌ ከተማ መንገድና ትራንስፖርት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ከበደ አሰፋ የመንግስትን ጥሪ በመቀበል ስራውን የጀመረው ጽህፈት ቤቱም ፣ ባሉት ውስን ሠራተኞች ፋይሎችን በማደራጀትና የተሰባበሩትን በመጠገን ወደ ስራ በመግባት ለመቐለ ከተማ ህብረተሰብ አገልግሎት እየሰጠ እንዳለ አቶ ከበደ አሰፋ ገልፀዋል፡፡

የሚያስፈልገውን የትራንስፖርት አገልግሎት በአራቱም አቅጣጫ ኬላዎች ህጋዊ እንቅስቃሴ እንዲፈጠርና ከታሪፍ ውጭ የሚያስከፍሉ አሽከርካሪዎችን በማስተማር ፌዴራል ፖሊስ እየሰራ ስለመሆኑም ጠቁመዋል፡፡

ኃላፊው አክለውም የፌዴራል ፖሊስ የስራ ጫናን ለመቀነስ የክልሉ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ የክልሉን ትራፊክ ፖሊስና የመንገድ ትራንስፖርት ተቆጣጣሪ ሰራተኞችን ወደ ስራ በማሰማራት አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ ስለመሆኑም ተናግረዋል፡፡

ሰላም ወዳዱ የትግራይ ህዝብ ቀድሞ ወደ ነበረበት እንዲመለስ ፣ የታመሙ ህክምና እንዲያገኙ ፣ ልጆች እንዲማሩ የሁሉም ሰው ኃላፊነት መሆኑን በመገንዘብ ከፀጥታ ኃይሉ ጎን በመቆም አስተማማኝ ሰላሙን ማረጋገጥ አለበት ሲሉ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ብስራት ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

@admasradio