Get Mystery Box with random crypto!

የገቢዎች ሚኒስቴር በግማሽ በጀት ዓመቱ 149 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ። የ | አድማስ ሬድዮ- Admas Radio

የገቢዎች ሚኒስቴር በግማሽ በጀት ዓመቱ 149 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ።

የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው በዛሬው ዕለት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በ2013 ዓ.ም የመጀመሪያ ስድስት ወራት 149 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን አስታውቀዋል።

የገቢ አፈጻጸሙ የዕቅዱን 102 ከመቶ ሲሆን ካለፈው ዓመት ስድስት ወራት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸርም የ21 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ማለትም የ17 በመቶ ብልጫ አለው ተብሏል።

ከአገር ውስጥ ገቢ 93 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር፣ ከወጪ ንግድ ቀረጥ እና ታክስ 55 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር፣ ከብሔራዊ ሎተሪ 130 ሚሊየን ብር መገኘት መቻሉ ተጠቁሟል።

ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ለገቢው ከፍ ማለት ኢ-ታክስ መጀመር፣ ለግብር ከፋዮች እና ለተቋሙ ሠራተኞች የእውቅና አሰጣጥ መጀመሩን ጨምሮ ዘመናዊ የግብር አሠራር ተግባራዊ መደረጉ አስተዋጽኦ ማድረጉ ተጠቅሷል።

(EBC)
@admasradio