Get Mystery Box with random crypto!

ሀገር አቀፍ የ”እንድናገለግልዎ ማስክ ያድርጉ” ንቅናቄ ከነገ ጀምሮ በትምህርት ቤቶች ይጀመራል፡፡ | አድማስ ሬድዮ- Admas Radio

ሀገር አቀፍ የ”እንድናገለግልዎ ማስክ ያድርጉ” ንቅናቄ ከነገ ጀምሮ በትምህርት ቤቶች ይጀመራል፡፡

የጤና ሚኒስቴር ዶክተር ሊያ ታደሰ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኮሮና ወረርሽኝ ስርጭት መጨመሩን እና በፍጥነት የሚዛመት አዲስ የኮሮናቫይረስ መገኘቱን አንስተዋል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም ከወትሮው የተለየ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ በበኩላቸው፥ ትምህርት ቤቶች የተከፈቱ ሰሞን የጥንቃቄ እርምጃዎች በተገቢው መልኩ ሲተገበሩ ቢቆዩም በቅርቡ ግን መዘናጋቶች መተስተዋላቸውን ገልጸዋል።

ይህ መዘናጋት ዋጋ እንዳያስከፍል “የእንድናገለግልዎ ማስክ ያድርጉ” ንቅናቄ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ከነገ ጀምሮ እንደሚካሄድ ተናግረዋል። በንቅናቄው በሁሉም ትምህርት ቤቶች ያሉ ተመሪዎች፣ መምህራን እና የትምህርት ሠራተኞች በትምህርት ቤቶቻቸው አቅራቢያ በእግር በመጓዝ “እንድናገለግል ማስክ ያድርጉ” የሚል ግንዛቤ ይሰጣሉ ተብሏል።

(AMN)
@admasradio