Get Mystery Box with random crypto!

አድማስ ሬድዮ- Admas Radio

የቴሌግራም ቻናል አርማ admasradio — አድማስ ሬድዮ- Admas Radio
የቴሌግራም ቻናል አርማ admasradio — አድማስ ሬድዮ- Admas Radio
የሰርጥ አድራሻ: @admasradio
ምድቦች: ሙዚቃ
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 1.80K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ከሰሜን አሜሪካዋ ደማቅ ከተማ አትላንታ እየተዘጋጀ በመላው ዓለም የሚተላለፈው
የ አድማስ ሬድዬ የቴሌግራም ቻናል ነው።
www.admasradio.info
melethio23@gmail.com
mike@admasradio.info

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2021-02-01 17:48:07
ሀገር አቀፍ የ”እንድናገለግልዎ ማስክ ያድርጉ” ንቅናቄ ከነገ ጀምሮ በትምህርት ቤቶች ይጀመራል፡፡

የጤና ሚኒስቴር ዶክተር ሊያ ታደሰ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኮሮና ወረርሽኝ ስርጭት መጨመሩን እና በፍጥነት የሚዛመት አዲስ የኮሮናቫይረስ መገኘቱን አንስተዋል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም ከወትሮው የተለየ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ በበኩላቸው፥ ትምህርት ቤቶች የተከፈቱ ሰሞን የጥንቃቄ እርምጃዎች በተገቢው መልኩ ሲተገበሩ ቢቆዩም በቅርቡ ግን መዘናጋቶች መተስተዋላቸውን ገልጸዋል።

ይህ መዘናጋት ዋጋ እንዳያስከፍል “የእንድናገለግልዎ ማስክ ያድርጉ” ንቅናቄ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ከነገ ጀምሮ እንደሚካሄድ ተናግረዋል። በንቅናቄው በሁሉም ትምህርት ቤቶች ያሉ ተመሪዎች፣ መምህራን እና የትምህርት ሠራተኞች በትምህርት ቤቶቻቸው አቅራቢያ በእግር በመጓዝ “እንድናገለግል ማስክ ያድርጉ” የሚል ግንዛቤ ይሰጣሉ ተብሏል።

(AMN)
@admasradio
142 views14:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-01 17:48:07
ከአጭበርባሪዎች ይጠንቀቁ!

የኤሌክትሪክ ቆጣሪ እናስገባለን በሚል ሰበብ ህገወጥ ድርጊት የሚፈፅሙ ግለሰቦች ስላሉ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳሰበ።

ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር ተያይዞ ለሚቀርቡ ሌሎች ማንኛውም ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጠውም ይህ ተቋም ሳለ ከህጋዊ አሰራር ውጭ የተቋሙ ሠራተኛ በመምሰል እኩይ ዓላማ ያነገቡ ግለሰቦች የኤሌክትሪክ ቆጣሪ እናስገባለን በሚል በህገ-ወጥ መንገድ ከህብረተሰቡ ገንዘብ የሚቀበሉ ግለሰቦች መኖራቸውን ተቋሙ በደረሰው ጥቆማና ባደረገው ማጣራት ማረጋገጡን ገልጿል።

ለአብነትም ነዋሪነቷ በአዲስ አበባ ከተማ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 የሆነች አንዲት ግለሰብ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የማያውቀው ነገር ግን "ከተቋሙ ነው የመጣነው ቆጣሪ እናስገባልሻለን" ብለው በማታለል ገንዘብ ተቀብለዋት ህጋዊ ያልሆነ የኤሌክትሪክ ቆጣሪ ገጥመውላታል። ግለሰቧ ለእነዚህ ሰዎች በሐሰተኛ እሴት ታክስ ደረሰኝ 12 ሺህ ብር የከፈለቻቸው ቢሆንም ድርጊቱ ከተቋሙ እውቅና ውጪ እንደነበር ነው የተጠቀሰው።

በመጨረሻም በተደረገው ማጣራት የተገጠመው ቆጣሪ ህገወጥና ትክክለኛውን የአሰራር ስርዓት ተከትሎ የተፈፀመ አለመሆኑን ተደርሶበት የተገጠመላት ቆጣሪ አገልግሎት እንዳይሰጥ መደረጉንም ነው የተገለጸው። ህብረተሰቡ እንደነዚህ አይነት መሰል እኩይ ድርጊቶች ሊያጋጥመው ስለሚችል አስፈላጊ ጥንቃቄ እንዲወስድ ተቋሙ ያሳስባል። ተቋሙ የአዲስ ቆጣሪ ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥበት የራሱ የሆነ የአሰራር ስርዓት የዘረጋ መሆኑ ታውቆ፤ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል።

(Ebc)
@admasradio
157 views14:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-01 16:00:27
ለክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ የምስጋና እና እውቅና ፕሮግራም እንደሚካሄድ የኦሮሚያ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ኃላፊ ከበደ ዴሲሳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት የእውቅና እና የምስጋና ፕሮግራሙ ጥር 30 ቀን 2013 ዓ.ም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ አድናቂዎቹ እና የአርቲስቱ ወዳጆች በተገኙበት ይካሄዳል፡፡

መርሃግብሩም አርቲስቱ ከ60 ዓመታት በላይ ለኦሮሞ ኪነ-ጥበብ እድገት ላበረከተው ጉልህ አስተዋጽኦ እውቅና ለመስጠት መዘጋጀቱን ነው የገለጹት።

አርቲስቱ ለኢትዮጵያ ህዝቦች አብሮነትና ማህበራዊ ትስስር ከፍ ያለ አስተዋጽኦ ማበርከቱንም ጨምረው ተናግረዋል።

በሙዚቃዎቹ ዘመን ተሻጋሪ መልዕክቶችን በማስተላለፍ መልካም ትውልድ እንዲቀረጽ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉም ተገልጿል።

በወቅታዊ ክስተቶች ሳይሸነፍ በከፍተኛ ጽናትና ብቃት ለረጅም ዓመታት በኪነ ጥበቡ ውስጥ ያሳለፈ መሆኑ ደግሞ አሁን ላለው ትውልድ ታላቅ ተምሳሌት እንደሚያደርገውም አውስተዋል።

ጥር 30 ቀን 2013 ዓ.ም በሚካሄደው መርሃግብር የአርቲስቱ የሕይወት ታሪክ እና ሥራዎች ላይ የተፃፈ መጽሐፍ እንደሚመረቅም ኃላፊው መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ በ1954 ዓ.ም የተመሰረተውን የመጀመሪያው የኦሮሚኛ ቋንቋ የኪነት-ቡድን “አፍረን ቀሎ”ን በመቀላቀል ነበር የሙዚቃ ስራውን የጀመረው።

አርቲስቱ ከኦሮሚኛ በተጨማሪ፣ በሱማሊኛ፣ በአፋርኛ፣ በሐረሪ፣ በአማርኛ እና በሱዳን ቋንቋዎች በርካታ ዘፈኖችን መጫወት ችሏል።

@admasradio
168 views13:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-01 16:00:26
የገቢዎች ሚኒስቴር በግማሽ በጀት ዓመቱ 149 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ።

የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው በዛሬው ዕለት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በ2013 ዓ.ም የመጀመሪያ ስድስት ወራት 149 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን አስታውቀዋል።

የገቢ አፈጻጸሙ የዕቅዱን 102 ከመቶ ሲሆን ካለፈው ዓመት ስድስት ወራት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸርም የ21 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ማለትም የ17 በመቶ ብልጫ አለው ተብሏል።

ከአገር ውስጥ ገቢ 93 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር፣ ከወጪ ንግድ ቀረጥ እና ታክስ 55 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር፣ ከብሔራዊ ሎተሪ 130 ሚሊየን ብር መገኘት መቻሉ ተጠቁሟል።

ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ለገቢው ከፍ ማለት ኢ-ታክስ መጀመር፣ ለግብር ከፋዮች እና ለተቋሙ ሠራተኞች የእውቅና አሰጣጥ መጀመሩን ጨምሮ ዘመናዊ የግብር አሠራር ተግባራዊ መደረጉ አስተዋጽኦ ማድረጉ ተጠቅሷል።

(EBC)
@admasradio
152 views13:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-01 16:00:26
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በጻፈው ደብዳቤ የተማሪ ከተቋም ተቋም ዝውውር እንዳይፈጸም አሳስቧል።

አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ተማሪዎች የሚያቀርቡትን የዝውውር ጥያቄ ተቀብለው እያስተናገዱ ነው ያለው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከቀን 21/05/2013 ቀን ጀምሮ ዝውውር እንዳይፈጸም አግዷል።

በዚህ የትምህርት ዘመን ዝውውር የሚፈጸመውም በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በልዩ ሁኔታ ታይቶ ሲፈቀድ ብቻ እንደሆነ አሳስቧል።

(MoSHE)
@admasradio
142 views13:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-01 16:00:26
ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበትን ቀን እንዲያሳውቅ ተጠየቀ።

ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበትን 'ቁርጥ' ያለ ቀን እንዲያሳውቅ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሳስቧል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ በበኩላቸው "ፈተናው የሚሰጥበትን ቀን ለማሳወቅ ለፈተናው የሚያስፈልጉት 400 ሺህ 'ታብሌቶች' ወደ አገር ውስጥ አልገቡም" ብለዋል።

ለዚህም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር እንደሚሰራና 'ታብሌቶቹ' ወደ አገር ሲገቡ ፈተናው የሚሰጥበት ቀን እንደሚወሰን ተናግረዋል።

የፈተና አሰጣጥ ሂደቱን ለማቀላጠፍ በ1 ሺህ 500 የፈተና ጣቢያዎች አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም አስረድተዋል።

(ENA)
@admasradio
146 views13:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-01 14:57:33 ያልታጠፈው ቃልኪዳን!!!!
(ራኬብ ሳሙኤል)

- "ኤርትራ የዋለችውን ውለታ በልባችን ጽላት ላይ ጽፈነዋል። ቀጣዪም ትውልድ ይዘምረዋል።

አገራችን ባላት እረጅም ዘመናትን ያስቆጠሩ ነባራዊ የታሪክ፣ የጆፖለቲካና ተያያዥ ጉዳዮች የተነሳ በብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ ማለፏ የተነሳ ዛሬ ኤርትራ እራሷን የቻለች ሉአላዊ አገር የሆነችበትን ሂደት መፍጠሩ እርግጥ ነው።
ያም ሆኖ ግን ከውጫዊው ተጽእኖ በላይ የተጋመድንበት የማንነት እሴት ይበልጥ ጥልቅ በመሆኑ በዚህ ሁሉ መውደቅና መነሳትም መካከል እንኳን እጣ ፋንታችን የማይለያይ ሆኖ ለመውጣቱ የሰሞኑን ክስተት ምስክር ነው።

ለእሩብ ክፍለ ዘመናት ያህል ማእከላዊውን መንግስት ለመቆጣጠር እድሉን ያገኙት ደደቢታውያን በስልጣን ላይ ለመቆየት ከነበራቸው ስር የሰደደ ፍላጎት የተነሳ እንበለ መርህ ከምእራቡም፣ ከምስራቁም፣ ከአረቡም ከጎረቤት አገሮችም ሳይቀር አንሶላ ይጋፈፉ ስለነበር ኢትዮጵያውያን ይህንን ጋንግሪን የሆነ ስርዓት ለመገልበጥ ከማተባችንና ከኤርትራ ውጭ ተስፋ የምናደርገው አንድም አጋዥ ሃይል አገር አልነበረንም። በመሆኑም ይህችኑ የቀረችንን አንድያይቱን የብርሃን ጭላንጭል ደግሞ ለማዳፈን ከመለስ ዜናዊ እስከ ደብረጽዮን ከሰባ ግዜ በላይ የሻቢያን ቢሮ አንኳኩተዋል። ከጸሃይ መውጫ እስከ ጸሃይ መግቢያ ድረስ ያሉ ነገስታትን አማላጅ ልከዋል።

ይህ አልሳካ ሲል ከድሃ ጉሮሮ የሚዘረፈውን ረብጣ ዶላር በማፍሰስ ሻቢያን ከውስጥ ለማፍረስም ሆነ በነጮች እርዳታ አንገት ለማስደፋት እስከ ሲዖል ዳርቻ ተጉዘዋል። ያም ሆኖ ግን ሻቢያ የቆመበትን የሞራል መሰረት ማናጋት አልተቻላቸውም። ደደቢታውያን በስልጣን ላይ በኖሩበት ዘመን ሁሉ በመልካቸው የቀረጿቸውን ተውሳኮች በመጠቀም ይልቁንም ባለፉት ሁለት አመታት አገሪቱን በአራቱም ማእዘን ለማንደድ ያልሳቡት ካርታ አልነበረም።

በዚህ ሁሉ ጸረ ኢትዮጵያ ዘመቻ የቆሰለችን አገር ገንዘው ለመቅበር የመጨረሻውን ምላጭ የሳቡት ደደቢታውያን በፍጻሜው ጦርነት ግብዓተ መሬታቸው ሲጠናቀቅ ኤርትራ የዋለችውን ውለታ በልባችን ጽላት ላይ ጽፈነዋል። ቀጣዪም ትውልድ ይዘምረዋል። ጨረስኩ!!!

(Eritrean press )
@admasradio
142 views11:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ