Get Mystery Box with random crypto!

ያልታጠፈው ቃልኪዳን!!!! (ራኬብ ሳሙኤል) - 'ኤርትራ የዋለችውን ውለታ በልባችን ጽላት ላይ ጽ | አድማስ ሬድዮ- Admas Radio

ያልታጠፈው ቃልኪዳን!!!!
(ራኬብ ሳሙኤል)

- "ኤርትራ የዋለችውን ውለታ በልባችን ጽላት ላይ ጽፈነዋል። ቀጣዪም ትውልድ ይዘምረዋል።

አገራችን ባላት እረጅም ዘመናትን ያስቆጠሩ ነባራዊ የታሪክ፣ የጆፖለቲካና ተያያዥ ጉዳዮች የተነሳ በብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ ማለፏ የተነሳ ዛሬ ኤርትራ እራሷን የቻለች ሉአላዊ አገር የሆነችበትን ሂደት መፍጠሩ እርግጥ ነው።
ያም ሆኖ ግን ከውጫዊው ተጽእኖ በላይ የተጋመድንበት የማንነት እሴት ይበልጥ ጥልቅ በመሆኑ በዚህ ሁሉ መውደቅና መነሳትም መካከል እንኳን እጣ ፋንታችን የማይለያይ ሆኖ ለመውጣቱ የሰሞኑን ክስተት ምስክር ነው።

ለእሩብ ክፍለ ዘመናት ያህል ማእከላዊውን መንግስት ለመቆጣጠር እድሉን ያገኙት ደደቢታውያን በስልጣን ላይ ለመቆየት ከነበራቸው ስር የሰደደ ፍላጎት የተነሳ እንበለ መርህ ከምእራቡም፣ ከምስራቁም፣ ከአረቡም ከጎረቤት አገሮችም ሳይቀር አንሶላ ይጋፈፉ ስለነበር ኢትዮጵያውያን ይህንን ጋንግሪን የሆነ ስርዓት ለመገልበጥ ከማተባችንና ከኤርትራ ውጭ ተስፋ የምናደርገው አንድም አጋዥ ሃይል አገር አልነበረንም። በመሆኑም ይህችኑ የቀረችንን አንድያይቱን የብርሃን ጭላንጭል ደግሞ ለማዳፈን ከመለስ ዜናዊ እስከ ደብረጽዮን ከሰባ ግዜ በላይ የሻቢያን ቢሮ አንኳኩተዋል። ከጸሃይ መውጫ እስከ ጸሃይ መግቢያ ድረስ ያሉ ነገስታትን አማላጅ ልከዋል።

ይህ አልሳካ ሲል ከድሃ ጉሮሮ የሚዘረፈውን ረብጣ ዶላር በማፍሰስ ሻቢያን ከውስጥ ለማፍረስም ሆነ በነጮች እርዳታ አንገት ለማስደፋት እስከ ሲዖል ዳርቻ ተጉዘዋል። ያም ሆኖ ግን ሻቢያ የቆመበትን የሞራል መሰረት ማናጋት አልተቻላቸውም። ደደቢታውያን በስልጣን ላይ በኖሩበት ዘመን ሁሉ በመልካቸው የቀረጿቸውን ተውሳኮች በመጠቀም ይልቁንም ባለፉት ሁለት አመታት አገሪቱን በአራቱም ማእዘን ለማንደድ ያልሳቡት ካርታ አልነበረም።

በዚህ ሁሉ ጸረ ኢትዮጵያ ዘመቻ የቆሰለችን አገር ገንዘው ለመቅበር የመጨረሻውን ምላጭ የሳቡት ደደቢታውያን በፍጻሜው ጦርነት ግብዓተ መሬታቸው ሲጠናቀቅ ኤርትራ የዋለችውን ውለታ በልባችን ጽላት ላይ ጽፈነዋል። ቀጣዪም ትውልድ ይዘምረዋል። ጨረስኩ!!!

(Eritrean press )
@admasradio